[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] – አንድነት ይመጣል፡ እውነቱም ይገለጣል (ከዲ/ኤፍሬም ስለሺ)

ከዲ/ኤፍሬም ስለሺ

መጀመሪያ ከታናናሾቹ ጀመሩ፡ “ልጅ ያቦካው፡ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጀርባ ወያኔ አለ እያሉ የቤተክርስቲያንን አንድነትን የጠየቁትን ወጣቶችን ሁሉ ተሳደቡ፡ ሲፈልጉ “ልጅ ያቦካው” ሲፈልጉ ከፋፋይ፡ አክራሪ ያደርጓቸዋል፡ ሲፈልጉ ደግሞ ያልተማሩ ሰሜታውያን ያደርጓቸዋል። ዝም ሲሏቸው እንደ ተሰጣቸው ኃላፊነት የቤተክርስቲያንን አንድነት ሊያስተምሩ በተነሱ ካህናት ላይ ድግሞ ዘመቱ፡ ግማሹን ሲያሳግዱ ግማሹን በስልክ የሞት ዛቻ ሲሰጡ ግማሹን “የ ፖሎቲካ ትምህርት” ነው ሲሉ፡ ግማሹን መስቀሉ የግል ይመስል “የእርሶን መስቀል አልሳለምም” ሲሉ ሰነበቱ። በአደባባይ በጀብድ “ካህናቱ ጠግበዋል እነሱን አባረን የተራቡ ካህናት እናመጣልን” እያሉ ፎከሩ። በየ ሚዲያው የቤተክርስቲአንን ካህናትና አንድነትን የናፈቀውን ምዕመን ተሳደቡ። የቤተክርስቲያንን ልዕልናና ክብር ሳይጠብቁ ውሸቱን ከሃይማኖት እየቀላቀሉ፡ ወይም ደግሞ ግማሽ እውነት ይዘው ከፖለቲካው እሳት ጋር እያጋጩ መንጋውን አስጨነቁ። ይባስ ብለው እራሳቸውን “የአባቶች አስታሪቂዎች እኛ ገልለተኞች ነን” ካሉ በኋላ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አራሱን ቤዛ አድርጎ በሰጠበት ዕለተ መድኃኔዓለም፡ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሊያስተምሩ ሊባርኩ ቢመጡ እግዚአብሔርን ሳይፈሩ ሰውንም ሳያፍሩ በቅድስናው ስፍራ በጫማቸው በመግባት የቀበሌ ሜጋ ፎን ይዘው ጮሁ ተሳደቡ፡ የሌባ ጣታቸውን ቀስረው ሊቀ ጳጳሱን “ሌባ ሌባ” አሉት። ጌታ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሏልና፡ ብጹዓን አባቶች ዲያቆኑ አድንኑ ካለ በኋላ የሰደቧቸውን ወደ ታች እየተመለከቱ በትህትና “አቤቱ ሕዝበህን አድን ርስትህንም ባርክ ጠብቃቸው እስከዘላለምም ድረስ ከፍ ከፍ አድርጋቸው” ብለው መረቁው ጸሎት አሳረጉ። ስራቸውንም እንደ ጀብድ “ኃይ ፋይቭ” እየተሰጣጡ ወጡ፡ እንደ መልካም ዜናም ቪዲዮውን አሰራጩት። ቅዱስ ሲኖዶስ አስተምሩ ብሎ በላካቸው መሠረት፡ ከ ቤተክርስቲያን ቀኖናና ከ ሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ምክርና ተግሣጽ ርቆ የመኖር “የገለልተኝነት” አቋም ቀርቶ ጌታ በደሙ በዋጃት፡ ሐዋርያት ደግሞ በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እንጠቃለል ዘንድ አስተምረው እንደሄዱ፤ በጠበቃቸው በኵል ሊቃነ ጳጳሳት ቤተክርስቲያን እንዳይመጡ አሳገዱ። በቅዳሴ መካከል ጣልቃ በመግባት ድሮ ድሮ በሂደት ይስተካከላል “ሰም መጥራት ብቻ ነው የቀረው” በሚል ሽፋን ይስተካከላል ተብሎ በትዕግሥት የቆየውን ሥርዓት ፤ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ከፍርድ ቤት በተጻፈ እገዳ ካህናቱ በቅዳሴው ሥርዓት ላይ የቅዱስ ፓትርያርኩ ስም እንዳይጠራ አሳገዱ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕገ-መንግስቱ ምርጫ እንዲራዘም ስለማይፈቅድ መፍትሄው ብጥብጥ ነው -- ሰርፀ ደስታ

