የናቁትን «አረዳ» ሊጎበኙ መጥተው  «አረዳ ጠባቂ» ብሎ ጠባቂውን መናቅ ምን ይሉት እውቀት ነው?

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመካነ ጦማራቸው ለጻፉት የተሠጠ ማስተካከያ ምላሽ፤

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ታሪክ ሰፊና ረጅም ነው። በገዳሙ ውስጥ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያለፉበትን ችግርና መከራ ለመናገርም ጊዜ ይጠይቃል። ነገር ግን በዚህ ዘመን ባለው ትውልድ የቀደምቶቹም ይሁኑ የአሁኖቹ ገዳማውያን እናቶችና አባቶች ታሪክና ቅርስ ተረክበው ከቦታው ላይ በመገኘታቸው ብቻ  «አረዳ ጠባቂና የዶላር ደመወዝተኛ» ተብለው የሚዘለፉበትን ምክንያት ግልጽ አይደለም። ዘመናዊ ትምህርትና እውቀት መገብየት የዘመኑን ተግዳሮት ለመረዳት ጠቃሚ ስለሆነ ተቀባይነት እንዳለው እንረዳለን። ነገር ግን ዘመናዊው እውቀት በራሱ የመንፈሳዊው ሕይወት አንድ አካል ተደርጎ ከተወሰደ ችግር አለው። ከዘመኑ ጋር ተዋውቀናል፤ ተምረናል የሚሉ ክፍሎች ብዙ ጊዜ በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ራሳቸውን በጣሉ ሰዎች ላይ ያላቸው እውቀት ያልተስተካከለ ነው።  አባቶቻችን ልዩ ልዩ ቋንቋ  አለመማራቸው ወይም አለማወቃቸው የአላዋቂነታቸው መጨረሻ አድርጎ የሚመለከት ትውልድ ባልተማሩ እናትና አባቱ የሚያፍር፤ አባቱንና እናቱንም የሚረግም ትውልድ ነው።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ የሚኖሩ አባቶችና እናቶች ሁሉም የዘመናዊ እውቀት ባለቤቶች አይደሉም። በገዳማዊ ሕይወታቸው ተወስነው በጾም በጸሎት የሚያገለግሉ ነገር ግን በተነከረ የጣት ቀለም የሚፈርሙ በመሆናቸው ብቻ ምንም እንደማያውቁ፤ ኢየሩሳሌምም ለመኖር ብቁ እንዳይደሉ ማሰብ አሳዛኝ ነው። የእግዚአብሔር ጸጋ ከማን ጋር እንዳለ መዛኙ ማነው? መለኪያውስ ምንድነው? ለ፳፻ ዓመታት ያህል መከራውን ችለው፤ ረሃቡን ታግሰው  ገዳሙን ያቆዩ አባቶቻችን በአላዋቂነት መመልከት አግባብ አይደለም።

እዚህ ላይ አንድ የተፈጸመ እውነተኛ ታሪክ ልናስታውስ ወደድን። በቅርብ ጊዜ ወደማያልፈው ዓለም በሞት የተለዩን እናት ጤንነታቸውን ለመመልከት ለመጣ ሐኪም እንዲህ አሉ።

ስምዎ ማነው? ብሎ ሐኪሙ ይጠይቃቸዋል።

ስሜ፤ ስሜ…… አሉና ሊያስታውሱ ሞከሩ። ነገር ግን ሊያስታውሱ ባለመቻላቸው ጓደኛቸውን «ስሜ ማነው?» ብለው  እስከመጠየቅ ደርሰዋል። እንኳን የዚህ ዓለም ጣዕም ሊያጓጓቸው ቀርቶ ስማቸውን ማስታወስ ያልቻሉ መንፈሳዊያን የኖሩበትና ያሉበት መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው።

ዲያቆን ዳንኤል ግን « ከዐሥር ዓመታት በላይ ተቀምጠው ዐረብኛና ዕብራይስጥ የማይችሉ ከሆነ ኢየሩሳሌም መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው?» ይሉናል። የሀገሩን ቋንቋ መቻል ጥሩ ነው። ለመግባባት አስፈላጊ መሣሪያ ስለሆነ የሚናገሩትን ማዳመጥ ይቻላል፤ የምንናገረውን ለሰሚው ለማቅረብ ያግዘናል። በዚህ መልኩ ደግሞ በገዳሙ ውስጥ በዐረብኛ፤ በዕብራይስጥና በእንግልጣር መግባባት የሚችሉ አባቶችና እናቶች ችግር የለበትም። ነገር ግን ዐሥር ዓመት ተቀምጠው መናገር ያልቻሉ መኖራቸው ብቻውን በኢየሩሳሌም የመኖር ጥቅሙ ምንድነው? የሚያሰኝ ከሆነ አስተሳሰቡ ችግር አለው። የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ካለማወቅ የመጣ ነው፤ አለበለዚያም «ቋንቋ መቻል አዋቂ ነው» ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ ከአባቶችና እናቶች ማኅበር ውስጥ ለመኖር አስፈላጊው ነገር ገንዘብ፤ እውቀትና ብልጠት አይደለም። የእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ!                                                                                                   ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ለእያንዳንዱ ሰው የኑሮ ዘመኑንና የመኖሪያ ስፍራው በእግዚአብሔር እንደተመደበ ገልጿል።

«ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው» የሐዋ 17፤26-27

ስለዚህ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ ያሉ እናቶችና አባቶች ደካማ ይሁኑ ጠንካራ እየኖሩ ያሉት በፈቃደ እግዚአብሔር ይኖሩ ዘንድ በተወሰነላቸው ስፍራ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዋቢ አድርጎ መናገር ይቻላል። ከዚህ ተነስተን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደተሳላሚ ወደ ገዳሙ መጥተው «ቋንቋ ካልቻሉ ኢየሩሳሌም የመኖር ጥቅሙ ምንድነው?» በማለት ቋንቋ መቻልን ኢየሩሳሌም ከመኖር ጋር ማስተሳሰራቸው ተገቢ አይደለም።  ዲያቆን ዳንኤል በመካነ ድራቸው ለጥቀው እንዲህ ይሉናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይነበብ «ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም» የ 6 ዓመቷ ህፃን ከወለጋ

«በማንኛውም መድረክ ተገኝተው ቤተ ክርስቲያንን ሊወክሉ የሚችሉ፣ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጭ ፈጥረው የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዱ ተቋማትን የማያፈሩ ከሆነ መነኮሳቱ ‹‹አረዳ ጠባቂ›› ከመሆን ያለፈ ለቤተ ክርስቲያን በቁዔታቸው ምንድን ነው?»

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ያሉ አበው መነኮሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክለው በልዩ ልዩ መድረኮች መገኘት መቻላቸው ጥሩ ነው። ገቢ በመፍጠርም የገጠር አብያተ ክርስቲያናትንም መርዳት ቢችሉ የመንፈሳዊ ትጋት አንዱ ማሳያ ስለሆነ በበጎነቱ የሚታይ ነው። ነገር ግን ይህንን ማድረግ አለመቻል ብቻውን መነኮሳቱን «አረዳ ጠባቂ» ከመሆን ያለፈ በቁዔት እንደሌላቸው ማሰብ ግን የጤንነት ምልክት አይደለም።  ያንን «አረዳ» ለመጎብኘት የተቻለው እኮ እነዚያ ከአረዳ ጠባቂነት ያለፈ ድርሻ የሌላቸው የተባሉት መነኮሳት ጠብቀው ስላቆዩት መሆኑን አለማሰብ የመንፈስ ጉድለት ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?

የኢትዮጵያ ገዳም ሁለቱ ቤተ መቅደሶች ማለትም የመድኃኔዓለምና የዐርባእቱ እንስሳ ቤተመቅደሶች ለ፹/80/ ዓመታት ያህል ተዘግተው እንዳይከፈቱ በተደረገበት በዚያ ክፉ ዘመን ኢትዮጵያኑ መነኮሳትና መነኮሳይያት የሽኮኮ ማደሪያ በመሰለው በዓታቸው ተከተው ዘመነ ዐጸባውን ያሳለፉት በረሃብና በመከራው ተሰቀው ይዞታውን ለቀው ይሄዳሉ እየተባለ ሲጠበቅ፤ ተራ በተራ ለሠርከ ኅብስት ልመና እየወጡ በጠባብ ጭንቅ አሳልፈው ነው። ፹ ዓመታትን እንደ ፹ ቀናት ታግሰው የተዘጋ ቤተመቅደሳችን አንድ ቀን ይከፈታል ብለው፤ በአምላካቸው ላይ ተስፋ ጥለው፤ በምድሩ ላይ እንደትኋን ተጣብቀው በመቆየታቸው እነሆ ዛሬ አእላፋት ታሪካችን ብለው በመንፈሳዊ ኩራት የሚመኩበትን ቤተመቅደስ «ቀኑ ሲደርስ አምባ ይፈርስ» እንዲሉ የቤተመቅደሱን ቁልፎች ተረክበው ያቆዩት «አረዳ ጠባቂ» የተባሉት ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ከመታመን በላይ ምንም የዘመኑ እውቀት ያልነበራቸው አባቶቻችን ናቸው።

የሀገሩን ቋንቋና ባህል በማወቅ፤ ግብጻውያን ከሚያደርሱብን መንፈሳዊ ያልሆነ ተጽዕኖ ነጻ ለመሆን ራሳችን ተጠናክረን መገኘት እንደሚገባ ይገባናል። ነገር ግን በዚህ ጉድለታችን ተጠግቶ ጠባቂነት ዋጋ የሌለው አድርጎ ማቅረብ ራስን የእውቀት ጥግ አድርሶ በማስቀመጥ ሌላውን አሳንሶ ከመመልከት የሚመነጭ ነው።

ዲያቆን ዳንኤል የገዳሙን መነኮሳት ከሸነቆጡበት አሳብ ሌላውን እንመልከት።

«ኢየሩሳሌም መመደብ ከሥጋዊ ዕድል በዘለለ ጥቅሙ ምንድን ነው? የራሳችን የቅብዐ ቅዱስ ማዘጋጅ፣ የዕጣን መቀመሚያ፣ የንዋያተ ቅድሳት ማዘጋጃ፣ የመስቀል መሥሪያ፣ ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ጥቅሙ በዶላር ደመወዝ ማግኘት ነው ማለት ነው፡»

እውነት ለመናገር የኢየሩሳሌም ገዳም መነኮሳት ከገዳሙ ውጪ ወጥተው በሌላው ሀገር እንደሚደረገው ተጨማሪ ሥራ በመሥራት የሚያገኙት ገንዘብ የለም። የገዳሙ ሕግ ይህንን ይከለክላል። ገዳሙ በደመወዝ ለማኅበረ መነኮሳቱ የሚሰጠውም ክፍያ የለውም። ነገር ግን ሀገሩን ሳያዩ በሀብታቸው ቤት ገዝተው ለአባቶች መርጃ ይሆነው ዘንድ በስጦታ ከነገሥታትና ንግሥታት፤ ከወንድ መኮንን ከሴት ወይዘሮ ከተበረከተለት ቤቶች ከሚያገኘው ጥቂት የኪራይ ገቢና በዓመት ከሚመጡ ተሳላሚ ኢትዮጵያውያን የሚያገኘው ገንዘብ ካልሆነ በስተቀር ሌላ የገቢ ምንጭ የለውም። ይህንን ገንዘብ አጠራቅሞ በገዳም ደንብ ገባዕተ ነግህና ገባዕተ ሰርክ ሳይል /ገዳሙ ውስጥ ፶ ዓመት የተቀመጠም ይሁን ትላንት ወደአንድነቱ ለገባ/ ለሁሉም እኩል የሆነ የኪስ መቁንን ይሰጣል።  ደመወዝ የለም የሚያሰኘውም ይህ ነው። ደመወዝ ለሰራው፤ ላገለገለውና ለሰጠው ግልጋሎት እንደየደረጃው የሚከፈል ሲሆን ገዳማዊ መቁንን ግን ያገኙትን በእኩል የሚቋደሱት፤ ከሌለ ደግሞ መከራውንና ችግሩን ታግሰው የሚቀመጡበት ስፍራ ነው። በዚህ መልኩ ከታየ ከኢትዮጵያ ውጪ መነኮሳት በማኅበር ሆነው በመቁንን የሚኖሩበት ከኢየሩሳሌም በስተቀር ሌላ ስለመኖሩ አናስታውስም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እነስብሀት ነጋ ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል

ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው የገዳሙ የኑሮ ሕይወት ገዳማዊ እንጂ የገንዘብ ጥቅም የሞላበት አይደለም። ዲያቆን ዳንኤል ከኢትዮጵያ ውጪ «በኢየሩሳሌም መመደብ ዶላር ለማግኘት ካልሆነ» ብለው መነኮሳቱን ለገንዘብ እንደሚኖሩ አድርገው የሚዘልፉት ለምን ይሆን? ዛሬ በምድርም፤ በአየርም የግንኙነት መስመሩ ስለሰፋና ኢትዮጵያውያን ተሳላሚዎች ስለበረከቱ የኪስ መቁንን መስጠት ተጀመረ እንጂ ገዳሙ ምን ባልነበረው ዘመን አባቶቻችን ዮርዳኖስ ማዶ ከዳጋማው ሀገር ተሻግረው ስንዴና ገብስ አጭደው በቀን ሠራተኝነት በሚያገኙት ገንዘብ ደረቅ ዳቦ ገዝተው አንጀታቸውን አስረው ያቆዩት ገዳም ዛሬ «የአረዳ ጠባቂዎች» ማኅበር መሰኘቱ በጣም አሳዛኝ ነው። በእርግጥ ርስትና ቅርስ ጠብቆ መገኘት ያኮራል እንጂ አያሳፍርም። በእናቱ ጠባሳ ከሚያፍር ትውልድ እንዲሰውረን ግን እንጸልያለን።

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ጥሮ ግሮ እንዲበላ አዞታል። ይልቁንም መነኮሳት በራሳቸው የስራ ውጤት እንዲተዳደሩ መጻሕፍተ መነኮሳት ያዛሉ። ነገር ግን ኢየሩሳሌም መገኘት ብቻውን ልብ እንደሚመኘው «የንዋያተ ቅድሳት ዝግጅት ማለትም ቅብዓ ቅዱስ፤እጣን መስቀልና ሌሎች ቅርሶችን ለማዘጋጀት በአፍ እንደሚነገረው እንዲህ ቀላል አይደለም። ነገር ግን የማይቻለውን እንዲቻል በሚያደርግ በእግዚአብሔር ኃይልና በመንፈሳዊ አሳብ ከተነሳን ማድረግ እንደሚቻል እናምናለን። ይህንን ለማድረግ የእያንዳንዱ ድርሻ እንዳለ ሆኖ የኔ ድርሻ ምን ሊሆን ይገባል? ብሎ ራስን መጠየቅ ተገቢ ነው። ከዚያ ውጪ በድክመታቸው ወይም ባለማወቃቸው ላይ ጣትን እየጠቆሙ «ይህንን ያላደረጉ አባቶች የሚኖሩት ለዶላር ነው» ማለት ዘለፋ እንጂ በጎነት አይደለም። ዲያቆን ዳንኤል ዶላር ለመነኮሳቱ  በስውር ሰጥተው ከሆነ ቢነግሩንና፤ በግልጽ ለሚከፍል አምላክ በስውር ብንጸልይላቸው ጥሩ ነበር። ያንን ማድረግ ባይችሉ ወይም ባይፈቅዱ እንኳን ያልኖርበትን ሕይወት «የዶላር ሕይወት» በማለት ጫማቸውን ባያነሱብን ራሱ ውለታ እንደዋሉልን እንቆጥራለን።  ምክንያቱም በአባቶቹ ድክመት፤ ስንፍናና አለማወቅ የሚዘባበት ትውልድ እድሜውም አጭር፣ ዘመኑም ትንሽ በመሆኑ ተግሳጻዊ ምክር ማንሳታችን ራሳቸውን የሚያዩበት እድል ለመስጠት ነው። ትውልዱ ከአባቶቹ የበለጠ ያወቀ ስለሚመስለው ምክር አይቀበልም። እንደዚያም ሆኖም በአባቶች ያለውን ከዘመኑ ጋር ያለመጓዝ የተወሰነ ክፍተት በማስተካከል፤ ወጣቱም ከችኩልነቱና ከተሻለ አዋቂነት ስሜቱ ረጋ ብሎ በሰከነ መንፈስ ሰምና ፈትል ሆኖ ከአባቶቹ ጋር ቢጓዝ አደራውን ተረካቢ ትውልድ ማግኘት ይቻላል። ከዚያ በሻገር «ዋኖቻችሁን አስቡ» ከተባለው ቃል በተቃራኒ «ዋኖቻችሁን ዝለፉ» የተባለ አይመስለንም።

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ለመኖር የሚያስገድደን ጥቅም እንደሆነ የሚያስብ ትውልድ እንዲኖር ስለማንፈልግ የዲያቆን ዳንኤል ጽሁፍ ፍጹም የተሳሳተ መረጃ መሆኑን አበክረን እንናገራለን። ኢየሩሳሌም መኖሩ በራሱ ምድራዊ ሀብት ሊለካው የማይችል ጸጋ ነው። ኢየሩሳሌም ማለት በአጭር ቃል «መጽሐፍ ቅዱስ» ማለት ነው። ትርጉሙስ «የሠላም መሠረት» ማለት አይደል? የሠላም መሠረት ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ወዲያ የት አለ? ስለዚህ ኢየሩሳሌም በክረምት ከዜሮ በታች፤ በበጋ ደግሞ 400ሴ በላይ ሙቀት ውስጥ የሚያኖረን የቅድስቲቱ ሀገር መንፈሳዊ ፍቅርና አባቶቻችን ከመንግሥታቸውና ከሕዝባቸውና ተነጥለው ማንም አስታዋሽ ባልነበራቸው በረጅም ዘመን ያሳለፉትን መከራና አደራ ብቻ እያሰብን መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ልንሳውቅ እንወዳለን።

ዲያቆን ዳንኤል፤ አሁን በግብጾች እጅ ስለተያዘው የዋና በር ቁልፍ ያቀረቡትም ጽሁፍ የተዛባ ዘገባ ስለሆነ ሊስተካከል ይገባል። ቁልፉ ከኢትዮጵያውያን እጅ ተነጥቆ ለግብጻውያኑ የተመለሰው ዲያቆን ዳንኤል እንዳሉት ሳይሆን በ1950ዎቹ ዓ/ም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከግብጾች ጋር በጆርዳን ሀሽማታዊ ግዛት ንጉሥ ሁሴን በተቋቋመው ፍርድ ቤት ባቀረቡት ማስረጃ ለኢትዮጵያውያን ከተወሰነና ቁልፉን ተረክበው 40 ቀን ከቆዩ በኋላ የግብጹ ፕሬዚዳንት ጋማል አብደል ናስር ለግብጾች መነኮሳት መብት ሲል ለንጉሥ ሁሴን በመጮሁ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ነገር ግን ዲያቆን ዳንኤል የተጣራውን መረጃ ከማኅበረ መነኮሳቱ ጽ/ቤት ቀርቦ ከመቀበል ይልቅ ያንን ሁሉ መንገድ ተጉዘው በተሳሳተ መረጃ መነኮሳቱ አሳልፈው የሰጡ በማስመሰል ከሌላ ታሪክ ጋር እያጣረሱ መጻፍ ተገቢ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢዜማ በዋሽንግተን ዲሲ በነበረው ዝግጅት ላይ ከመጪው ምርጫ ፉክክር በፊት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንዳሉ አስታውቋል

ዲያቆን ዳንኤል «ቁራጭ ጧፍና ውሃ በመሸጥ» ብለው የዘገቡት ነገር መስረቅ እንጂ ያለውን ሸጦ መኖር ስራ ስለሆነ አያስነውርም። ዲያቆን ዳንኤል፤ በምን ገቢ «አረዳ» ያሉትን ቅዱስ ቦታ ሊጎበኙ እንደመጡ ባናውቅም እሳቸውም ይህንን መሰል የገቢ ማስገኛ መንገድ ቢፈጥሩ ያስመሰግናቸዋል እንጂ አያስተቻቸውም።  በዘንድሮው በዓል ላይ ለመሸጥ ያስገደደን ምክንያት በየዓመቱ ለሚመጡ ተሳላሚ ኢትዮጵያውያን ጧፍና እሽግ ውሃ የሚያቀርቡት በአካባቢው ያሉ የዐረብ ወጣቶች ሲሆኑ የሚያስከፍሉት ገንዘብ እጅግ ውድ በመሆኑ የተነሳ አንድም የኢትዮጵያውኑ ገንዘብ ለኢትዮጵያ ገዳም እንዲገባ ከማሰብ፤ በሌላ መልኩም ኢትዮጵያውያኑ ባልተረፋቸው ገንዘብ ከዋጋ በላይ እየከፈሉ በመቆየታቸው የተነሳ ለወጪ እንዳይዳረጉ ሲባል በጎ አመለካከት ካላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በቀረበ አሳብ የተፈጸመ እንጂ ገንዘብ ለመሰብሰብ አይደለም። ደግሞም ሰርቶ መኖር የማንም ሸክም ከመሆን ይታደጋል።

«ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም» 2ኛ ተሰ 3፤8

በተረፈ ዲያቆን ዳንኤል፤ ገዳሙን የሚጠቅም፤ የሚያሳድግና ረብ ያለው ሃሳብዎን ይዘው በመጣት ከቻሉ በተግባር ሠርተው እንዲያሠሩ በጸሎታችን እናግዝዎታለን። ከዚህ በፊት ብዙዎች ተናግረውት አንድም ነገር መስራት ያልቻሉበት ሁኔታ እንዲገጥምዎ  ግን አንመኝም።  ድክመትን መናገርና ወደተግባር መቀየር የተለያዩ ነገሮች ስለሆኑ ብዙዎች ተናግረው በቃላቸው መርጋት አልቻሉም። ድክመታችን፤ስንፍናችንና አለማወቃችን እየታየ እንዳስቸገርዎ ካሰቡ ግን መሥራት አቁመዋል። የሚሠራ እንጂ የሚነቅፍ ባልጠፋበት ዘመን እንደመገኘትዎ መጠን በዘመናዊ አስተሳሰብ ያደጉ ከመሰልዎ  እና የተሻለ ትችት አቅራቢ ለመሆን አስበው ከሆነ አስተዋይ ልቡና እንዲሰጥዎ እንመኛለን። እኛ ገዳማውያኑ  አባቶች ያቆዩልንን ርስትና ቅርስ ያንን «አረዳ» ያሉትንና፤  እርስዎም ለመጎኘት ቸል ያላሉትን ሥፍራ ከመጠበቅ ለአፍታም አንዘናጋም። «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዳለው ጠቢቡ የመከራ ዘመኑን እግዚአብሔር አንድ ቀን እንደሚገፈው አንጠራጠርም። እስራኤል ከጠፋችበት ከሁለት ሺህ ዘመን በኋላ ትንሣዔዋን ያበሰረ አምላክ ዴር ሡልጣን ገዳማችንንም የኢትዮጵያ ብቸኛ ይዞታ መሆኑን ለማብሰር የሰው እውቀት፤ ህግ፤ ጥበብና ሰልፍ ለእግዚአብሔር አስፈላጊው አይደሉም።  ፹ ዓመታትን ለማስከፈት የተደረገው ትግል ሳይፈጽመው «መከራው በቃ» ባለበት ሰዓት የእሽጉን ቁልፍ ሰብሮ፤ ሸረሪት ያደራበትን ጠፍ ቤተመቅደስ የሰጠን አምላክ ማንም ይሆናል ብሎ ባላሰበበት መንገድ ነው። ዛሬም ለሁሉም ያለን አክብሮት ሳይጓደል ከማንም ምንም ሳንጠብቅ የርስታችን ደብዳቤ በእርግጠኝነት እንደምናገኝ በአምላካችን ላይ ያለን ተስፋ ታላቅ ነው። እንደግብጻውያን የትግል ብዛትና ዘረፈ ብዙ ጥረት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያውያን በዚያ አረዳ የድንጋይ ንጣፍ ይዞታ ላይ አንድም ቀን ባላደርን ነበር።

ስለሆነም በአምላክ ላይ ያለንን እምነት ሳንቀንስ ሁላችንም በጸሎት እንበርታ! አስተዋይ ልቡና ይስጠን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን።

በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ማኅበር

እስራኤል፤

9 Comments

  1. Good orthodox church, the backward empire builder, still asking for ignorance of the people to finish them with hunger.
    Orthodox need to be banned from Ethiopia, because it is the source of ignorance. Those people who don’t want to read or learn to read, how did they learn religion? For devil? They were sent to Isreal because they were relatives of the ruling party of the former regime. they are not religious but money seeking, people.

    • at Dolom
      As you name decribe your are not only ignorant, but dull! I see who your inside when you open your mouth.

  2. ዳንኤል ያለው በቤተ ክህነት በኩል ስለሚመደቡት ሰዎች ነው። ማስተካከያ ሰጭው እያወሩ ያሉት በፈቃዳቸው ዓለም በቃን ብለው በገዳሙ ስለሚኖሩት አባቶችና እናቶች ነው። ገዳሙን ለማስተዳደር የሚመደቡ አባቶች አሁንም ዘመኑን የዋጀ ትምህርት፣ሕይወት ያስፈልጋቸዋል። ካልሆነ ለሹመት ብቻ መሽቀዳደም ያው ለዶላር ነው ሹመቱ ከሚለው ትችት ማመለጥ አይቻልም።

    ዲ /ን ዳንኤል የፃፈውን ደግማችሁ አንብቡ ማስተካከያ ለመስጠት ከመሮጥ በፊት ። ያንድ የቤ/ክ አባል አስተያየት ደግሞ ማስተካከያ መግለጫ ማዉጣት አያስፈልገውም። ለዚህ ከመቸኮል ለሌላ አገልግሎት ቸኩሉ።
    ለማንኛውም የርሱ ፅሁፍ ይሄው።
    ” … ለመሆኑ ወደ ኢየሩሳሌም ገዳማት የምንመድባቸው አባቶች መመዘኛቸው ምንድን ነው? የሃይማኖት ትምህርት፣ የእምነት ጽናት፣ ለጸሎትና ለአገልግሎት ያላቸው ፍላጎት፣ ለመማር ያላቸው ትጋት፣ ከአካባቢው ጋር ተዛምደው ለመኖር ያላቸው ዝግጁነት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አምባሳደር ለመሆን ያላቸው ችሎታ ይታያል? ከዐሥር ዓመታት በላይ ተቀምጠው ዐረብኛና ዕብራይስጥ የማይችሉ ከሆነ ኢየሩሳሌም መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? አገልግሎቱ ሲሆን ከሀገር ቤት ካልበለጠ ካልሆነም እንደ ሀገር ቤቱ ካልሆነ በኢየሩሳሌም ገዳማት መኖሩ በአሜሪካ ከመኖር ልዩነቱ ምንድን ነው? በኢየሩሳሌም ገዳማችን ደረጃውን የጠበቀ፣ አባቶችን ለዓለም አቀፋዊ አገልግሎት የሚያበቃ ትምህርት ቤት ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ከሥጋዊ ዕድል በዘለለ ጥቅሙ ምንድን ነው? የራሳችን የቅብዐ ቅዱስ ማዘጋጅ፣ የዕጣን መቀመሚያ፣ የንዋያተ ቅድሳት ማዘጋጃ፣ የመስቀል መሥሪያ፣ ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ጥቅሙ በዶላር ደመወዝ ማግኘት ነው ማለት ነው፡፡ የኢየሩሳሌም ገዳማችን ቤተ ክርስቲያናችን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያጠናክሩ፣ ከአካባቢው ባለ ሥልጣናት ጋር በሚገባ ተግባብተው የገዳማችንን መብት የሚያስከብሩ፣ በልዩ ልዩ ሞያ ሠልጥነው ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተስፋ የሚሆኑ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ለማወቅ የሚመጡትን ምሁራን በደረጃቸው የሚያናግሩ፣ በማንኛውም መድረክ ተገኝተው ቤተ ክርስቲያንን ሊወክሉ የሚችሉ፣ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጭ ፈጥረው የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዱ ተቋማትን የማያፈሩ ከሆነ መነኮሳቱ ‹‹አረዳ ጠባቂ›› ከመሆን ያለፈ ለቤተ ክርስቲያን በቁዔታቸው ምንድን ነው? መቼም ይህንን ሁሉ ያላደረግነው በግብጻውያን ምክንያት ነው አንልም፡፡”
    http://www.danielkibret.com/2014/04/blog-post_22.html#more

