የኢትዮጵያ አየር ኃይል ካፒቴን አስመራ ላይ ተቃዋሚዎችን ተቀላቀለ፤ * መንግስት አላስተባበለም

(ሚግ 23 – ፎቶ ከፋይል)
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባላት ገዢውን የኢሕአዴግን መንግስት በመክዳት ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚያደርጉትን ስደት ቀጥለዋል። የኤርትራ ሚዲያዎች የመንግስታቸውን ቃል አቀባይ በመጥቀስ እንዳስነበቡት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሚግ 23 አብራሪ የሆነው ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስ ስርዓቱን ጥሎ አስመራ ገብቷል።

እንደኤርትራ ሚዲያዎች ገለጻ ከሆነ ካፒቴን ዳንኤል የሺዋስ ኤርትራ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተቀላቅለዋል። ሚዲያዎቹ በምን መልኩ ወደ አስመራ እንደገባ የገለጹት ነገር ባይኖርም ማዕዶት የተባለው የኤርትራውያን የመረጃ መረብ የኤርትራን መንግስት ቃል አቀባይ በመጥቀስ ካፒቴኑ ለኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት እጁን የሰጠው ከነ አውሮፕላኑ ነው ሲል ዘግቧል።

የኢሕአዴግ መንግስት በመከላከያ ውስጥ ያለውን የዘር አድልዎና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በቸልታ መመልከት እያንገፈገፋቸው የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት እየሸሹ ወደ ኤርትራ በመግባት ተቃዋሚዎችን እንደሚቀላቀሉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት ካፒቴን ዳንኤል የሽዋስን መክዳት አስመልክቶ ምንም ያወጣው መግለጫ የለም። ዘ-ሐበሻ ከመንግስት አካባቢ ዜናውን ለማረጋገጥ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ልዑክ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ማድረጉ ታውቋል።

1 Comment

  1. Deg arege tigray behon aykedam. Man keterut alachu he has to be pure tigrian.dont trust the amaras. Clean them all before they heart our front.

Comments are closed.

Share