በዚህ ጊዜ እለቱ አርብ ነውና ጭንቀት መጣ፡ ካህናቱ የሊቀ ጳጳሱን ትዕዛዝና ሕገ ቤተክርስቲያን ይከተሉ ወይስ ከፍርድ ቤት የመጣውን እገዳ? ይህ ጊዜ አጣብቂኝ ነበር። የጠበበችው በርና ሰፊዋ በር እንደ አማራጭ መጡ፡ ይህ ጊዜ ዮሐንስ ከ ይሁዳ ተለየ፡ ይህ ጊዜ አቋም ተለየ ፡ማን ከማን ጋር እንደሚቆም ተለየ። ቤተክርስቲያንን እንደ ቤተክርስቲያንነቷ ያከበሯት ካህናት ንብረቴ ትዳሬ ገንዘቤ ሳይሉ በጠበበችው በር ገቡ። የሰው ፊት እየገረፋቸው እውነተን መሰከሩ፡ ያስተማሩትን በተግባር አሳዩ። ከ ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት የተለዩት ፬ቱ ካህናት ግን ሥልጣን፡ ገንዘብ፡ ዝናን ያተረፉ መስሏቸው የቤተክርስቲያንም አንድነት በግልጽ ተቃወሙ። ይሁዳ ኑሮው አገልግሎቱና አዳሩ ከሐዋርያት ጋር ነበር፡ አርብ ቀን ስትመጣ ግን ከ ቀያፋና ሐና ጋር ቆመ፡ እነዚህም ፬ ካህናት ውሏቸው አገልግሎታቸው ልሳናቸው ከ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት ጋር ነበር፡ ዛሬ ግን ዕለቱ አርብ ነውና “ጳጳስ የለም” “ጳጳሱ ሌባ ነው” ጳጳሱን “አንተ” ብለው ከተሳደቡት ጋር አብረው ሆነው የገዛ ወንድሞቻቸውን ካህናት “ስቅሎ ስቅሎ” አሉ። እነዚሁ አካላት ትናንተና ገንዘባቸው እንዲቆረጥ፡ ክበራቸው እንዲገፈፍ፡ በክህነታቸው እንዳይከበሩ አንዴ “መረጃ አለን” አንዴ “አባሯቸው” አንዴ “እሱ ሌባ ነው” የሚሏቸው አካላት ነበሩ። ዛሬ ግን ቤተክርስቲያንን ይከሱ ዘንድ አብረው ተማከሩ። ጌታ ግን ከባቴ አበሳ፡ ኃዳጌ በቀል (ኃጢያት የሚሸፍን በቀል የሌለበት) እንደሆነው ሁሉ አብረዋቸው ሌሊት እና ቀን የሚያገለግሉት( በተለይ ቋሚ ካህናቱ) ለአመታት ሁሉን ሸፈኑት ሁሉን አለፉት ሁሉንም ቻሉት።
ከ ፲፬ቱ ማኅበረ ካህናት ጋር በቤተክርስቲያን አንድነት አልተባበርም ያሉቱ ፬ቱ ካህናት ከሊቀ ጳጳሱ ትዕዛዝ ውጪ ሲውጡ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ።

ያ አልበቃ ብሎ “በቅደሴ ሥርዓት ውስጥ ያለው ቅዱስ ፓትርያርክን ስም እንደ መጽሐፉ መጸለይ “ትውፊት” ነው፡ ሊቃነ ጳጳሳት ባንዳዎች፡ ሃሰተኞች፡ ወያኔዎች ናቸው እያለ ሲናቀፍ ሲሳደብ ቆይቶ የፕሮቴስታንትና የኢሳትን መግለጫ እንደ ቤተክርስቲያን የመጨረሻ መረጃ ሲያቀርብ ኖሮ በአለፈው እሁድ በድምፅ ሬድዮ ወጥቶ ግዝቱ “ወፈ ግዝት ነው፡ እንዳውም ዛሬ ሊቀ ጳጳስ የሚባል የለም” ብሎ ካደ። ያ አልበቃ ብሎ ትናንት ሊባርኩን በመጡ ቁጥር “ወያኔ ናቸው፡ አንፈልጋቸውም፡ ምንም አይነት ድርጎ ልንሰጣቸው አይገባም” ሲሉ የቆዩ አካላት ዛሬ ደውለው ግማሽ ታሪክ በመንገርና እውነቱን በማጣመም እየተቀዱ እንደሆነና ለአለም ድረ ገጽ እንደሚበትኑት ሳይነጕራቸው “መርጌታውን ሊቀ ጳጳሱ አወገዙ ይባላል ምን ይመስሎታል” በለው ጠየቋቸው። አይደለም ከሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ቀርቶ ከመላው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እርሳቸውን ለማጣላት የራቸሳቸውን የግል አስተያየት ተጠቅመው አንድነትን የናፈቀውን የሕዝበ ክርስቲያኑን ሕልም ያጨለሙ መስሏቸው አዲስ ሰይፍ ይዘው ተነሱ። በነገራችን ላይ መሪጌታው አው አልተወገዙም! ሥልጣነ ክህነታቸው ግን ተይዟል” መወገዝ ሌላ ነገር ሥልጣነ ክህነት መያዝ ደግሞ ሌላ ነገር። አማረኛው ሁለቱን ነገሮች ለይቶ ስም ሰጥቷል፡ አንዱን ውግዘት” አንዱን ደግሞ “ሥልጣነ ክህነት መያዝ” ይባላል። አንድ ካህን ሥልጣነ ክህነቱ ተያዘ ማለት የክህነት ሥራን መስራት አይችልም እንጂ ተወግዟል አይባልም። With that said the English word “excommunication goes for both meaning. the word Excommunication can be used for both the word ውግዘት and ሥልጣነ ክህነት መያዝ In case of the Merigeta and three other priest’s excommunication that came from the Archbishop፣ is restriction from practicing the acts of priesthood. (ሥልጣነ ክህነት መያዝ) ። ስለዚሀ መርጌታው ሊቀ ጳጳሱን በመተላለፋቸው ሥልጣነ ክህነታቸው ቤተ መቅደስ ከመግባት፡ ታቦት ከመዳሰስ፡ ቀድሶ ከማቊረብ፡ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ እንጂ አልተወገዙም። ውጉዝ ከመአርዮስ አልተባሉም። ሥልጣነ ክህነታቸው ነው የተያዘው። ምዕመን የመሆን በቤተክርስቲያን መመላለስን አልተከለከሉም ያም ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ አሁንም ቢመለሱ እውነተኛይቷን ወንጌለ መንግሥት አብረው ከሌሎቹ ወንድሞቻቸው ጋር ቢያስተምሩ እናት ቤተክርስቲያን ሥልጣነ ክህነታቸውን እንደምትመልስ እጆችችዋን ዝርግታ እንደምትጠብቅ የሊቀ ጳጳሱ ደብዳቤ ይናገራል። (ስለ ግዝትና ሥልጣነ ክህነት መያዝ ለይተው ሊቃውነቱ እራሳቸው ስለሚያስተምሩን እኔ ወደዛ አልገም።) ግን አሁንም ቢሆነ ቅንጭብ እውቀት ይዞ በሬድዮ መቅረብ እራስን ያስገምታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እስቲ ተጠየቁ- ምንድን ነው ምትሹ ፤ - ይገረም አለሙ

