June 10, 2014
2 mins read

የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት የፊታችን እሁድ ጁን 15 በሚኒሶታ ይከበራል

(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ እና ዘ-ሐበሻ ድረገድ የፊታችን እሁድ በሚኒሶታ 6ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል። በዚህ የ6ኛ ዓመት በዓል ላይ በሚኒሶታ በመልካም ሥራቸው ከሚታወቁ የማህበረሰቡ አባላት ውስጥ አንዱ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በሚል እንደሚሸለም የዝግጅቱ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል።

ታዋቂው አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ በዚህ በዓል ላይ በክብር እንግድነት እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ለዘ-ሐበሻ ድረገጽና ጋዜጣ ማጠናከሪያ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት እንደሚኖርም ታውቋል።

በሚኒሶታ ሴንትፖል ከተማ ኬሊ ኢን በተባለው ሆቴል ከቀኑ 3 ሰዓት ጀምሮ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከታማኝ በየነ በተጨማሪ በሚኒሶታ የሚገኙ ምሁራን የሚሳተፉባቸው ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውም ታውቋል።BEST WESTERN PLUS Kelly Inn!
161 Saint Anthony Avenue
Saint Paul, Minnesota, 55103 ዘ-ሐበሻ በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ የተመሰረተች ነፃ የመገናኛ ብዙሃን እንደመሆኗ መጠን በዓሉን በተመሰረተችበት ከተማ ለማክበር መመረጡን ያስታወቁት አስተባባሪዎቹ ወደፊት በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት እቅድ እንዳለ አስታውቀዋል።

በዚህ በዓል ላይ በሌላ ስቴት የሚኖሩና ሊገኙ የማይችሉ ድጋፋቸውን በፔይፓል በኩል መክፈል የሚችሉ ሲሆን በቼክ ለመላክም አድራሻው እንደሚከተለው ቀርቧል።

ዝግጅቱን ለማገዝና እንዴት ዘ-ሐበሻን ማገዝ እንደምትችሉ ለመጠየቅ የበዓሉን ዋና አስተባባሪ አቶ አልዩ ተበጀን በስልክ ቁጥር 612-986-0557  ያነጋግሩ።

ለዘ-ሐበሻ በቼክ እገዛችሁን ለመላክ
Zehabesha LCC
6938 Portland Ave S
Richfiled
MN 55423

መጠቀም ትችላላችሁ።

ዘ-ሐበሻን በፔይፓል በኩል ማገዝ ለምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ ላይ ይክፈሉ

እውነት ያሸንፋል!

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop