[ስሞታ ለኢትዮጵያ ህዝብ] “በኤችአይቪ ቫይረስ ተይዤም መንግስት መጠለያዬን ነጥቆ ለባለሃብት ሰጠብኝ” – ወ/ሮ እታገኝ መኮንን

እኔ ወ/ሮ እታገኝ መኮንን ካሣ አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 760/ሀ ነዋሪ ነኝ፡፡ በአሁኑ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ከላይ ቁጥሩ በተገለፀበት ቤት ከ40 ዓመት በላይ ተከራይቼ ስኖር በ1990 ዓ.ም በኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ መያዜን አወኩ፡፡ ቤቴንም ሆነ ልጆቼን እንዲጠብቅልኝና እንዲረዳኝ በማለት ከ1994-1997 ዓ.ም ድረስ በውክልና ሰጥቸው የነበረ ሲሆን ከ97 በኋላ ግን ውክልናውን ትቶ የራሱን ቤት ሰርቶ ሄዷል፡፡ ቤቱ እስከታሸገበት ጥር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ድረስ ለአቶ ደረጄ ጎዳና ከመንግስት ተከራይ በማስመሰል በቤት ቁጥር 760/ሐ በአቶ ደረጄ ስም የአንድ አመት (በ1998 ዓ.ም) የቤት ኪራይ በስማቸው ቀበሌ ሂዶ ከፍሏል በማለት እኔ ደካማና በሽተኛዋን የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው በማለት ቤቴን ጥር 12 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመድኃኒቴ እና በንብረቴ ላይ በማሸግ በእኔም ሆነ ቤተሰቦቼን ከፍተኛ ችግር ደርሶብናል፡፡

ሆኖም መጋቢት 24 ቀን 2006 ዓ.ም እኛን በፖሊስና በመሣሪያ ኃይል ከግቢ ውስጥ አስወጥተው ንብረቴን በሌለሁበት አውጥተውብኝ እኔ ስምንት ቤተሰቤን ይዤ ዕቃ ቤት እንድኖርና ግማሹ ንብረቴን ውጭ ተጥሎ ለዝናብምና ለፀኃይ እንዲጋለጥ በማድረግ ከፍተኛ ውድመት እንዲደርስብኝ አድርገዋል፡፡በየደረጃው ላሉት የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ አቤት ብልም ቤቱን ለፈለጉት ሠው ለመስጠት ሲሉ ያላደረኩትን አድራጎት እያቀረቡ ጥፋተኛ ነሽ በማለት ለረዥም ወራት እያንከራተቱኝ መሄጃው ጠፍቶብኝ እገኛለሁ፡፡

ሁከት ስለፈጠሩብኝ ይወግድልኝ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ባቀርብም የወረዳ 09 ቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት የሀሰት ማስረጃ እያቀረቡ ሁከት አልፈጠረም በማለት ውሳኔ ተሰጠብኝ፡፡ በበኩሌ በ2005 ዓ.ም ይግባኝ ብልም ወረዳውን መጥራት ሳያስፈልገኝ የተሠጠው ውሳኔ ትክክል መሆኑን አረጋግጭአለሁ፤ መልስ ሰጪውን መጥራት አያስፈልግም ብሎ መዝገቡን ዘግቶብኛል፡፡ እንዲሁም ሠው ሁልጊዜ ከማስችገር በማለት ትንሽዬ የሸራ መጠለያ አድርጌ ከሰል ቸርችሬ የማድርባትን መጠለያ የደረጄ ነው በማለት ግቢው ውስጥ ሁለት ክፍል አድርገው ቀምተው ሰኔ 16/2004 ዓ.ም ለአስቴር መለስና ለጌታቸው መለስ የልማት ተነሺ ናቸው በማለት ሰጥተውብኛል፡፡ አሁን ደግሞ የምኖርበትን ከመንግስት በየአመቱ የምዋዋልበትን ቤት ለኃይልና ለውኃ ልማት በፃፉት ደብዳቤ ቤቴ መሆኑን በማመልከቻ ላይ ገልጸውልኛል፡፡ እኔ እታገኝ መኮንን በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 09 መንግስት ቤት ቁጥር 760 ነዋሪ መሆኔን በ26 ዝውውር 2006 እስከ ዛሬ እኖርበት የነበረውን መኖሪያ ቤት ለልማት ተነሺዎች የተሰጠ መሆኑን በደብዳቤያቸው አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ ለተከሰተው ረሃብ ግሎባል አሊያንስ የድጋፍ ጥሪ አደረገ

እኔ የ63 አመት አዛውንት የሙት ልጆች ይዤ ብርድና ፀሀይ እየተፈራረቀብኝ እገኛለሁ፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ እላለሁ!

በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ።

3 Comments

  1. “በዚሁ የየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ ፰ ውስጥ ሁለት ተያያዥ ቤቶች አሉ። ሁለቱ ተከራዮች ቢያንስ ቤቱን ከመንግስት ተከራይተው የኖሩበት ከ፶ዓመት በላይ ነው። አንደኛዋ ተከራይ ፫ የደረሱ ልማታዊ ልጆችና አንድ በራሱ የተመካ መሀንዲስ አማች አላቸው። ሁለተኛዋ ተከራይ ፮ ልጆች ሲኖራቸው ፫ከዚህ ዓለም አልፈዋል።የሁለቱም ቀደምት ኖሮ ዝቅተኛና ተመሳሳይ ነበር። ሁለቱም ተከራዮች የመግቢያ ጠፈጠፍ ሲያስቸግራቸው በአንድ ቆርቆሮ ዕርዝምት በረንዳ ዘርግተው ለመሸፈን ሲፈልጉ ልጆችና አማች ያላቸው ፍቀድ አግኝተው መሠረቱ በኒሚንቶ ቋሚው በብረት አራት ቆርቆሮ ድርድረው ሠርተዋል። ሁለተኛዋ ተከራይ ግን ቆርቆሮውን አቁመው በረንዳውን በእንጨት ቀስት እነጂ በብረት ለመሥራት አልተፈቀደላቸውም።(ዳግማዊ ደርግ!)…. በዚያን ዘመን ሁለት የቀበሌው ተመራጮች ለ፲፯ዓመት የቤት ኪራይ ሳይክፍሉ በመጣው ምርጫ ሁሉ የማሟያ ምርጫ እየተባለ ሲጠቀሙ ኖረዋል ዛሬ በኢህአዴግ ያልከፈሉበትን የኪራይ ቤታቸውን ባላቤት ሆነው ሸጠው በጥሩ አሸናኘት ተደርጎላቸው መላ ቤተሰባቸውን ይዘው በአሜሪካ ይኖራሉ። ይህ ነበር የኖርንበት እኝህም እናት የሚኖሩበት አለም!!

    **በውጭ ሀገር ተቀምጣችሁም እያማሰላችሁም ያሳረራችሁን..ሀገራችሁ ገብታችሁ ፵/፷ የምታበስሉ…ፖለቲካ በድረ ገፅ የምትቀቅሉም ይሁን..በፓልቶክ የምትቆሉ…ይህ የተዘበራረቀ በቀለም ያበደ ባንዲራ ይዛችሁ የሰው ሀገር የምትቀውጡም…የፀሐዩ መንግስት እያላችሁ እንጀራና ቅመማቅመም ከሕዝብ ጉሮሮ ነጥቃችሁ በመሸጥ የከበራችሁ…ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሃይማኖት ቋንቋ መልካም ሥነምግባርን ጥለው የባዕድ ይዘው ገደል እንዲገቡ ጥረት የምታደርጉ እራስ-ወዳዶችም ብትሆኑ…ለግል ጥቅም አድርባይነት..አውርቶ-አደርና ሠርቆ-አደር መሆን ዘለዓለማዊ ለሚመስላችሁ…በቀን አስር ግዜ እየበላችሁ ለወገኖቻችሁና ለፆም-አዳሪው ወጣት ትውልድ የማቀጣጠያውና መቃጠያው ነዳጅ የምታቀብሉ ዲያስፐርስ…ዘረኝነትን ሙስናን ጎጠኝነትን ዘርታችሁ የድሃ ልጅ በጥይት ለምታስቀጥፉ ሁሉ…የምታመጡት ለውጥ ከነበረው የተሻለ እንጂ ጭራሽ በመከፋፈልና በጎሪጥ በመተያየት ጥቅማጥቅመኞት(ለልማት ተነሳሺ!) ካድሬ… ታማኝ ምሁራን…አክቲቪስት አርቲስት ኢንቨስትር…ተብለው ሥርዓቱን እንዳለ ያለ ‘ተፎካካሪ ተወዳዳሪ አማራጭ’ ፓርቲና የነፃ ሚዲያ እራሱ አውርቶ.. እራሱን አድንቆና አጨብጭቦ እንዲቀጥል ለሚያደርጉ ምቹ ሁኔታን መፍጠራችሁ እነደሆነ ልትገነዘቡ ይገባል። ዝምታም ትብብር ነው!።ከበላተኛውም ጎን ሆኖ በሌላ አጀንዳ ንጹሕ ሕዝብን ማተራመስም ሥርዓቱን መተባባር ነው!።