መሪጌታ

መሪጌታ የተያዘው ሥልጣነ ክህነትዎ እንዲመለስ ባለፈው ብጹዕ አቡነ ዘካሪያስ ጋር ልክ እንደደወሉት፡ ለቅዱስ ሲኖዶስም አቤቱታ ማቅረብ ሲገባዎት የኢየሩሳሌም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታችን ብጹዕ አቡነ ዳንኤል ጋር ደውለው ስለ “ውግዘትዎት” ሲያስጠይቁ
፩- አንድ የሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያወገዘውን ካህን ወይም ሥልጣነ ክህነቱ የተያዘበትን ካህን ሌላ ማንም ሊቀ ጳጳስ እንደማያፈተው በቀሲስ ዶክተር መስፍን ጉዳይ ላይ ይናገሩና ያስተምሩ አልነበርም? (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፬ ቁ፷፩)
፪- አንደ የቅዱስ ሲኖዶስን አባል በማታለል፡ እውነቱን በማጣመም እናንተ ባቀረባችሁላቸው ክፉ ወሬ ተነስተው የራሳቸውን የግል አስተያየት ቢሰጡ ቀድታችሁ ለአለም ስታሰራጩ አይደለም ከሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዛካሪያስ ጋር ከመላው ቅዱስ ሲኖዶሰ ጋር እንደምታጣሏቸው ይህን አያውቁም? ነው ወይስ የዚህ አልበቃ ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስንም እንክፈለው?

እሺ እኛ “ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም” ወይም አክራሪዎች ስሜተኞች እንሁን። ለቤተክርስቲያን አንድነት ንብረቴ ገንዘቤ ሳይሉ የቆሙላት ካህናት ድግሞ “ወያኔ” አላችሁ፡ በየሚዲያውና አለማዊ ደረ ገጽ የቤተክርስቲያንን ልጆች አዋርዳችሁ፡ ሊቃነ ጳጳሳቱንም በቅድስናው ስፍራ ሰደባችሁ አሁን ታዲያ ሕግጋቷንና ቅዱሳት መጻሕፍቷን ለራሳችሁ እንዲመች ስታጣምሙት ዝም እንበላችሁ? (፩ ጴጥ ፪፡፲፩)

መሪጌታ ብዙ ሰው አለቀሰቦት ብዙ ሰው ቆሰሎቦት ብዙ ሰው ጠፋቦት፡

ግን እኮ አለ ቅዱስ ፖሊካርፐስ፡ ግረፉን፡ በመጋዝ ሰንጥቁን ለአናብሰት አሳልፋችሁ ስጡን በእሳት አቃጥሉን በሰይፍ ሰይፉን..ነገር ግን…እናንተ በገረፋችሁን በመጋዝ በሰነጠቃችሁን ለአናብስት አሳልፋችሁ በሰጣችሁን በእሳት ባቃጠላችሁን በሰይፍ በሰየፋችሁን ቁጥር እኛ እየበዛን እንሄዳለን፡ ለምን ብትሉ የቅዱሳን ደም ለቤተክርስቲያን ጌጧና ውበቷ ነው፤ የክርስቶስ ክብር መገለጫዋ ነው። (ቅዱስ ፖሊካርፐስ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀደመ ውን ፍቅርህን ትተሃልና የምነቅፍብህ ነገር አለኝ።

የሚደንቀው ነገር ግን ክብር ለመድኃኔዓለም በትግል ብዛት አትወሰንም ቅድስት ቤተክርስቲያን፡ አንድነት ይመጣል፡ እውነቱም ይገለጣል!

የቅዱሳን አምላክ ማስተዋሉን ትንሽ፡ እንዳው ትንሽ ብቻ!! ለሁላችንም ይስጠን።

14 Comments

  1. ዲያቆን ኤፍሬም፤ ተንኮልና ነገር እንደ አረቄ አናትህ ላይ ወጥተው ስላሰከሩህ፤ ውሸታም ደግሞ አስቀድሞ የተናገረውን ስለማያስታውስ እንጂ ባለፈው የበተንከው/የበተናችሁት ፍላየር ላይ “ከተወገዙ ካህናትና ዲያቆናት ጋር አብረን በቅዳሴ መሳተፍ መንፈሳዊ አግባብነት የሌለው መሆኑ የታወቀ ስለሆነ” ነበር ያልከው/ያላችሁት። ታዲያ ዛሬ ሳምንት ሳይሞላ “ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ” እንጂ አልተወገዙም አልከን፤ ወንዴሜ እባክህን አንደ አረብ ሬዲዬ ዝም ብለህ አትቀለቅል። ባልከው ላይ ፅና፣ ከሁኔታዎች ጋር እንደ እስስት አትቀያየር

    • Ze ethiopian lemhunu aneta eras tawekewalek yametawerawn. Dacon Epheram ewenat new yetaenageraw endat akerere ayedelem. aneth ers sekeram neh enge yatenagera lalegabawe hezeb maseradatu new. selezeh pls kachelek yehehen adebet weyem afeken lasehnetbet tetekemebet. balege deros kadeanet ayenet mine yetebekal ka zeneb mar ayetebekem.

  2. ZeEthiopia why you need to insult Deacon Ephrem, the paper that sent to those four X-kahinats from Abune Zekarias are posted in zehabesha, read it yourself, I am sure you don’t need an interpreter.

  3. Deacon ephrem, you became completely crazy, liar, dedeb, woyane, unmatured and anti- unity and anti-christian. You did a phone call to Abune Daniel and His holiness told you to shut your mouth up. Now you tried to preach separation and hate among christians. Please kneel down and pray to God, he will give you the answer. If you don’t you will…Because christians preach unity, peace, love and live in harmony.

  4. Daikon Eframe the little boy i don’t know why you are craying all about. I am very ashamed by your comment or Article. Are you trying to teach MEREGETA About GEZET what a shame? when i know you long time ago you where five years old. I remember you are siting under his feet and learn how to be Daikon. Please preach your followers TEHADESO, we don’t need in-experience Daikon. you need to learn more go back to Ethiopia to your master with your bottle. I don’t think you gonna learn from Aba hilemikel. Stop blaming our hero go with your leftist priest Cray for a piece of land. Grow-up. I am sure you did not write this maybe Abreham did it for you in your name. God Bless Gileltena Group. I pray for you my son, even if we aren not related.

  5. ለዳቆን ኤፍሬም
    መቼም መዋሸት የተማርከዉ ከጌቶችህ ከወያኔ ወሮበሎች ነው አፋህ እዳመጣልህ ቀባጥር መሬት እስኪሰጥህ ንፋ ወሬህን

  6. All humans (including church fathers and deacons) make mistakes. Our church teachers actions and words, however, crossed the mistake category and passed into becoming a deliberate sin. Since last December, these people made up a lot of staff (lie), created disturbance in our church. When our church was disrespected and insulted by those two bishops, the priest and individuals in his group failed to stand up for the God church and correct the bishops.
    God gave you more than 4 months to identify your mistake and repent. Because you didn’t take His offer, He took you out of his Holly Church. His door will not be closed forever, therefore, repent and ask for His forgiveness. After that, you should come and ask the congregation for forgiveness. In your teaching you thought us to forgive 7 x 77 time, therefore for our own sake we will forgive you but not forget what happened.

    Your group has already started church service in another location. No one object to that, please leave us with dignity and peace. My advice to D/ Ephrem and his friends is to pray and ask God to open their eyes and lead them to the right direction. Your uncountable ideas, that came out from your many strategy sessions, didn’t bear any fruit. Time to Change.

    Be true to your self and leave a peaceful life.
    God Bless you,

  7. Diyakon epherem, egziabher yibarkeh!! Ante abamela yemitbal zega gin be sinde mehal yemitgegn enkirdad neh.ye amist amet stale yemitawkew diykon men yahil yanten yeshagete chinkilat endebelete ayeh? Maferia neh , yichi akuwamih kazalekechih ena hizbachinen ekefafilalehu yemil akuam kaleh ye ehud fukera men yadergilhal abatachin endalut wede arat kilo kereb bilo zeraf ayishalihm ??? demo finish efer engi tilk azawint honeh bilgena, balege kiletam yeshimagle poletikegna

  8. Deacon Epheram you have been doing so much that has disappointed me and your actions continue to hurt our church. How does trashing a church leader who has taught you almost everything you know about being a deacon helpful in this hard and confusing time for our church? How do you expect people to continue to have trust in your wishes to serve God when you repeatedly insult a priest you should have respect for and when you do dedicate all of your energy into destroying a church that has raised you. Who are you to pass judgment on people when you are blatantly disrespectful to God’s house and to everything that our religion stands for which is unity and forgiveness. Knowing just how corrupted the Ethiopian government is why would you fight to have our beloved church be a part of the Ethiopian Synodos knowing full well that the government meddles in how the church is run? Can you honestly tell me that no one who is fighting to be a part of the Ethiopian church doesn’t have anything to gain whether its money, politics or becoming a papas? on another note our Orthodox Church mass services are secured so why is it that you all are holding services from one place to another. From what I was taught about the bible the church services are not to be held at whatever place that one wishes to have it. It is said in the bible that churches where we worship our lord are not simply buildings randomly picked they are special places where when Jesus Christ our savior’s blood was spilled around the world and places where his blood landed are where churches are to be based at. I would hope that i wouldn’t have to explain this to the people of God and “agelgaies.” You say that the priests and deacons who have stayed to continue services are going against God’s will for holding service at a church that Jesus Christ’s blood has landed, the place that a papas has blessed and the place that has been our spiritual home for over 20 years a place where all of you have served God. You all are outraged by this fact yet you all think it is acceptable for all of you to hold church services wherever you please because you are in a disagreement. I don’t mean any disrespect but that is shameful and Hypocritical on your part. For the week of hemamat you all were willing to go to it and call it your church but continued to disrespect the tabot by participating in service you felt like and walking out on the ones you didn’t feel like. What is worse is that you all post Facebook pictures and statutes to criticize the priest and deacons, whom you should have respect for. I have seen so many disgraceful posts about the leader of our church leka tiguhan, and the other priests and deacons that stand with him and it absolutely saddens me because talking about people when they are not there to defend themselves and trash their good name is just down right childish. We are all adults here and I think it’s time we start acting like one and leave our childish ways in the past. We seem to forget that we are the role models for the future generation that will be taking over this church. Egizabhare yekirybalchiu lebonam yestachu.

