ኣሸጎዳ የንፋስ መብራት ማመንጫ ሃይል ዲናሞ በመቃጠሉ ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆነ

ከአምዶም ገብረሥላሴ

በመቐለ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኝ የኣሸጎዳ በንፋስ የሚሰራ ኤለክትሪክ ማመንጫ ሃይል በዲናሞ መቃጠል ምክንያት ከስራ ውጭ መሆኑ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ 150 ሜጋዋት የማመንጨት ኣቅም የነበረው ሲሆን ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በመቃጠሉ ሃይል የማመንጨት ኣቅሙ ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ ቅያሪ በሃገር ውስጥ እንደሌለና ከፈረንሳይ ሃገር እንደሚመጣ ታውቋል። የህወሓት የ40 ዓመት የልደት በዓል እንደ ታላቅ ውጤትና ማጣፈጫ ተደርጎ ሊወሰደ ታስቦ የነበረ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቁጣና ድንጋጤ መፍጠሩ ታውቋል።

የትግራይ ባለስልጣናት እንደ ግዝያዊ መፍትሄ ኣድርገው የወሰዱት የየካቲት በዓል እስኪያልፍ ከፈርንሳይ በክራይ እንዲመጣና ብልሸት እንዳልደረሰው ኣስመስሎ በማሳለፍ በዓሉ ከተጠናቀቀ በሗላ ዲናሞው ወደ ፈረንሳይ እንዲመለስ የሚል ትእዛዝ ኣስተላልፈዋል። የህወሓት ባለስልጣና የየካቲት በዓል ታዳሚዎች ኣሳፋሪ በሆነ ድራማ ኣጭበርብረው ለመመልስ ከፈረንሳይ ዲናሞ ተከራይተው ካሳዩሗቹ በሗላ ተመልሰው ወደ መጣበት ይመልሱታል።

ህወሓት የዲናሞው መቃጠል ለየካቲት በዓል ማክበርያ ካወጣችው 1 ቢልዮን ብር ወጪ የምታወጣው ተጨማሪ ግዙፍ ብር ይሆናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰማያዊ ፓርቲ በተገደሉት ተማሪዎች ጉዳይ መግለጫ አወጣ፤ "የዜጎችን ጥያቄ በግድያ ማስቆም አይቻልም"

3 Comments

  1. ወያኔ የምትችለው በቁጥር ላይላዩን ጨዋታ እንጂ ማስላትና የሚገኘው ውጢት መተርጎም አይገባትም። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከ5 ተኛ ክፍል የዘለለ ትምህርት የላትም። የምታውቀው ዓራቱን መደብ ብቻ ነው። ይኽውም፦ መደበኛ ቁጥሮችን መደመር፤ መቀነስ፤ ማባዛትና ማካፈል ብቻ። ክፍልፋይ ቁጥርማ ማስላት ሞቷ ነው።

    • ኽኽኽኽኽኽኽኽኽኽኽኽ…………………..ያልክው ሁሉ ትክክል ነው……………. very funny i like it

Comments are closed.

Share