    **አቶ መለስ ” እኛ ለሽማግሌውና ለአዛውንቱ ግድ የለንም እኛ የምንፈልገው አዲሱ ትውልድ እንዲከተለን ብቻ ነው” ብለው ነበር…አዎን! በዚህ ዘመን በአራቱም አቅጣጫ(ማዕዘን) የሚሰራው ይህ ነው። ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያ ታሪክ የላቸውም የሚያስተምሩት ብሄርና የግለሰቦችን ራዕይ ነው.. ሽማግሌና አሮጊት የድሮ ሥራዓት ናፋቂ ይባላሉ ግን ያለ እነኝህ ዜጎች አስተዋጽዎ ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር።፡አዲሱ ትውልድ እነደፈለጉት የሚነዱት የቁም ከብት ሆኖ ተከልሎና ተከልክሎ ጸጥ ብሎ ይገዛል!! ዕለታዊ ጉርሱን በቀን አበልም ይሁን ጥቅማጥቅም ካገኘ እናቱን ለገንዘብ ያስማማል… እናት በሎ ሀገር አደለምን!?ቻይና ሕንድ ዓረብ ቱርክ ሲከራየውና ሲገዛው መች እንቢኝ አለ!? ዙሪያውን ይጨፍር የለምን! ታዲያ እርስ በእርሱ ሲሆን ሜንጫ ስሎ! ሽመል ቆርጦ እሳት ጎርሶ.. እሳት ልሶ አቃጥሎ በጥይት ይቃጠል ለምን!? አልቅስ ያለው ዓይን ጭስን አጥብቆ ጠየቀ!

    ***አቶ ኀይለመለስ “ኢትዮጵያዊነት ደምቋል አሉ” በሸውራራ ዓይን መነፅር ተደርጎ ተጥበርብሮባቸው ካልሆነ ወይንም ይህ ዙሪያውን የሚጠዛጠዘው ሕዝብ ኢትዮጵያዊ አደለም ካላሉ ወይንም እራሳቸው እንዲበጣበጥ ከላዘዙና በእጅ አዙር እንቨስት ካላደረጉ በቀር የደመቀች ኢትዮጵያ የት ነሽ? ወይ ተበድሮና ለምኖ መድመቅ!? ፻፷፮ ኪሎ ሜትር ወልቂጤ ከተማ እሳት አዳጋ መኪና የሌላት የ፷፭ዓመት አዛውንት ፰ቤተሰብ ይዘው ቤታቸው ተነጥቆ ዜግነታቸው ተረግጦ ይህ ዕድገት…ሠርቶ በማፍረስ የት ይደርሳል! እነኛ በበረሃ የአሞራ እራት ሆነው የቀሩ ታጋዮች ጭቆናን አስወግደው ብላ ተባላን መርሆአችን፣ አንድነታችን እፍረታችን!ብሔር!፩ ብሔረሰብና፪ ሕዝቦች ፫ (የአፓርታይድ ከተማ) መስርተው ልዩነታችን ውበታችን! ብለውን ለመናገር.. ለመንቀሳቀስ.. ለመሰብሰብ..ለመዘዋወር..ለመሰለፍና ሞተንም ለመቀበር አሳውቀን አስፈቅድንና ለምነን በፍርሃት እንድንሸበብ አድርገው ከልለውና አስከልክለው ለእራሳቸው ለቤተሰባቸው ለወገኖቻቸው ለእኛና ለኢትዮጵያ ሳይሆኑ ገድለውን ለምን አረፉ!!!?ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን!

  2. ኣየሽ ወሬ ቤት ኣይሆንም ብዛ ላይ በሽታ ብለንብረት ኣይደርግም ንብረት የ ባለንብረቱ ነው ብዝ ላይ ቤቱን ለሰው ስጥተሽ (ኣክራይተሽ) የት ነበርሽ ለብነት ኣልሳካ ሲል ኡ ኡ ሌባ ይሄም ሲያንስሽ ነው

  3. መጀምርያ ነገር በሽታ ይንብሬት ባለቤት ኣያደርግም ንብረት የባለ ንብረቱ ነው ሌላው በቱን ኣከራይተሽ ይት ትኖሪ ነበር የራስን ቤት ሰርቶ ሄድ ነው ያልሽው ቤቱ ታሽግ ነብር ኣይድል ኣየሽ ሌብነት ኣልሳካ ሲል አኡ ኣኡ
    ቀጣፊ

Comments are closed.

Share