  9. ወንድሜ ኤፍሬም
    በመጀመሪያ ሰላመ እግዚ አብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን። በመሰረቱ ስለ እውነት እንነጋገር ከትባለ የቤተክርስቲያን ድምፅ ያለው በካህናቱና በዲያቆናቱ እጅ ነበር በየት በኩል ነው ውሸቱን ከሃይማኖት …..ግማሽ የሃይማኖት ይዘው ህዝቡን ያስጨንቁት? ኤፍሬም ማንም ሰው ቢሆን እኔ ትክክል ነኝ ነው የሚለው ትክለኛውን የሚያውቀው ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው። ብቻ ትልቅ ጥፋት ጠፍቷል። ይህን ያህል ዓመት ስንኖር ለዲያቢሎስ በር ከፍተንለት አናውቅም ነበር።ዛሬ ግን ሁላችንም እልኸኝነት የልብ ትዕቢት ውስጣችንን ሞልተናል በፍቅር ሁሉን ማሸነፍ ይቻል ነበር ግን አልተቻለም። በመጀመሪያ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ብናስብ ኖሮ በዚህ አስቀያሚ ጊዜ ጳጳሳትን ባላመጣን ነበር።በርግጥ እናንተ ያሰባችሁት መባረካቸውን ማስተማራቸውን ነው አብሮ የሚመጣው ነገር ብዙም አላሰባችሁበትም። ግን ይህንን ያህል ዘመን ያላስመጣችሁትን አባት አሁን ማስመጣት ለምን አስፈለገ? ከመጡም ከሁልቱም ወገን ያለውን ነገር ሰምተው አስታራቂ ሀሳብ አቅርበው ባያስታርቁ እንኳን ለማስማማት ቢሞክሩ እንኳን መልካም ነበር።እሳቸው ግን………..እሺ ቅዳሜ የዛን ያህል እረብሻ ከተፈጠረ እሁድ መደገም የለበትም አባቶቹን ቢቻል ማርያም ሄደው እንዲቀድሱ አልያም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ይቻል ነበር። ግን ለምን ይሄ ሁሉ ነገር እንዳስፈለገ እኔ አሁንም አልገባኝም ኤፍሬምዬ እስቲ ለትንሽ ሰዓት ተረጋግተን እናስብበት በዚህ ማሀል ስንት በጎችን እናጣለን በአሁን ሰዓት ስንታችን ነን ቃሉን የተራብን ለእኛ ኑሮ ለተስተካከለልን የቤተክርስቲያን መዘጋት ምንም ላይሰማን ይችላል። በዚህ ጭንቀት ብቸኝነት እራስን የመጥላት ብዙ ብዙ ነገር ባለበት ሀገር በመቅደሱ ተደፍተው የሚያለቅሱ የቤቱ መጥተው ሰላምን የሚለምኑትን ምስኪኖችን ብናስባቸው ጥሩ ነበር። አውቃለሁ እኛ ምን እናድርግ ትለኝ ይሆናል፤ሁሉ በእጃችን ነበር ግን አልትጠቀምንበትም እግዚአብሔር እንደፈቀደ አንድ ቀን እርሱ ይፈታዋል ብዬ አምናልሁ
    ዛሬም ቢሆን ገና ነው ማስተዋልን ከሰጠን ትንሽ ማሰብ ከቻልን ነግሮችን ከማባባስ ሰከን ብለን እናስብ።እስቲ አስቡት “ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት”የሚል ተረት አለ። በሁለቱም በኩል ያለነው ምዕመናን ካህናቶች በዚህ አመት ሁዳዴን ጾምን ብለን እናወራ ይሆናል በርግጥ ስጋ አልበላንም ወተትም አልጠጣንም ግን ቤተ ክርስቲያንን ከመኖር ወደ አለመኖር ቀይረናታል።የሚያሳዝነኝ ትላንት ቤተክርስቲያን መግዛት አለብን ብለን ወደፊት ሩጫችንን ስንሮጥ ይሚይዘን ጠፍቶ ነበር ዛሬ ደግሞ ያለችንን ቤተክርስቲያናችንን ለማፈራረስ የኋሊት እጥፍ እየሮጥን ተዉ የሚለን መጥፋቱ ነው። ማወቅ ያለብን ነገር ግን በመከፋፈል ያደገ አለመኖሩን ነው። ድሮ አንድ ሆነን ዝማሬአችን ማማሩ በመቅደሱ ተስብስበን መገኘታችን የሚሰጠን ስሜት ለመግለፅ ያቅተኛል ። ዛሬ ግን……..በዕለተ ሆሳህና ቅዳሴ አንቀድስም አላችሁን። ለምን? መልሱን እራሳችሁ መለሳችሁልን የአቡን ማቲያስን ስም ካልጠራን አንቀድስም አላችሁ ። ተቀብየዋለሁ ግን የእሳቸው ስም ካልተጠራ የጌታን ስጋ እና ደም ሊቀበል የመጣው ሰው በዚያች ቀን ሊያገኘው የነበረውን የእግዚ አብሔርን በረከትና ክብር ማሳጣታችሁ ምንም አልተሰማችሁም እግዚ አብሔርስ አያዝንባችሁም? ያን ቀን በእናተ ሳይሆን ያዘንኩት በትላልቅ አባቶቼ ነው።እሺ ይሁን ስም መጠራት ከሆን ችግራችን ለምን ማርያም ሄደን አላስቀደስንም? ምንም ይሁን ምን ይህን ሁሉ ጊዜ ያገለገልንበትን ቤተክርስቲያን ቢያንስ ያለውን ነገር ሁሉ ችለን ቢቻል እስከ ስብሰባው ባንችል ደግሞ እስከ ዳግማ ትንሳዬ መቆየት ነበረብን ።መቼም ይህንን ሁሉ ዐመት ቀድሰን ሀጥያት ያልሆነብን 3 ቀን ቀድሰን ሀጥያት ይሆንብናል ብዬ አላስብም።
    ለማንኛውም እኛ አስተማሪ ስንሆን ለብዙዎች የእንቅፋት ድንጋዮች ሆነናልና አምላካችን ያስበን። እንደ እህትነቴ “ከረጋ ወተት ቂቤ ይወጣዋልና “ ትንሽ ተረጋግተን እየሮጥንበት ያለውን መንገድ መጨረሻው የት እንደሚያደርሰን ቆም ብለን ማሰብ አለን እላልሁ። ሰው ባልጌ ሆነና እኛም መሆን የለብንም ሰው ሀጥያት ሰራና እኛም መስራት የለብንም ሲሆን ትዕግስትን ማስተማር እንጂ እናስብበት ሁሉም ያልፋል ካንተ ባላውቅም 3 ጥቅሶችን ጠቅሼ ፅሁፌን ልዝጋው
    እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ። ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም። 1ቆሮ. ም 8፥ 12-13
    ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል 1ቆሮ ም 10፥ 12-13
    በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። 1ቆሮ ም 13 ፥ 1-10 እግዚ አብሔር ለሁላችንም ልቦና ሰጥቶን የመቅደሱ ልጆች ያድርገን አሜን

