Breaking News: በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አዳዲስ ጳጳሳትን ሊሾም ነው

June 1, 2013
አቡነ መርቆሪዮስ እና የሲኒዶሱ አባቶች
(በዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ)
ፎቶ የዘ-ሐበሻ ምንጮች

(ዘ-ሐበሻ) ለረዥም ዓመታት በገለልተኝነት ቆይቶ አሁን ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ በተቀላቀለው የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ሲደረግ የሰነበተው የሕጋዊው ሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቀቀ። ላለፉት 6 ቀናት በዳላስ ከተማ ሲደረግ በቆየው የሲኖዶሱ ጉባኤ ላይ በርከት ያሉ ጉዳዮች የተነሱና ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገቡ።

የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች የጉባኤውን ፎቶ ግራፍ ጭምር በማያያዝ እንደዘገቡት ከሆነ ለጊዜው የቁጥራቸው ብዛት የማይገለጽ ጳጳሳት ሹመት እስከ መጪው ሐምሌ ወር ድረስ ይደረጋል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በጉባኤው ላይ በተለይ ባለፉት 6 ወራት የተሰሩ ሥራዎችን መገምገሙን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በጉባኤው ላይ ባለፉት ስድስት ወራት ቅዱስ ሲኖዶሱ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ከበፊቱ የተሻሉ ሥራዎችን መፈጸሙን፤ በገቢ ደረጃም ከፍተኛውን ገቢ እንዳስገኘ ተገልጿል ብለዋል።

በዚህ ጉባኤ ላይ በተለይ ለብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ሹመት ተሰጥቷል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሆኑ መደረጉንም አስታውቀዋል።

አቡነ ዮሐንስ የቴክሳስ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

በጉባኤው ላይ በቅርቡ በአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የማፈናቀል ተግባር አባቶቹ ማውገዛቸውን ያስታወቁት ምንጮቻችን በባህርዳር የተፈጸመውን ግድያም አባቶች አውግዘው ጸሎት እንዳደረጉላቸው ዘግበዋል።

በተለይም ባልተሳካው የሁለቱ ሲኖሶች እርቅ፤ ለእርቁ አለመሳካት ተጠያቂውን የወያኔ/ኢሕአዴግን መንግስት ተጠያቂ ያደረገው ይኸው ጉባኤ በሁለቱ ሲኖዶስ መካከል ወደ መግባባት ተደርሶ በመጨረሻው ላይ በመንግስት የተሰናከለው እርቅ ከአሁን በኋላ ሊሳካ የሚችለው ስርዓቱ ሲወድቅ ብቻ ስለሆነ ሕዝቡ ተደራጅቶ በአንድነት እንዲታገል፤ እንዲጸልይም ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ዛሬ ወይም ነገ ጠዋት ለሚዲያዎች እንደሚላክ ታውቋል። ዘ-ሐበሻም መግለጫው እንደደረሳት ለአንባቢዎቿ እንደምታካፍል ከወዲሁ ትገልጻለች።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስም በተመሳሳይ ጉባኤ ተቀምጦ ነው የሰነበተው። ስብሰባው በምን መልክ ይጠናቀቅ ይህን ዜና እስከሚጠናቀቅ ባንደርስበትም ትናንት ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ብሎግ ሲኖዶሱ የሚወያይባቸውን እና የማይወያይባቸውን ር ዕሶች ዘርዝሮ ነበር። ለግንዛቤዎ እንደወረደ ይኸው፦

 • ምልአተ ጉባኤው 18 የመነጋገሪያ አጀንዳዎችን ለይቶ ውይይቱን ቀጥሏል

ምልአተ ጉባኤው በዋናነት ከሚነጋገርባቸው ጉዳዮች ውስጥ፡-

 • ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሪ ዕቅድ መመራት እንዳለባት የታመነበት በመኾኑ መሪ ዕቅዱ ‹‹ተዘጋጅቶ ሲቀርብ›› ተመርምሮ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
 • የሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቃለ ዐዋዲ ማሻሻያ ረቂቆች በኮሚቴው ቀርበውና ተደምጠው ተጨማሪ ሐሳብ ይሰጥባቸዋል፤
 • በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደርና ሙስና ችግሮች ላይ ‹‹መጠነ ሰፊ›› ውይይት ተደርጎ ውሳኔ  ይተላለፋ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችና ድርጅቶች፣ በሁሉም አህጉረ ስብከት መዋቅሮች ሙስናን የመከላከያውና መቆጣጠርያው አግባብ ከሚያሰፍነው ጥብቅ ሥርዐት አንጻር አጀንዳው አነጋጋሪና አከራካሪ እንደሚኾን ይገመታል፡
 • የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥ/አስኪያጅ ምርጫ ይካሄዳል በቂ የሰው ኀይልና በበጀት ተደግፎ በሦስት ዴስኮች እንዲደራጅና የራሱ ወርኃዊ መጽሔት እንዲኖረው የተወሰነለት የውጭ ግንኙነት መምሪያ አዲስ ሓላፊና ሊቀ ጳጳስ ይሾምለታል፤ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የቅድሚያ ግምት የተሰጣቸው ቢኾንም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይጠበቃሉ፤
 • ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምን ጨምሮ አባቶች እንዲመደቡባቸው የሚያስፈልጉና ችግር ያለባቸው አህጉረ ስብከት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፤ በአጀንዳው የተጠቀሱት አህጉረ ስብከት÷ የአዲስ አበባ፣ የትግራይ ማእከላዊ ዞን አክሱም፣ የሐዋሳ ቡርጂና ቦረና ብቻ ናቸው፡፡ በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ የቅዱስ ላሊበላ ደብርና ሌሎች ወረዳዎች አስተዳደር ከሙስናና ጎጠኝነት፣ በድሬዳዋና ምዕ. ሐረርጌ፣ በምሥራቅ ጎጃም፣ በዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካከኑፋቄና ጎጠኝነት ጋራ የተያያዙ የካህናትና ምእመናን አንገብጋቢ ጥያቄዎችስ?
 • የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት አዲስ አሠራርን ተመርምሮና ተጣርቶ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡

ከሌሎች የምልአተ ጉባኤው አጀንዳዎች፡-

 • የቀድሞው ፓትርያሪክ ንብረትን በተመለከተ ውሳኔ መስጠት፤
 • ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ቀድሞ በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ) አስመልክቶ የቀረበውን ጽሑፍ በንባብ ሰምቶ መወሰን፤
 • የቀጣይ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን መመደብና በጽሑፍ የሚቀርቡ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የዝውውር ጥያቄዎችን መወሰን የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በምልአተ ጉባኤው አጀንዳ ያልተካተቱና ሊታዩ የሚገባቸው ወቅታዊ ጉዳዮች፡-

 • የአንድ ዓመት ጊዜ ገደብ የተሰጠው የፌዴራል ጉዳዮ ሚ/ር የሃይማኖትና እምነት ተቋማት ምዝገባ መመሪያ ረቂቅበተመለከተ ከቤተ ክርስቲያናችን አሐዳዊነት፣ ነባራዊነትና ሉዓላዊነት አኳያ የሚኖረን አቀባበል፤
 • የቅዱሳት መካናት /ገዳማትና አድባራት/ ይዞታና ክብር መጠበቅ ከመንግሥት ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች /በጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት፣ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት. . .አንጻር እንዲሁም የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ ጥፋት /መዝባዕ ገዳም/
 • በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  የትምህርት አስተዳደሩ ብቃትና አግባብነት ባላቸው ሓላፊዎችና ዲኖች እንዲመራ፣ አስተዳደሩ ከሙስናና ብልሹ አሠራር የጸዳ እንዲኾን ደቀ መዛሙር ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ኮሚቴው /ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሦስት፣ ከመንግሥት ሁለት አባላት የተውጣጡበት/ ያቀረበውና በዋናነት ሦስት ነጥቦችን የያዘው የመፍትሔ ሐሳብ፤ ከዚሁ ጋራ በተያያዘ የጠ/ቤተ ክህነቱ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ለመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን፣ የካህናት ማሠልጠኛዎቻችንና የአብነት ት/ቤቶቻችን አመራርና ድጋፍ ለመስጠት ያለው ብቃት፤  

3 Comments

 1. Abune Yohanes was a HUGE trouble maker in Portland Oregon. He was the archbishop of Ethiopian churches in Oregon. He is the first Ethiopian archbishop who sued members of the St. Mary ETOC in the county court. He was advised and begged by elders of the Portland area not to go to the court. He defied the elders and also the Ethiopian culture. He is a disgrace to the synod in exile!!! I hope he learned a lesson from the mess he created or else Dallas St. Michael people should watch out for their church and unity. We the members of the diaspora church under the exiled synod, have expressed our legitimate frustrations to the leaders of the synod both openly and behind the scene. However, it seems no one in the leadership is willing to listen to the leity. Althoug he was archbishop of Oregon, Abune yohanes lived in Seattle for the duration of his papacy. So if the synod decides to dispatch him to Texsas be it…. And we are VERY HAPPY about his moving out of Oregon….mat the same time we feel very sorry to the texan Ethiopians in Dallas area. On the final note if the exiled synod want to be serious about what they talk, my advice is for you to start looking inside… And inside you. Look what happened to churches in Seattle, Portland, and Vancouver Canada. These churches were peaceful and prosperous under Abune Zena Markos. After the passage of Abune Zena Markos, the so called like diyakon Tadesse with the help he get from Abune Lukas and Abune Yohannes is causing a misery to Ethiopian church members in the region. All Seattle portland and Vancouver churches are going through court proceedings. It is a very sad state of our community. Tadesse is DESTROYING the church and the “good” name of the exiled synod. Please listen to all of us… although we were not in Gondar, we are orthodox Christians too.

 2. to the habesha editor-
  Yihe zegeba layi “amarenja tenagari” eyalk emitashofew lemin dinew? difen hagerituwa amarenja tenagari yemolabat ayedelechem weyi? sima amarejachenen eyetetkemk atisdeben-ye amhara bihereseb layi yemidersew engilit bilek tsaf-alya antem ke dekalochu andu honek be ethiopia sime Amharawin litgalib yemitfelig agasses nehe!

Comments are closed.

berhan hailu
Previous Story

ቀጣዩ ታሳሪ ወይም ፈርጣጭ የፍትህ ሚ/ሩ ብርሃን ኃይሉ?

3862
Next Story

የኢትዮጵያውያን ሰሜን አሜሪካ ፌዴሬሽን አመራሮች በቬጋስ ተጫዋቾች ሊከሰሱ ነው

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop