በአምሳል ወረታ
1. መግቢያ
ህወሓት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞብኛል ብሎ የሀሰት ትርክት በማሰራጨት ትግራይ የዓለም-አቀፉን ማህብረሰብ ድጋፍን እንድታገኝ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በቻለበት ሁኔታ፤ አማራ በእውኑ ላይ የደረሰበትን እና እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ሚዲያ እና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማድረግ ተስኖት የሚገባውን ትኩረት ማግኘት አልቻለም። የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ላለው ሰቆቃ ተሰሚነት ማጣቱ እንዲሁ ድንገተኛ ሳይሆን በሜዲያ፣ በማህበራዊ ንቅናቄ፣ ሀብት በማሰባሰብ እና አሳማኝ የዲፕሎማሲ ጥረትቶችን በማድረግ ረገድ ስትራቴጂያዊ ግቦችን አስቀምጦ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ ምክንያት ነው።
ይህንንን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀልበስ ሲባል አማራ መር ትርክቶችን በመቆጣጠር፣ ጠንካራ የሚዲያ መረቦችን በመገንባት፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመደገፍ፣ የገንዘብ ሀብቶችን ማሰባሰብ እና በዓለም-አቀፍ ማህበረሰብ ጋር በስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መንቀስቀስ ያስፈልጋል። ይህ ፅሁፍ ህወሓት በዚህ ረገድ ለምን ስኬታማ እንደነበረ እና የአማራ የህልውና ትግል ለዓለም ለማሳየት እንዴት ጠንካራ እና ውጤታማ ስትራቴጂ መተግበር እንሚቻል በዝርዝር ያስረዳል።
ትግሬዎች የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍ በማግኘት ረገድ ስኬታማ የነበሩበት መንገድ
ሀ. የሚዲያ ትርክትን በዓለም-አቀፍ ደረጃ በመቆጣጠር
- ህወሓት ከምዕራባውያን ጋር (በተለይም ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት) ጋር በነበረው የቀድሞ ግንኙነት ምክንያት ከምዕራባውያን ጋዜጠኞች ጋር ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ች ነበር።
ሀ. የሚዲያ ትርክትን በዓለም-አቀፍ ደረጃ በመቆጣጠር
- ህወሓት ከምዕራባውያን ጋር (በተለይም ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት) ጋር በነበረው የቀድሞ ግንኙነት ምክንያት ከምዕራባውያን ጋዜጠኞች ጋር ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ች ነበር።
- የምዕራባውያንን ሚዲያ ለመቆጣጠር የህዝብ ግንኙነት ስራ የሚሰሩ ድርጅቶችን እና የሎቢ ቡድኖችን ለመቅጠር ብዙ ሀብት ኢንቨስት አድርገዋል።
- የትግራይ ዳያስፖራ በማህበራዊ ሚዲያ የሐሰት መረጃዎችን ለማሰራጨት ከዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ጋር ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር ችለው ነበር።
ለ. ስሜት የሚነኩ ምስሎችን እና ታሪኮችን በመጠቀም
- ህወሓት ጠንካራ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ በምስል የተደገፉ ፕሮፓጋንዳዎችን በማቀነባበር የጥቃት ሰለባ የሆኑ ህፃናትን እና ሴቶችን በማሳየት የውጭው ዓለም ለእሱ እንዲወግን ሰርተዋል።
- ሐሰተኛ ጭፍጨፋዎችን በመፈብረክ፣ ንፁሃን የጥቃት ሰለባዎች እንደሆኑ በተጋነነ መልኩ በማሰራጨት፣ እና በትዊተር በከፍተኛ ሁኔታ ቅንጅት የፈጠሩ ሃሽታጎችን (ለምሳሌ #TigrayGenocide) በመጠቀም ዘመቻዎችን ማድረግ ችለዋል።
ሐ. ጠንካራ የዳያስፖራ አስተባባሪ ቡድኖችን መገንባት
- የትግራይ ዳያስፖራ በዋሽንግተን፣ ብራሰልስ እና ለንደን ከፍተኛ በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው የሎቢ ስራዎችን ሰርቷል።
- ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር የነበራቸውን የግል ግንኙነት በመጠቀም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጣልቃ ለመግባት እና ማዕቀብ ለመጣል ያስቻሉ ተግባራትን አድርገዋል።
መ. የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን መጠቀም
- ህወሓት በዋና ዋና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች (ለምሳሌ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች) ውስጥ ደጋፊዎቹን አስርጎ በማስገባት የተዛቡ ሪፖርቶች በየጊዜው እንዲወጡ ለማድረግ ችለዋል።
- የህወሓትን ወንጀሎች ችላ እያሉ በኢትዮጵያ ላይ ያተኮሩ የአንድ ወገን ሪፖርቶችን ብቻ ለማሳተም እንዲያስችላቸው ከፍተኛ ገንዘብ መድበው የየራሳቸውን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን መስርተዋል።
3. በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም አቀፍ ትኩረት ማግኘት ያልቻለው ለምንድን ነው?