  10. Deacon Epheram you have been doing so much that has disappointed me and your actions continue to hurt our church. How does trashing a church leader who has taught you almost everything you know about being a deacon helpful in this hard and confusing time for our church? How do you expect people to continue to have trust in your wishes to serve God when you repeatedly insult a priest you should have respect for and when you do dedicate all of your energy into destroying a church that has raised you. Who are you to pass judgment on people when you are blatantly disrespectful to God’s house and to everything that our religion stands for which is unity and forgiveness. Knowing just how corrupted the Ethiopian government is why would you fight to have our beloved church be a part of the Ethiopian Synodos knowing full well that the government meddles in how the church is run? Can you honestly tell me that no one who is fighting to be a part of the Ethiopian church doesn’t have anything to gain whether its money, politics or becoming a papas? on another note our Orthodox Church mass services are secured so why is it that you all are holding services from one place to another. From what I was taught about the bible the church services are not to be held at whatever place that one wishes to have it. It is said in the bible that churches where we worship our lord are not simply buildings randomly picked they are special places where when Jesus Christ our savior’s blood was spilled around the world and places where his blood landed are where churches are to be based at. I would hope that i wouldn’t have to explain this to the people of God and “agelgaies.” You say that the priests and deacons who have stayed to continue services are going against God’s will for holding service at a church that Jesus Christ’s blood has landed, the place that a papas has blessed and the place that has been our spiritual home for over 20 years a place where all of you have served God. You all are outraged by this fact yet you all think it is acceptable for all of you to hold church services wherever you please because you are in a disagreement. I don’t mean any disrespect but that is shameful and Hypocritical on your part. For the week of hemamat you all were willing to go to it and call it your church but continued to disrespect the tabot by participating in service you felt like and walking out on the ones you didn’t feel like. What is worse is that you all post Facebook pictures and statutes to criticize the priest and deacons, whom you should have respect for. I have seen so many disgraceful posts about the leader of our church leka tiguhan, and the other priests and deacons that stand with him and it absolutely saddens me because talking about people when they are not there to defend themselves and trash their good name is just down right childish. We are all adults here and I think it’s time we start acting like one and leave our childish ways in the past. We seem to forget that we are the role models for the future generation that will be taking over this church. Egizabhare yekirybalchiu lebonam yestachu..

