ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫ

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።

በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራው ይህ ቡድን ከ March 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።  ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።

ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል።  የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣  በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱ መብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች እዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ለመረዳት ችለናል።

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእነ ሽመልስ ፉከራ ማግስት የ4 ኪሎና መቀሌ ሽር ጉድ ወዴት!? | Hiber Radio

አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።  ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።

በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽ ግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆች እንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

 

 

8 Comments

  1. የኛ ጀግና እግዝአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

  2. bemichot menor eyechale yehizibin bisot lealem lemasawek mesewatinetin keflo halafinetun yeteweta ewinetegna jegna. tarok ayiresahim.

  3. Convey our heartfelt gratitude to the Gov’t Switzerland and its people for not handing over Pilot Hailemedin to one of the worst dictatorial regime on this planet.
    God bless Switzerland and its people.

  4. Woyane’s prison is full of inocent Ethiopian I do not think they have more space for another one.

  5. melekethen balawkewm negroch hulu kemtasbew ena kemetetbkew belay w esebesebena aschegary selhonubeh yehen ayent wsane endetwesen adergohal wsaneh yetnkare yayebeger jegnent new .

Comments are closed.

Share