መምህር ግርማ ወንድሙ በ50 ሺህ ብር ዋስ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው አጥማቂና መምህር ግርማ ወንድሙ ከታሰሩበት የማጭበርበር ክስ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን ከአዲስ አበባ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ሲያመለከቱ ቤተክህነት ባቀረበችባቸው ተጨማሪ ክስ ደግሞ ህዳር 3 ቀን 2015 ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተሰማ::

በፖሊስ ዛሬው ዕለት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የመምህር ግርማን ግብረ አበሮች አልያዝኩም በሚል ተጨማሪ 14 ቀን ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል:: ጥቅምት 18 2008 ፖሊስ 14 ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆባቸው ችሎቱ 7 ቀን ፈቅዶ የነበረ ቢሆንም በዚህ ግዜ ውስጥ ፖሊስ አገኘሁት ያለው ማስረጃ በተጠርጣሪው ቤት በተደረገው ብርበራ 8 የሞባይል ሲም ካርዶችን ማግኘቱንና የተጠርጣሪው ግብረ አበር እየተፈለገ መሆኑን በመጥቀስ እነዚህን ቀሪ የምርመራ ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ተጨማሪ 14 ቀን ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶቹ በማን ስም ወጡ እና የያዙትን መረጃ ለመጠባበቅ 5 ቀን ፈቅዶ የነበረ መሆኑን ገልጿል::

ፖሊስ አሁንም ከቴሌ መረጃዎችን በመጠበቅ ላይ በመሆኑ 14 ቀን ይሰጠኝ ሲል ሲጠይቅ የመምህር ግርማ ጠበቃ በበኩላቸው ባለፈው ቀጠሮ ከኢትዮ ቴሌኮም የሚመጣውን ውጤት ለመጠባበቅ ብቻ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሰጠው አስታውስው ፖሊስ በዛሬው ቀጠሮ ምንም የሰራው ስራ የለም ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ተጠርጣሪ ለመያዝ በባለፈው ቀጠሮ ተጨማሪ ጊዜ አልፈቀደም የሚለውንም እንዳልተቀበለው አስታውሰዋል። አንድን ተጠርጣሪ አስሮ ሌላ ተጠርጣሪ ማፈላለግ ህጉ እንደማይፈቅድ እና ደንበኛችን የተጠረጠሩበት ወንጀልም የዋስትና መብት የሚከለክል ባለመሆኑ በተመጣጣኝ ዋስትና ደንበኛችን እንዲለቀቁ ሲል አመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የመርማሪ ፖሊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ይለቀቁ ሲል ወስኗል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕወሓቱ ልሳን ወይን ጋዜጣ አዘጋጅ ደብዛው ጠፋ

በሌላ በኩል መምህር ግርማ ላይ ቤተክህነት ያቀረበችው ክስ መሠማት ይጀምራል:: በሌላ ክስ ህዳር 3 2008 ፍርድ ቤት የሚቀርቡት መምህር ግርማን ጉዳይ ተከታትለን እንዘግባለን::

መምህር ግርማ ወንድሙ በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን አካባቢ የአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤትን እምነታቸውን በመጠቀም በ2006 እስከ ጥር 30 ይህን ቤት ለቀው ካልወጡ አስከሬንዎ ይወጣል በማለት በማስፈራራት ግለሰቡ እጅግ በጣም አነስትኛ በሆነ ዋጋ በ700 ሺህ ብር እንዲሸጡ እና ይህንንም ገንዘብ ልፀልይበት ብለው ወስደዋል በሚል በማታለል ወንጀል መጠርጠራቸው ይታወሳል።

2 Comments

Comments are closed.

Share