  3. Amesgnalehu abatochin silakeberhilen
    Awakinen bayochi betekirstianen yematfat
    Telko new yezew yemetut.erasachewn diakon,mergeta,
    Eyalu betekrstianachin eyebetbetu new yalut.
    Bemgemeriya ewnetegna yebetkrstian lig bihonu
    Adelm egziabehair yemertachew abatochachin ayidelam
    lelawn sew makiber neberebachew.gin enzih alamachew yetfat alama
    new yalachew.silzih abatatochin eyawaredu eyenaku behizbi zend yalachewn
    tesminet asatitew. Erasachewn awaki adergew teseminet lemagegnet
    akuarachi menged metekemachew new gin ayisakalachewm .

    egziabehair Ethiopian yibark

  4. በ እውንቱ ጸሐፊው መልስ መስጠቶው ያስመስግናል። ግን የሚያሳዘነው ልምን ስማችን ተነሳ በማለት የተጻፈ ይመስላል። ዲ ዳኒኢል ያለው ከቤተክህነት በዘምድ በአዝማድ በድጅ ጥናት በግቦ የሚደቡትን አባቶች ነው። እነዚያም በሰኢና በረሃ አቋርጠው የመጡትን እድሜያቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር የሚኖሩትን አላለም። በሰከነ አእምሮ አንብቡት። አሁንም ከአምላካችን ርዳታ ጋር በእየሩሳሌም ያለንን ገዳም ለመጠበቅ የዋህ አባቶቻችንም ያስፈልጉናል፣፤ ዘመኑ የሚፈልገውን ቤተክርስቲያንችንን በተለያየ መድረክ የሚወክሉ አባቶች ያስፈልጉናል።
    ሰላም ሁኑ

  5. selam le hulachn yehonena wede hasabe legeba !!! megmrya ye danieln hasab terdtachal new wyes edyaw lemen enenkalen new bezhe ayent eko mechwem yechy batkrstyan wedfet lethad atechlm !!!! ena edtrdawet keza lemnoruw abatoch yametaw hasab egye wekesa ayedelm memekakers medenew tefatuw setzrfuw lemn zerfach tebal belo erta terw ayedlm sew bayaye egzhabher yayal zerfach eyalkach ayedlm gen bega bate west awen yalew edzh ayent ayen yaweta labnt wesht eyseman eyayen selhon new !!! hulachnm egthabhern yamnamelk kehone begowen egye tenkoluwn mayet yelbenm !!! awenm d/n daniel teruw eyeta new yayew mestekakel yalebt beshatu mastekakel new egye lemne bate kerstyan yetades belho tsafe eyaluw memaget nege erasen ena chercheun yegodal teruw mehon leras new wedmoch

  6. እኔን የሚገርመኝ ዳንኤል ከተናገረው ይልቅ ለዳንኤል የአስተያየት ሽፋን የሚሰጡ ሰዎች ናቸው።
    ዳንኤል በሁለት መንገድ ትችቱን አቅርቧል።
    / በቤተክህነቱ በኩል ያለውን ለዴርሱልጣን ገዳም ትኩረት ያለመሰጠቱ ጉዳይ
    2/ በዴርሱልጣን ገዳም ባለው ማኅበር ላይ ያለውን የእውቀት ጉድለትና ስንፍና ገልጿል።
    የቤተክህነቱን ጉድለት ቤተክህነቱ መልስ ይስጥበት። ማሳሰቢያውን ደግሞ ሁሉም በኅብረት ያድርግ።
    በገዳማቱ ማኅበር ላይ የሰነዘረው ትችት ግን መሰረት የሌለውና ተጨባጩን ችግር ያላገናዘበ ስለሆነ ማስተካከያና ስህተቱ እንዲታረም ማስገንዘቢያ አስፈልጓል። ዳንኤልም የተሰማውን መፃፉ ፅፏል። ቁም ነገሩ ገዳሙ መብቱ የሚያስከብርበትን መንገድ ከመፈለግና እውነቱን ከማሳወቅ ረገድ የቱ ይሻላል ካልሆ የክስ መድረክ ስላይደለ ዳንኤልብ በተናጠል በመውደድ ሚዛናዊ እንዳያደርገን ማስተዋል ጥሩ ነው።

  7. Tsehafiw yeDn Danieln Eyita Yeteredaw Almeselegnim. Lemin Tenekahu Ayinet Menfes Yitayibetal. Tiru Tiru Tikomawechin Setitual. Tekebelu Enji

Comments are closed.

Share