February 27, 2023
5 mins read

የብልጽግና መንግስት ሆይ! 

 If you can't convince them, confuse them
If you can’t convince them, confuse them
  1. የፌደራል መንግስትም የክልል አስተዳደር፣ የከተማ አስተዳደር ተጠያቂነት፣ ግልጽነት ጠፍተው፣ ሕዝብን ያማረሩ ጉዳዮች በየደረጃው ተበራክተው፣ በዲያስፓራ የሚገኘውን ኢትዮጵያውያን ለማማለል፣ ለመከፋፈል፣ ብሎም  የመንግስት ደጋፊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ መመሪያ ለኤምባሲዎች ማስተላለፉ በሀገራችን ለሚፈጠሩና እየተፈጠሩ ለሚገኙ በርካታ ግዙፍ ችግሮች ፣ የመብቶች ጥሰቶች መፍትሄ አይሆንም። ለህወሃትም አልፈየደም ።
  2. በዓለም ዙሪያ የሚገኘው ዲያስፓራ አብዛኛው ምንም ጥቅም ሳይጠይቅ፣ከመንግሥት ዲፕሎማቶችበይበልጥ ሳይቀር ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ትንቅንቅ ያደረገው አደጋ ላይ የወደቀውን ሀገሩን ለመታደግ እንጂ ጥቅም ፈላጊ ቢሆን በህወሃት ዘመን ያደርገው ነበር:፡
  3. በውጭ አለም የሚገኘው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መንግሥትን የደገፉት የለውጡ ጅማሮ ሀገርን ይታደግ ይሆናል በሚል ተስፋ: በጦርነቱም ሙሉ ድጋፍ የሰጠውም የሀገር ህልውና ከፍተኛ አደጋ ወድቆአል በሚል ጭንቀት፣ ካለፉ ስርአቶች የተወረሱና አዲስ የመጡም  የህገራችንን ውስብስብ ችግሮችና ችግሮቹን የደራረቡ ገፊ ምክነያቶች ስረ- ምክነያቶች  ብዙ ስራ ይጠይቃሉ ፣ መንግስት ግዜና ቦታ ያስፈልገዋል በሚል በመረዳት እንጂ ኢፍታሃዊ ህሊናን የሚያሳምሙ ደባወች ሕዝብ ላይ እየተፈጸሙ እንደሆነ ሳይታዘብ ቀርቶ አይደለም።
  4. ህገ ወጥነት፣ ኢ-ፍትሃዊነትን ኢ-ሰበአዊነት (ለምሳሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከአስር ሺ ዜጎች በላይ  ማፈናቀል፥ በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ነዋሪዎች ፣ ህሙማንን ጨምሮ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከል፣ ዜጎች የአጼ ሚኒልክን ምስል የያዙ ቲ-ሸርቶች ሸጣችሁ፣ በሱቆች ሰቀላችሁ በሚል ማስፈራራት፣ ሱቆችን ማሸግ ፣ ወዘተ)፣ ቅጥ ያጣ ሌብነት፣ የስልጣን ብልግና ወዘተ እንዲሰፍን በሩን ከፍተህ ስድ ለቀቅህ።
  5. በሁሉም ብሄረሰቦች ፣ በነዋሪዎቿ ላብና ጥሪት የተገነባችው የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እንደዘረኛ ወራሪ በጉልበት ወደ አንድ ክልል ለመሰልቀጥ፣ ነዋሪዎች ድምጽ አልባ ተደረጉ  ፣ ማሸማቅቅ የእለት ተእለት ክስተት ሆነ ፣ መብትና ነጻነት መግፈፍ ፣ ቅጥ ያጣ ስግብግብነት ተስፋፋ።
  6. ይህን ሁሉ ግፍ እየተቀበለም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለመደው ትእግስቱና አስተዋይነቱ ከዛሬ ነገ የተሻለ ይመጣል መንግሥት ጩኸታችን ለቅሶአችንና ምሬታችን ይሰማል እያለ በጸሎትና በተስፋ እየተጠባበቀ ነበር። ግን መንግሥት ማዳመጥ አልፈለገም! አሁንም ፊቱን አዙሮ ልቡን ከፍቶ ግፉን ካላየና ሕዝቡን እያዳመጠ አቅጣጫውን ካላስተካከለ በእራሱም ሆነ በሀገራችን ላይ አደገኛ መዘዝ ያመጣል::
  7. መንግስት ሆይ! ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎች መልስ ስጥ፣ የመረጠህንም ሆነ ያልመረጠህን ሕዝብ በእኩል ዐይን እይ: የህግ የበላይነትን አክብርና አስከብር፣ ሕዝብን በፍትህና በእኩልነት አገልግል።
  8. ስለዚህ የብልጽግና መንግሥት ሕዝብን እንዲሰማ እንጠይቃለን! ከአድዋ ድል ቅድም አያቶቻችን አስተውሎ የምንማረው ብዙ አለ! ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!

Neamin Zeleke

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop