የ13 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የመኪና አደጋ የሹፌሩ መሞት ማጣራቱን ያጓትተዋል ተባለ

በትናንትናው እለት ወደ ደብረማርቆስ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልጥቦ ለ13 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሲሆን አደጋውን ለማጣራት ፖሊስ እየሠራ ቢሆንም የሹፌሩ ሕይወት ማለፍ ማጣራቱን ውስብሰብ እንደሚያደርገው የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

ትናንት ከጠዋቱ 7 ሰዓት አካባቢ ወደ ደብረማርቆስ የሚጓዘው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የተገለበጠው በኦሮሚያ ክልል ወረ ጃርሶ ወረዳ ነው። 60 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረው ይኸው አውቶቡስ በምን ምክንያት እንደተገለበጠ ባይታወቅም አንዳንድ ታዛቢዎች ግን በኢትዮጵያ የሚደርሱት እንዲህ ያሉት አደጋዎች ከቸልተኛ ሾፌሮች በመነጨ ነው ይላሉ።

እንደነዚህ ታዛቢዎች ገለጻ መጠጥን፣ ጫትን እና አደንዛዥ እጾችን ተጠቅሞ መኪና የሚነዱ ሰዎችን መንግስት ተከታትሎ ስለማይቀጣ ሾፌሮች በግድሌሽነት ረዥም መንገድ ሲነዱ አደንዛዥ እጾችን እንደሚጠቀሙ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ሌላው ለመኪና አደጋ የሚያጋልጠው የመንገድ ጥራት ማነስ ሲሆን በተለይም የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች የአገልግሎት ዘመናቸው ስለማይታወቅ አደጋ እንደሚያደርሱ ተገልጿል። በሰለጠነው አለም ለሕዝብ ማመላለሻነት የሚውሉ መኪኖች የተመረተበት ዓ.ም በገደብ የሚቀመጥ ሲሆን ገደብ ከተቀመጠለት ዓ.ም በፊት የተመረተ መኪና ሕዝብ እንዲጭን አይፈቀድም።

ወደ ደብረማርቆስ 60 ሰዎችን ጭኖ የተጓዘው አውቶቡስ የተገለበጠበት ሥፍራ ከዚህ ቀደም በርካታ አደጋዎች የደረሱበት መሆኑም ጨምሮ የደረሰን ዜና ያስረዳል።

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ታሰሩ

1 Comment

Comments are closed.

Share