  11. ወንድሜ ኤፍሬም
    በመጀመሪያ ሰላመ እግዚ አብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን። በመሰረቱ ስለ እውነት እንነጋገር ከትባለ የቤተክርስቲያን ድምፅ ያለው በካህናቱና በዲያቆናቱ እጅ ነበር በየት በኩል ነው ውሸቱን ከሃይማኖት …..ግማሽ የሃይማኖት ይዘው ህዝቡን ያስጨንቁት? ኤፍሬም ማንም ሰው ቢሆን እኔ ትክክል ነኝ ነው የሚለው ትክለኛውን የሚያውቀው ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው። ብቻ ትልቅ ጥፋት ጠፍቷል። ይህን ያህል ዓመት ስንኖር ለዲያቢሎስ በር ከፍተንለት አናውቅም ነበር።ዛሬ ግን ሁላችንም እልኸኝነት የልብ ትዕቢት ውስጣችንን ሞልተናል በፍቅር ሁሉን ማሸነፍ ይቻል ነበር ግን አልተቻለም። በመጀመሪያ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ብናስብ ኖሮ በዚህ አስቀያሚ ጊዜ ጳጳሳትን ባላመጣን ነበር።በርግጥ እናንተ ያሰባችሁት መባረካቸውን ማስተማራቸውን ነው አብሮ የሚመጣው ነገር ብዙም አላሰባችሁበትም። ግን ይህንን ያህል ዘመን ያላስመጣችሁትን አባት አሁን ማስመጣት ለምን አስፈለገ? ከመጡም ከሁልቱም ወገን ያለውን ነገር ሰምተው አስታራቂ ሀሳብ አቅርበው ባያስታርቁ እንኳን ለማስማማት ቢሞክሩ እንኳን መልካም ነበር።እሳቸው ግን………..እሺ ቅዳሜ የዛን ያህል እረብሻ ከተፈጠረ እሁድ መደገም የለበትም አባቶቹን ቢቻል ማርያም ሄደው እንዲቀድሱ አልያም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ይቻል ነበር። ግን ለምን ይሄ ሁሉ ነገር እንዳስፈለገ እኔ አሁንም አልገባኝም ኤፍሬምዬ እስቲ ለትንሽ ሰዓት ተረጋግተን እናስብበት በዚህ ማሀል ስንት በጎችን እናጣለን በአሁን ሰዓት ስንታችን ነን ቃሉን የተራብን ለእኛ ኑሮ ለተስተካከለልን የቤተክርስቲያን መዘጋት ምንም ላይሰማን ይችላል። በዚህ ጭንቀት ብቸኝነት እራስን የመጥላት ብዙ ብዙ ነገር ባለበት ሀገር በመቅደሱ ተደፍተው የሚያለቅሱ የቤቱ መጥተው ሰላምን የሚለምኑትን ምስኪኖችን ብናስባቸው ጥሩ ነበር። አውቃለሁ እኛ ምን እናድርግ ትለኝ ይሆናል፤ሁሉ በእጃችን ነበር ግን አልትጠቀምንበትም እግዚአብሔር እንደፈቀደ አንድ ቀን እርሱ ይፈታዋል ብዬ አምናልሁ
    ዛሬም ቢሆን ገና ነው ማስተዋልን ከሰጠን ትንሽ ማሰብ ከቻልን ነግሮችን ከማባባስ ሰከን ብለን እናስብ።እስቲ አስቡት “ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት”የሚል ተረት አለ። በሁለቱም በኩል ያለነው ምዕመናን ካህናቶች በዚህ አመት ሁዳዴን ጾምን ብለን እናወራ ይሆናል በርግጥ ስጋ አልበላንም ወተትም አልጠጣንም ግን ቤተ ክርስቲያንን ከመኖር ወደ አለመኖር ቀይረናታል።የሚያሳዝነኝ ትላንት ቤተክርስቲያን መግዛት አለብን ብለን ወደፊት ሩጫችንን ስንሮጥ ይሚይዘን ጠፍቶ ነበር ዛሬ ደግሞ ያለችንን ቤተክርስቲያናችንን ለማፈራረስ የኋሊት እጥፍ እየሮጥን ተዉ የሚለን መጥፋቱ ነው። ማወቅ ያለብን ነገር ግን በመከፋፈል ያደገ አለመኖሩን ነው። ድሮ አንድ ሆነን ዝማሬአችን ማማሩ በመቅደሱ ተስብስበን መገኘታችን የሚሰጠን ስሜት ለመግለፅ ያቅተኛል ። ዛሬ ግን……..በዕለተ ሆሳህና ቅዳሴ አንቀድስም አላችሁን። ለምን? መልሱን እራሳችሁ መለሳችሁልን የአቡን ማቲያስን ስም ካልጠራን አንቀድስም አላችሁ ። ተቀብየዋለሁ ግን የእሳቸው ስም ካልተጠራ የእግዚ አብሔር ስም አይጠራም ? የጌታን ስጋ እና ደም ሊቀበል የመጣው ሰው በዚያች ቀን ሊያገኘው የነበረውን የእግዚ አብሔርን በረከትና ክብር ማሳጣታችሁ ምንም አልተሰማችሁም ? እግዚ አብሔርስ አያዝንባችሁም? ያን ቀን በእናተ ሳይሆን ያዘንኩት በትላልቅ አባቶቼ ነው ቤተ ክርስቲያንስ ያዘነባቸው በመሪ ጌታ ሳይሆን በነ አባ ነው። ትላንት መሪ ጌታ ተገዝተዋል ስንል ዋልን ዛሬ ደግሞ ክህነታቸው ተወሰደ እንጂ አልተገዘቱም አልን የምንነጋገረውን እራሱ በደንብ አናውቀውም። እሺ ይሁን ስም መጠራት ከሆን ችግራችን ለምን ማርያም ሄደን አላስቀደስንም? ምንም ይሁን ምን ይህን ሁሉ ጊዜ ያገለገልንበትን ቤተክርስቲያን ቢያንስ ያለውን ነገር ሁሉ ችለን ቢቻል እስከ ስብሰባው ባንችል ደግሞ እስከ ዳግማ ትንሳዬ መቆየት ነበረብን ።መቼም ይህንን ሁሉ ዐመት ቀድሰን ሀጥያት ያልሆነብን 3 ቀን ቀድሰን ሀጥያት ይሆንብናል ብዬ አላስብም። ለማንኛውም እኛ አስተማሪ ስንሆን ለብዙዎች የእንቅፋት ድንጋዮች ሆነናልና አምላካችን ያስበን። እንደ እህትነቴ “ከረጋ ወተት ቂቤ ይወጣዋልና “ ትንሽ ተረጋግተን እየሮጥንበት ያለውን መንገድ መጨረሻው የት እንደሚያደርሰን ቆም ብለን ማሰብ አለብን እላልሁ። እናስብበት ለፍቅር እንጂ ለጸብ አንሽቀዳደም ። ካንተ ባላውቅም 3 ጥቅሶችን ጠቅሼ ፅሁፌን ልዝጋው
    እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ። ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም። 1ቆሮ. ም 8፥ 12-13
    ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ። ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል 1ቆሮ ም 10፥ 12-13
    በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። 1ቆሮ ም 13 ፥ 1-10 እግዚ አብሔር ለሁላችንም ልቦና ሰጥቶን የመቅደሱ ልጆች ያድርገን አሜን

  12. kale hieywet yasemalen .Endezehe ewenet yemenager chrestian ayastan.lehulachenem lebuna yesten

  13. D/n Ephrem God bless you and thank you so much, Negergin enezih sewoch geleltegnanen bayoch iwunetin lemamen libachewu dendinuwal weyim ” alemamen tinikarenewu” yemil yelenin phlosophy ayimiroachewun tebtibo yizowal.beterefe ene le Ato Getahun toloniqa belut yemitwedut sewoch ke may 11 bewala demoz mafes yelem, mortgage yelem qedimomi apartment neberkina wede apartment temelesaleh aleziya adarihina wuloohi post road yihonal becikane 47 hig reqolihalina wedewal temelisehi JUNE 02 IMAGE adirgewu. kemilase tsegur yineqelal. digisu yiyenewu.

Comments are closed.

Share