/

Hiber Radio: በኢትዮጵያ ሰራዊቱ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ትግል የሚቀላቀልበት ጊዜ ሲመጣ ትግሉን ይቀላቀላል ሲል ጃዋር መሐመድ ገለጸ፣

የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በ ያሳለፈው ጠንካራ ውሳኔ በተግባር እንዲውል ኦነግ ጠየቀ፣የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ የአገር ቤቱ ትግል ውጤት መሆኑ ተገለጸ፣ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ መንግስት ክህደት መፈጸሙን ገለጹ፣ በኢትዮጵያ እየታየው ያለው ያለመረጋጋት እና የደህንነት እጦት ምዕራባዊያን ኢንቨስተሮችን እንዳያሸሽ አስግቷል የሚሉና ቃለ መጠይቅ ከጃዋር መሀመድ ጋር፣የአቶ ነአምን ዘለቀ ስለሰራዊቱ የተናገሩትና ሌሎችም አሉን

Hiber
የህብር ሬዲዮ ጥር 15 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ ሕግ ነው አገራቱ ተግባራዊ የሚያደርጉት ትልቅና ጠንካራ ውሳኔ ነው።ይሄበኦሮሞ ትግል ውጤት የተገኘ እንጂ አውሮፓውያኑ ዝም ብሎ ስለፈለጉ ብቻ የሆነ አይደለም። ሌላውምበኦሮሞ እንደታየው በመግለጫ ብቻ ሳይሆን በተግባር ስራ መስራት አለበት።ተቃውሞን በመግለጫ ብቻጥቅም የለውምሰራዊቱም የተነሳውን ተቃውሞ እንደ  ሀኪሙ፣መምህሩ፣ሰራተኛው ሁሉ ጊዜው ሲደርስይቀላቀላል። ሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ አመራሩም ተቃውሞውን ይቀላቀለቀል አስቀድሞ ታስቦበትየተሰራበት ስትራቴጂ ነው ።ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ይታያል…>   ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክዋና ዳይሬክተር የአውሮፓ ፓርላማን ውሳኔ መሰረት አድርገን በወቅታዊ ጉዳይ ለጠየቅነው    ከሰጠን ቃለመጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኦርላንዶ ፍሎሪዳ የገቢ ማሰባሰቢያ በተመለከተ (ቆይታ ከዝግጅቱ አስተባባሪዎችጋር)

<<…ሰራዊቱ ብሄራዊ መነሳሳት ሲኖር ሁሉንም ወገን የሚያሳትፍ አጀንዳ ተቀርጾ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱምሆነ የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ ሲቀጥል ከሕዝቡ ጎን ይሰለፋ።በጭቆና ውስጥ ያለ በዘረኛና ባልተማሩትየወያኔ  የጦር ጄኔራሎች የሚመራ ሰራዊት እነሱ እንዳሰቡት አብሯቸው በአንድ ላይ የሚቆም አይደለም።ዛሬ በኦሮሞ አካባቢ የሚደረገው ትግል በሁሉም አካባቢዎች ሕዝቡ ለመብቱ እምቢ ለወያኔ አልገዛም ብሎመንቀሳቀስ አለበት። ለዚህም ንቅናቄያችን…> አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጭ ግንኙነትሀላፊ በኦርላንዶ ፍሎሪዳ ተገኝተው ካደረጉት ንግግር መካከል ሰራዊቱን በተመለከተ ከተናገሩትየተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

 

በቬጋስ የሚገኘው የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲፈርስ የተጠየቀበትን የኦዲት ሪፖርት መሰረት አድርጎየተደረገ ውይይት (ቀሪውን ያዳምጡት)

 

በቱኒዚያ ውስጥ ሰሞኑን የአንድ ስራ አጥ ወጣት ራሱን በኤሌክትሪክ ሽቦ ላይ ተንጠልጥሎ መሞትን ተከትሎያገረሸው አመጽ እና ያስከተለው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ  (ልዩ ዘገባ)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ሰራዊቱ በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ትግል የሚቀላቀልበት ጊዜ ሲመጣ ትግሉን ይቀላቀላል  ሲልጃዋር መሐመድ ገለጸ

የአውሮፓ ፓርላማ ውሳኔ የአገር ቤቱ ጠንካራ ትግል ውጤት መሆኑ ተገለጸ

የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በኢትዮጵያው አገዛዝ ላይ ያሳለፈው ጠንካራ ውሳኔ በተግባር እንዲውል ኦነግጠየቀ

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ መንግስት ክህደት መፈጸሙን ገለጹ

በኢትዮጵያ እየታየው  ያለው ያለመረጋጋት እና  የደህንነት እጦት ምዕራባዊያን ኢንቨስተሮችን እንዳያሸሽአስግቷል

በአዋሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

በኢትዮጵያ ውስጥ ለተንሰራፋው ድርቅ እና ርሃብ አለማቀፋዊ በቂ ማላሽ መታጣቱ የበጎ አድራጊድርጅቶችን  በእጅጉ ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል

የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በጠበቃና በቤተሰብ ሳይጎበኝ ሌላ ተጨማሪ ጊዜለፖሊስ ተፈቀደ

ግብጽ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኖችን ከአገሯ አባረረች፣ታንዛኒያ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞችን ወደ እስርቤት መወረወሯ ታወቀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