ሥርዓቱ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱትን ስኳር በመከልከል ማስፈራራት ጀምሯል

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የቦቀል ቀበሌ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ስልልወሰዳችሁ ስኳር አይሰጣችሁም መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በአካባቢው ስኳርን ጨምሮ ሌሎች አቅርቦቶች በስፋት እንደሚጠፉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ዛሬ ጠዋት የቀበሌ ካድሬዎች በድምጽ ማጉያ ‹‹ዛሬ ስኳር ስለመጣ ቀበሌ ድረስ መጥታችሁ እንድትወስዱ፡፡ የመጣው ስኳር ውስን በመሆኑ ሊያልቅ ስለሚችል ዛሬውኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ ከዛሬ ውጭ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡›› እያሉ ሲለፉ እንዳረፈዱ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም መጥቷል የተባለው ስኳር ለማግኘት ወደ ቀበሌው ያመሩት ነዋሪዎቹ ስኳሩን ለመውሰድ ሲጠይቁ ‹‹የምርጫ ካርድ ወስዳችኋል?›› የሚል ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ግልጸዋል፡፡ የምርጫ ካርድ የሚያሳዩ ነዋሪዎች ስኳሩ ሲሰጣቸው፤ ያላወጡት በአስቸኳይ ምርጫ ካርድ አውጥተው እንዲመለሱና ስኳር እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡ በአንጻሩ ስኳር ለመውሰድ የምርጫ ካርድ ማውጣት የለብንም ያሉት ነዋሪዎች ስኳር እንደማያገኙ የተነገራቸው ሲሆን ‹‹እንደዜና የምርጫ ካርድ ወሰድንም አልወሰድንም ስኳር የማግኘት መብት አለን›› ያሉ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበው እንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በጠዋቱ የቀበሌ ነዋሪዎች ያሰሙት የነበረውን ለፈፋ ሰምቶ ወደ ቀበሌ ያመራ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ መምህር የምርጫ ካርድ ካላመጣ ስኳር እንደማይሰጠው ተነግሮት መመለሱን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ መምህሩ ‹‹የምርጫ ካድር የመውሰድና ያለመውሰድ መብት አለኝ፡፡ የማምንበት ፓርቲ ሲኖር የምርጫ ካርድ እወስዳለሁ፡፡ ካልሆነ ግን አልወስድም፡፡ ብወስድም ስኳር ለማግኘት ብዬ አይደለም፡፡ እንደማንኛውም ዜጋ ስኳር የማግኘት መብት አለኝ፡፡›› በሚል የቀበሌ ሰራተኞቹን ለማስረዳት ቢሞክርም ‹‹እኛ ስኳር ስጡ የተባልነው ካርድ ለወሰደ ብቻ ነው፡፡ ካርድ ካልወሰድክ አይሰጥህም›› ተብሎ እንደተመለሰ ገልጾልናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‘’እኛ በወንጀላችን ከምንጠየቅ ትግራይ ብትገነጠል ይሻላል’’ የህወሐቶች መፈክር

2 Comments

  1. የትግሬ ወያኔ አንዱ መገለጫዉ አስገድዶ ከሀገር ማባረር አስገድዶ ማስለፍለፍ አስገድዶ ከመሬት ማፈናቀል አስገድዶ ስብሰባ መጥራት አስገድዶ መዝረፍ አስገድዶ መድፈር አቤት ! ጣጣዉ አበዛዝ ይሀዉ እንግዲህ ቀጠለ አስገድዶ ምርጫ ካርድ ዉሰዱ አስገድዶ መብትሕን መከልከል ዉይ ! የዚህ ምድር ቆይታ በላይህ ልሰልጥን የሚል የትግሬ ነገድ አቤት ! በላያቸዉ ያለ የዛር መንፈስ ታዲያ ምን ያረጋል አኪራዉ የተመታ ቀን.. ወይ… ያኔ.. የት ይገቡ ይሆን.. አዎይ.. አዎይ…. እችክ.. እችክ…. ቲድ.. ዘራፍ… ዘራፍ……!!!

Comments are closed.

Share