የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የፊታችን ሐሙስ ከቦታው ይነሳል

ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ከቦታው ሊነሳ ነው ስትል ስትዘግበው የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት የፊታችን ሃሙስ አሁን ከሚገኝበት ቦታ እንደሚነሳ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ማስታወቁን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ።

በአ.አ ከተማ እየተካሄደ ባለው የቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት  ምንክንያት ሐውልቱ የሚያርፍበት ቦታ የሚቆፈር በመሆኑ በጊዜያዊነት ይነሳል ሲል መንግስት ቢያስታውቅም ብዙዎች ግን ተመልሶ ቦታው ላይ ለመቀመጡ ጥርጣሬ እንዳላቸው አስተያየታቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ይገኛሉ።  የፊታችን ሐሙስ እንደሚነሳ የሚጠበቀው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጊቢ ውስጥ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

ባለሙያዎች የቀላል ባቡር ግንባታው ሐውልቱን በማይነካ መልኩ መካሄድ ይችል ነበር ሲሉ በተደጋጋሚ ቢገልጹም የመነሳቱ ነገር እርግጥ ሊሆን 48 ሰዓታት ቀርተውታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአማራ ክልል የወጡ አዳዲስ መረጃዎች! | ከይልቃል ከፋለ እና ጌታቸው ረዳ መተቃቀፍ ባሻገር!

4 Comments

Comments are closed.

Share