ሽብርተኛው ህወሃት ለሚያደርገው ትንኮሳ የመከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች እርምጃ የሚወስዱበት አቅጣጫ ተቀመጠ

ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ለሚያደርገው ትንኮሳ የመከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች በጥናት ላይ ተመስርተው እርምጃ የሚወስዱበት አቅጣጫ ተቀመጠ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራው የፌደራል ጸጥታ ምክር ቤትና የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች ውይይት በሀገራዊ ጸጥታ ሁኔታ ላይ የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ትኩረት አድርጓል።

በምክክሩም ሀገሪቱ አሁን ያለችበት አንጻራዊ ሰላምና ጸጥታን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ማስቆምና በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠሩ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን ቅርጽ ማስያዝ እንደሚገባ ከስምምነት ተደርሷል።

በተለይ ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን የሚያደርገውን ትንኮሳን ተከትሎ እርምጃዎች የሚወሰድበት አግባብ አቅጣጫ ተቀምጦለታል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሀገሪቱ ቀጣይ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች ከወዲሁ መስመር የማስያዝና የማስተካካያ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አንስተዋል።

ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ የኮንትሮባንድና መሰል እንቅስቃሴዎች የተገመገሙ ሲሆን፥ በውስጥ ያሉ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ ቀጠናው ላይ ሰላምን ማስጠበቅ እና ሀገራዊ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ብለዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው የአሸባሪ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በመገምግም እርምጃ መውስድ የሚቻልበት ሁኔታን ከመመልከት ባለፈ አሸባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድን የተመለከተ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።

የተቀመጡ አቅጣጫዎችም ሆነ የተደረሰባቸው ስምምነቶችን የፌደራልም ሆነ የክልል የጸጥታ አካላትና አስተዳደሮች በየደረጃው ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል።

Prosperity Party – ብልፅግና

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰበር ዜና፡ ጳጳሳት የፓትርያርክ ምርጫው ወደ ግንቦት እንዲዛወር ጥያቄ አቀረቡ

1 Comment

  1. This is really a very stupid political game being played by the very faction of crime infested EPRDF that controls the very deadly palace politics simply by getting rid of the dominant power of its brain- father (TPLF) . This is a very cowardice and brutal political faction of the very backward and mutually distractive political system of ethnocentrism . This faction has no any sense of shame or moral value at all!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share