የሕወሓት ጄኔራሎች ሲታመሱ ዋሉ፤ ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል

ምንሊክ ሳልሳዊ እንደዘገበው፦

በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲሶች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።

ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።
ፎቶ ፋይል
በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ የፊታችን እሁድ በአ.አ. ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቃታል

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።

3 Comments

  1. ጊዜው ቅርብ ነው። ወያኔ እየተፍረከረከ ነው። ጎሳን ሃይማኖትን ሳይለይ ለአንዲት ሃገር የተደራጅና የታጠቀ የተቃዋሚ ሃይል ቢኖር ኑሮ ሰው ሃገር ቤት ይቀራል ብየ አልገምትም። ሰው ወያኔን አክ እንትፍ ካላቸው ውሎ አድሮአል። መታሰር፤ መገደል፤ ከሥራ መባረር፤ በዘር በጎሳ ሳቢያ ከሃገር ውጡ መባል የወያኔ የደራ ገቢያ ነው። ጉረኞች ሲወድቁ አይታያቸውም። መቃብር ላይ ቆመው የዘላለም ሰዎች ነን ይሉናል።
    አሁን በሃገሪቱ መሪ የለም። ጠበንጃ ያነገተ ሰው እንዳሻው የሚያግትበት፡ ፍትህ ርትዕ የጎደለባት ሃገር ናት። ሌባው እየሰረቀ ሌላውን ሌባ ነህ ብሎ ለእስር የሚዳርግበት ምድር ናት። የወያኔ ባለስልጣኖች ከእኛ በላይ ላሳር ነው የሚሉን። ዋ የሮም አወዳደቅ ሲወድቁ ታየኝ። ያኔ የት ነው የሚገቡት? ከወያኔ ሴራ አንድ ላጫውታቹሁ። አንድ ታታሪ ሰው ሃገር ቤት ከ 20 አመት ልፋት በህዋላ በዙ እንግዶች የሚያስተናግድ ሆቴልና ምግብ ቤት ይከፍታል። ሰው በጣም ሰለወደደው ስራውና ገቢው የተሳካለት ሆነ። አንድ ቀን ሁለት የወያኔ ኦዲተርስ ይመጡና ግብር አልከፈልክም ይሉታል። እርሱም የከፈለበትን ደረሰኝ ያሳያቸዋል። ተንኮልን የተሞሉት ካድሬዎችም ለአመታት የከፈልከው በትክክል ያልታሰበ ስለሆነ የሚቀርብህ 2.5 ሚሊዬን ብር ክፈል ይሉታል። እርሱም ይህ ሊሆን አይገባም ስህተት ነው ስሌታቹ ሲላቸው ካልከፈለ ቦታው ተሽጦ የመንግስት እዳ ይከፈላል ይሉታል። ነገር ለማሳጠር ቦታው ይሸጣል። የተሽጠው 3.0 ሚሊዬን ብር ነበር። የተሸጠው ለወያኔ ሰው ነው። ባለሃብቱ በዚህ ተናዶ ሃገር ለቆ አሁን አንድ ሌላ ሃገር ታክሲ ነጂ ሆኖ ይኖራል። ወያኔ ግፈኛ ነው ስንል መረጃ ይዘን ነው። ያ ሆቴልና ምግብ ቤት በወያኔው አሽከርና አባል አሁን በስራ ላይ ይገኛል። እንዲህ ባለ መንገድ ነው ሰውን የሚያሰቃዩት። ያደለው ነው ከሞትና ከሥራት ተርፎ እፎይ ለማለት የበቃው። ስንቶች ተረሽነዋል። አ. አ በ አራተኛ ጦር መምሪያ አካባቢ ቁፋሮ ሲደረግ የተገኘው አስከሬን እነ ማን እንደሆኑ ታውቃላቹ? እውነተኛ ሃገር ወዳድ ነገ ዛሬ ሳይል ወያኔ ለመታገል መነሳት አለበት። እሳትን ማጥፋት የሚቻለው በእሳት ብቻ ነው።

  2. GOOD NEWS ,BUT TRY TO FIND THE NAME OF ALL …..THAT IS IMPORTANT BECAOUSE IF THEY COME TO ANOTHER COUNTRY ..CAN HELP TO IDRENTIUFY THEM

Comments are closed.

Share