https://youtu.be/pRbWY7395Jw
እርግጥ ነው የደፋር አርቲስቶቹ መልእክት ያለውን የገማ የገለማ ዃላ ቀር የጎሰኞች ስርዓትና የሚመራበትን አገር አፍራሽ ህዝብ አጫራሽ የጥፋት ሰነድ ይወገድና አገራችን በአንድነትና በነጻነት ህዝብም በእኩልነትና በህብረት ይኑር ነው እነዚህ ደፋሮች በአገር ውስጥ ለዚያውም በአዲስ አበባ ተቃምጠው ይህንን የመሰለ ጀግንነትን የተላበሰ ትግል በሙያቸው ሲያደርጉ ምሁር ተብዬው አድር ባይ በሽህ ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሆኖ ሥርዓቱን ለማዳን በኤኮኖሚ፣በፖለቲካ፣አማካሪነትና በገንዘብ ተባባሪ መሆኑ ያሳዝናል።የትኛው ምሁር እንደሆነ ያዬንበት ጊዜ ነው።ህዝባዊ ትግሉ ተሳክቶ ሥርዓቱ ሲገረሰስ የስርዓቱ አዘጥዛጭ ጎራ ምን ይውጠው ይሆን?ሁሉም የስራውን ያገኛል፣እያምታቱ መኖር አይቻልም።ማን ምን እንደሰራ ተመዝግቧል።
Agere Addis