ህወሓት ማድረግ ከቻለው አንፃር ሲታይ፤ አማራ እየየደረሰበት ያለውን ሰቆቃ ለዓለም ለማሳወቅ፣ ሚዲያን፣ ዲፕሎማሲን እና ዓለም-አቀፍ የድጋፍ ጥረቶችን በአግባቡ መጠቀም አልቻለም። ለዚህ ዋና ዋና ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ. በቂ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኝ የአማራ ሚዲያ መረብ አለመፈጠር
- የአማራን ጭፍጨፋ የሚመለከቱ ሪፖርቶችን በቋሚነት የሚዘግብ ምንም አይነት ዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫ ተቋም የለም።
- ልክ እንደ አልጀዚራ (ለአረቦች) ወይም እንደ ቢቢሲ ትግርኛ (ለትግራይ) የቆሙ ሚዲያዎች አይነት በአማራ ባለቤትነት ስር ያሉት ዓለም-አቀፍ የሚዲያ መረቦች የሉም።
- የአማራ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ዓለም-አቀፍ ታዳሚዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ በተበታተነ፣ ወጥነት በጎደላቸው እና ቅንጅት በጎደላቸው ዘገባዎች ላይ አብዛኛውን ትኩረታቸውን አድርገዋል።
ለ. የስትራቴጂክ ሎቢ እና የድጋፍ እጦት
- ህወሓት በዋሽንግተን፣ ብራሰልስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሎቢስቶችን ለመቅጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አውጥቶ ከሰራው አንፃር ሲታይ፣ የአማራ ተሳትፎ የተቀናጀ ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ማድረግ አልቻለም።
- አማራን ወክሎ ከምዕራባውያን ፖሊሲ አውጪዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር የሚችል ወሳኝ የአማራ የፖለቲካ ድርጅት የለም።
ሐ. ደካማ የማህበራዊ ሚዲያ እና የሃሽታግ ዘመቻዎች
- ህወሓት የሀሰት የዘር ማጥፋት ጥያቄዎቹን ለማሰራጨት ወጥ የሆነ እና በደንብ የተደራጀ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴን ሲጠቀም ቆይቷል፤ የአማራ ዘመቻዎች ግን አልፎ አልፎ የሚደረጉ እና ቅንጅት የሚጎድላቸው ናቸው።
- አብዛኛዎቹ የአማራ ተወላጆች በማህበራዊ ሚዲያው ጦርነት ውስጥ በትጋት ለመሳተፍ ያመነታሉ፣ በዚህ ምክንያት አማራ-ጠል ሃይሎች የማህበራዊ ሚዲያ ትርክቱን እንዲቆጣጠሩ ዕድሉ ተፈጥሮላቸዋል።
መ. መንግስታት እና የዓለም-አቀፉ ማህበረሰብ በአማራ ላይ የሚፈፅሙት አድልዎ
- አብዛኛዎቹ የምዕራባውያን መንግስታት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ዛሬም ድረስ አማራን የኢትዮጵያ ገዥ አድርገው ይመለከቱታል፣ በዚህ ምክንያት አማራ እየደረሰበት ላለው ሰቆቃ የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ ሊሆን ችሏል።
- የኢትዮጵያ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያጋልጡ ጋዜጠኞችን እና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን በማሰር የአማራን ድምፆች ላይ አፈና ይፈፅማል።
✔ 4. መፍትሔዎች፡ ለአማራ ሚዲያዎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና ዲፕሎማሲ ተግባራት
✔ በአማራ ላይየሚፈፀመውን አፈና አሸንፎ ለመውጣት እና በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም ለማሳወቅ፤ ሁሉን አቀፍ እና አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያስገኝ ስልት ያስፈልጋል። ይህ አራት ዋና ዋና የአፈፃፀም መንገዶችን መቀየስ የሚጠይቅ ሲሆን እነሱም ሚዲያ፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የሀብት ማሰባሰብ እና ዲፕሎማሲ ናቸው።
ሀ. ዓለም አቀፍ የአማራ ሚዲያ አውታረ መረብ መገንባት
- ዓለም አቀፍ የአማራ ሚዲያ እና የዜና ተቋም መፍጠር
- የአማራን ጉዳዮች ቀጣይነት ያለው ሽፋን ለመስጠት የሚችል እና በቂ የገንዘብ ድጋፍ ያለው ልክ እንደ ትግራይ ሚዲያ ሀውስ (TMH) አይነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚዲያ መረብ መፈጠር አለበት።
- በአማራ ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት የሚያሳዩ ዘጋቢ ፊልሞችን፣ ሰበር ዜናዎችን፣ ቃለ መጠይቆችን እና የሰብአዊ መብት ሪፖርቶችን የሚያካትቱ ጠንካራ ይዘቶችን ማዘጋጀት መቻል አለበት።
- የአማራን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች መደገፍ እና ማስፋፋት
- #StopAmharaGenocideNow (የአማራው የዘር ማጥፋት አሁኑኑ ይቁም) አይነት ይዘት ያላቸው ዓለም አቀፍ የሃሽታግ ዘመቻዎችን ለማደራጀት እና ለመቆጣጠር ቁርጠኛ የሆነ የአማራ ዲጂታል ተሟጋቾች ቡድን መቋቋም አለበት።
- በጅምላ ጭፍጨፋዎች፣ በጦር ወንጀሎች እና በመፈናቀል ላይ ያተኮሩ ዕለታዊ መረጃዎች ትዊተርን፣ ፌስቡክን እና ዩቲዩብን ማጥለቅለቅ እንዲቻል በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።
- አማራ-ጠል ፕሮፓጋንዳዎችን ማጋለጥ
- የህወሓትን እና የኦሮሙማን ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋለጥ እና ለማስተባበል የሚያስችል የሀቅ ማረጋገጫ መድረክ መፈጠር አለበት።
- የአማራ ሚዲያዎች የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን፣ የሂዩማን ራይትስ ዎች እና የአልጀዚራን አድሎአዊ ዘገባዎችን በትጋት መቃወምና መጋፈጥ አለባቸው።
ለ. የአማራ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን እና እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ማብቃት
- የአማራ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን ማጠናከር እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ
- በዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን እና በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ ጥናታዊ ሪፖርቶችን ለህትመት የሚያበቁ የአማራ የሰብአዊ መብት ድርጅት መቋቋም አለበት።
- እነዚህ ሪፖርቶች የውጭ መንግስታት ላይ ጫና መፍጠር እንዲችሉ ከዋና ዋና ዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በጋራ ሊሰሩ ይገባል።
- የአማራን የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን ማሰልጠን እና መደገፍ
- አማራዎች በምዕራባውያን አካዳሚክ እና ፖለቲካዊ ክበቦች ውስጥ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር በዲጂታል ጦርነት ዘርፍ በብቃት መታገል እንዲችሉ ማሰልጠን ያሰፈልጋል።
- ታዋቂ የአማራ ግለሰቦች በአማራ ላይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ለማጋለጥ በዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሚዲያዎች ላይ ንግግር እንዲያደርጉ መድረኮችን መፍጠር እና ማመቻቸት ያስፈልጋል።
ሐ. የአማራን የአድቮኬሲ ጥረቶች የሚደግፉ የፋይናንስ መረቦችን መመስረት
- ለሎቢ ስራ የሚውል የአማራ የፖለቲካ ፈንድ ማቋቋም
- በዳያስፖራው ማህበረሰብ የሚገኙ አማራዎች በዋሽንግተን፣ ብራሰልስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሎቢስቶችን ለመቅጠር የተማከለ የፖለቲካ ፈንድ ውስጥ መዋጮ ማድረግ አለባቸው።
- ሎቢስቶች የአማራውን የዘር ማጥፋት ለማጋለጥ ከምዕራባውያን ህግ አውጪዎች፣ ጋዜጠኞች እና ፖሊሲ አውጪዎች ጋር እንዲገናኙ ማድረግ ያስፈልጋል።
- የተፈናቀሉ እና ከፕፍጨፋ የተረፉትን አማራዎች መደገፍ
- በአማራ ላይ እየተፈፀመ ካለው የጅምላ ጭፍጨፋ የተረፉትን እና ተጎጂዎችን ለማስፈር፣ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራትን ለማከናወን የገንዘብ ድጋፍ መረብ መፈጠር አለበት።
መ. የዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማጠናከር
- የምዕራባውያን መንግስታት የአማራውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እውቅና እንዲሰጡ ግፊት ማድረግ
- የአማራ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የአሜሪካ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአማራዎች ላይ የሚፈፀሙ የጅምላ ግድያዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን ይፋዊ እውቅና እንዲሰጡ መጠየቅ እና ጫና መፍጠር አለባቸው።
- በጅምላ ጭፍጨፋው ላይ በተሳተፉ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ እንዲጣል መጠየቅ እና ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል።
- የክስ መዝገቦችን አደራጅቶ ወደ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ማቅረብ
- የአማራ ጠበቆች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል ለመክሰስ የሚያስችል ማስረጃ ማሰባሰብ እና ማደራጀት አለባቸው።
- ከሌሎች የተጨቆኑ ቡድኖች ጋር መተባበር
- በብልፅግና መንግስት ላይ የሚደረገውን ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ለማጠናከር ኦሮሞ ያልሆኑ አናሳ ብሄረሰቦችንና በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሌሎች የተገለሉ ቡድኖች ጋር ጥምረት መፍጠር ያስፈልጋል።
ማጠቃለያ፡ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው
የአማራ ህዝብ በስርዓቱ እየተጨፈጨፈ ባለበት በዚህ ወቅት በዝምታ ሳይደራጅ እና ለችግሩ ምላሽ ሳይሰጥ በዝምታ መቀጠል አይቻልም። በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ለማጋለጥ እና ለማስቆም ቀጣይነት ያለው፣ በቂ የገንዘብ ድጋፍ ያለው እና በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀ ሁሉንተናዊ ዘመቻ ማድረግ በእጅጉ ያስፈልጋል።
ይህንን ለማሳካት የሚከተሉትን መንገዶች ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፦
- ጠንካራ የአማራ ሚዲያ አውታረ መረብ መገንባት ያስፈልጋል።
- ውጤታማ የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄን መፍጠር
- ሎቢ ለማድረግ እና በፖለቲካዊ ተፅዕኖ ኢንቨስት ለማድረግ አስፈላጊውን ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ
- ወንጀለኞችን በአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ተጠያቂእንዲሆኑ አበክሮ መስራት።
የአማራ ህዝብ የመረጃ ጦርነቱን ማሸነፍ፣ ፍትህን ማረጋገጥ እና በመጪዎቹ ጊዚያት ሊፈፀሙ የሚችሉ የጅምላ ጭፍጨፋዎች መከላከል ይችላል። ይሄንን ለማድረግ ጊዜው ከማለፉ በፊት አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ያለው ጊዜው አሁን ነው።