25ቱ ለኢትዮጲያ ብሄራዊ ውይይት አመቻች ኮሚሽን ኮሚሽነርነት አብላጫ ድምፅ ያገኙ እጩዎች

1-ዶ/ር ሰሚር ዩሱፍ
2-ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም (በኢትዮጲያ የኦሮሚያ መጅሊስ ፕሬዘደንትና የሀገር ሽማግሌ)
3-መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ(ከኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤ/ህ መምህር)
4-ፕ/ር ሙሐመድ ሐቢብ
5-አቶ ለማ መገርሳ
6-አቶ ሐቢብ ሙሀመድ ያዮ(የቀድሞ የአሰብ ራስገዝ የመከላከያ አስተዳድር መምሪያ ኋላፊ የሱልጧን ሙሀመድ ያዮ ልጅ)
7-ዶ/ር አሚር አማን-(የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር)
8-ረ/ፕ አደም ካሚል
9-አባገዳ በየነ ሰንበቶ
10-የትነበርሽ ንጉሴ(በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት)
11-ጠበቃ ተማም አባቡልጉ
12-አቶ አብዱልዋሲዕ አመንዲድ(የዩኒቨርስቲ መምህርና የተለያዩ ኮሌጆችና ት/ቤ ፕሬዝደንት)
13-አትሌት ደራርቱ ቱሉ
14-አቶ ዑመር አብዱረዛቅ(የሕዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ አባል)
15-አቶ ጀማል አህመድ (የሜድሮክ ዋና ስራ አስፈጻሚ)
16-ዶ/ር ፋዒዝ ሙሀመድ ቃሲም(የዩኒቨርስቲ መምህር፣ ተመራማሪና አሰልጣኝ)
17-አቶ መሕዲ አህመድ ገዲድ(በጃፓን፣ በኢንዶኖዢያ፣ ፊሊፒንስ አምባሳደር፤ የዩኒቨርስቲ መምህር፣ በአፍሪካ የውጪ ጉዳይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አማካሪ…)
18-ወ/ሮ መዓዛ ብሩ
19- ፕ/ር ያዕቆም ኃ/ማ
20-ሐጅ ሁሴን ላለምዳ ሀምዛ (በተለያዩ ጊዜያት የሀገር ሽማግሌ በመሆን ያገለገሉ።)
21-ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
22- አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ
23-አርቲስት አበበ ባልቻ
24-ጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር
25-አቶ በለጠ ባሹ(የሀገር ሽማግሌ)
●የኢትዮጲያ ብሄራዊ ውይይት አመቻች ሀገራዊ ውይይቶች እና የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች እጩዎች ናቸው ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ፊት ለፊት: ሳዲቅ አይመድ ይጠይቃል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይመልሳሉ | Video

3 Comments

  1. ለማ መገርሳ: ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ አበበ ባልቻእንዲህ ያለ ታላቅ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ባይገቡ መልካም ነበር ዜጋን በማሳረድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ አድርገዋልና በአንጻሩ ሀላፊነት የሚሰማቸው ሀጅ ሙፍቲ ኡመር ፣መምህር ታየ ቢካተቱበት ታማኝነትን ያገኛል። አህመዲን ጀበል ግን መንግስት ባያባርረው እራሱን ያባርራል የሚል እምነት ይኖራል የሞራል ሰው ከሆነ።

  2. ጎበዝ ከ25ቱ 15ቱ እስላሞች መሆናቸው ሀሜት ላይ ይጥላል ባላንስም አያስጠብቅም ደብለቅ አድርጉበት ሀዝቡን አትናቁት።አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቱባ ቱባ የሚያህሉ ለአለም የሚበቁ ምሁራን አሉን አለፍ ሲል ደግሞ እንደነ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፤ዶር በፍቃዱ በቀለ ከጀርመን፤ፕሮፌሰር ሐይሌ ላሬቦ ከወደ አሜሪካ፤አቶ ኪዳኔ አለማየሁን የመሰሉ ሀገር ወዳድነትን ከእውቀት ጋር ያዋሃዱ ዜጎች እያሉን እንደ አህመዲን ጀበል አይነት እይታው በአርብ መንፈስ የተቃኘ እንዲህ ያለ ሃላፊነት የሚጠይቅ ስራ ላይ ማምጣት ምን ይሉታል? እስላምም ሁነው እንደ ሐጂ ሙፍቲ ኡመር የመሳስሉ ቃላቸው የታመነ ነገሮችን ሁሉ በታላቅ ጥበብ ትህትና ማስተዋል የሚመለከቱ መሀል ተገኝተው በዘርና በአረባዊ ቅኝት የተቃኘውን ሀይ ቢሉት መልካም ነበር። ካልሆነም ነገሩ ሁሉ ግራ የተጋባ በመሆኑ ስብሃት ነጋ ሊቀ መንበር ሁኖ ያወያያቸው ነጻ ነህ ተብሎ ተለቅቆ የለ። ስብሃት ከተለቀቅ ኢትዮጵያ እስር ቤት ምን ይሰራላታል ሁሉን መዝጋት ነው።

  3. ነቢዩ እና ቢረጋ አስተያየታችሁን ማሰማታችሁ ባልከፋ። ችግሩ ይኸ እንጂ ይኸ አይሆንም ማለታችሁ ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ነች! ያልተረዳችሁት አንድ ነገር፣ ምሑራን ሁሉ እኲል ብቃት የላቸውም። ኮሚሽኑ ካቀረባቸው ከብዙ እጩዎች መሓል 25ቶቹ ተጣርተው የተገኙ ናቸው። መንግሥት የያንዳንዱን ዜጋ አስተያየት እየዞረ አይጠይቅም። አሠራር እንደዚያ አይደለምና። እናንተ አልተስማማንም ያላችሁትን ግለ ሰብ ሌላው ይስማማኛል ይላል። አንድ ግልጽ የሆነ ጒዳይ እጩዎቹ ኢትዮጵያን ስለ መገነጣጠል እንደማይወያዩ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share