ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) በአማራው ላይ የሚያደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክርቤት በጥብቅ ያወግዛል

ቀን፡ መጋቢት 29፤ 2013

ህወሃት ከመጀመሪያውም አላማ አድርጎ የተነሳውን የገዢውን መደብ ማጥፋት በሚል ሽፋን አማራውን ለማጥፋት መሆኑ
የራሳቸው ፕሮግራም ይገልጻል :: ዛሬም ከሃያ ሁለት አመት በሗላ አላማውን እግቡ ለማድረስ በአማራው ላይ በልማት ሰበብ
የሚያደርገው ትእቢት የተሞላበት ሰቆቃ በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል::
ከዚህ በፊት በደቡብ ክልልና በሌሎቹም የተለያዩ ክልሎች በተደጋጋሚ የአማራ ተወላጆችን በመግደልና ከቀያቸዉ በማፈናቀል
ዜጎች በኢዮጵያዊነታቸዉ በሀገራቸዉ የትም ቦታ የመኖር መብታቸዉን በመጻረርና በመንፈግ የፈጸመዉ ፍጹም ኢሰብአዊነት
የጎደለዉ ዘርን የማጥፋት ወንጀል ሳያንሰዉ፡ ሰሞኑን 59 ኢትዮጵያውያን ከቤኒሻንጉል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ተብለዉ
ያለፍላጎታቸዉ በሀይል ለዘመናት ሲኖሩበት ከነበሩባቸዉ ቦታዎች በማፈናቀል ወዳልታወቀ ቦታ ሲወሰዱ ተሳፍረዉበት
የነበረዉ መኪና ተገልብጦ ህይወታቸው በአሰቃቂና አጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ማለፉን ሰምተናል።
ከዚህ በፊት በአማራ ወገኖቻችን ላይ ስርአቱና የስርአቱ ሀላፊዎች የፈፀሙት በህግ የሚያስጠይቃቸዉ አጸያፊ ተግባራት እንዳሉ
እያሉ ሰሞኑን በደረሰዉ አደጋ ሴቶች: ህጻናት: እርጉዞች: አዛውንት ሳይባል ህይወታቸው በማለፉ የተሰማንን እጅግ መራር ሀዘን
እየገለጽን፤ የእያንዳንዱን መስእዋት የከፈለዉን ወገን ደም ለመታደግ የስርአቱን ባለስልጣናት በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት በዘር
ማጥፋት ወንጀል የምንፋረድ መሆኑንና በዚህ አጸያፊ ተግባር የተሳተፉት ግለሰቦችና የስርአቱ መሪዎች ፍርድ እስኪያገኙ ድረስ
የማንወስደዉ የትግል እንቅስቃሴና የማንፈነቅለዉ ድንጋይ የማይኖር መሆኑን አጽንኦት እናረጋግጣለን።
በአሁኑ ወቅት በአማራዉ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍም ከዚህ በፊት በኦሮሞ፤ አፋር፤ ደቡብና፤ ዓኙዋክ ወገኖቻችንም ላይ የደረሰ
በመሆኑ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሀት/ኢህአዴግ አኩይ የከፋፋይነት ተግባር መቼም ሳይከፋፈል እንዲያዉም ከመቼዉም
ጊዜ በላይ የህዝቡ አንድነት እየተረጋገጠ መጥቷል።
በዚሁም አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማናቸዉም የኢትዮጵያ ግዛት የመኖርና የመስራት መብት እንዳለዉና ይህም
እስኪረጋገጥ ድረስ ትግላችንን በቁርጠኝነት የምንቀጥል መሆኑን ለምናከብረዉ ህዝባችን እያረጋረጥን፡ የመላዉን የኢትዮጵያ
ህዝብ ብሎም የአማራዉን ህዝብ መብት ለማረጋገጥ ለሚንቀሳቀሱ ማናቸዉም ድርጅቶችና ሀይሎች ያለንን ከበሬታና
የማያቋርጥ ድጋፍ በድጋሚ እናረጋግጣን። በተጨማሪም ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎችና ድርጅቶች በአንድነት የሀገራችን ጠላት
የሆነዉን ስርአት ለማስወገድ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ለጋራ ትግል በቁርጠኝነት እንድንነሳ ጥሪ እናቀርባለን።
አንድ ህዝብ፤ አንድ ሀገር!!!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ሊፈቱ ይሆን?

1 Comment

Comments are closed.

Share