በትግራይ የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ሁለት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠየቁ

በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ነፃነት ፓርቲዎች ህወሓት በሥልጣን እንዲቀጥል የሚያስችል የሕግ አግባብ የለም ባይ ናቸዉ። ፓርቲዎቹ በትግራይ ያለዉ የህወሓት መንግሥት፤ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማስያዊ ዉድቀት አጋጥሞታል፤ በትግራይ መንግሥት ላይ ያለዉ ከበባ እና መዘጋምት ተጠናክሮ ቀጥሎአል፤ ህዝባችን አደጋ ላይ ነዉ ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ትግል «ዲሞክራሲያዊት እና ሉዓላዊት ትግራይን» እዉን ማድረግ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረግ የርዕዮተ አለም ፍጥጫ አይደለምም ሲሉ በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል። የሁለቱን የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ያለዉ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ «ህወሓት» የሰጠዉ መልስ እስካሁን አልተሰማም።
–«ሊንክ ኢትዮጵያ» የተባለ ድርጅት በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ትምህርታቸውን ላቋረጡ ተማሪዎች እገዛ የሚሆን የትምህርትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
–በሱዳን ከሦስት ወራት በፊት የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬ ዳግም ለተቃዉሞ አደባባይ ወጡ
–በአሸባሪነት ተከሳ ቱርክ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ የነበረችዉ የጀርመናዊው ጋዜጠኛ የፍርድ ሂደት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተሰማ። የ 37 ዓመትዋ ትዉልደ ኩርዳዊት ጀርመናዊት ጋዜጠኛ መሣሌ ቶሉ ከክስ ነፃ መሆንዋ የተነገረዉ ከአራት ዓመት ከስምንት ወር እና ከ ሃያ ቀናት የክስ ሂደት በኋላ ነዉ።
–የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አቡ ዳቢ ዋና የዘይት ማከማቻ ቦታ አቅራቢያ በነዳጅ ታንኮች ላይ ጥቃት ደርሶ የሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  የ“ማዕበል ጋላቢ” መጽሐፍ ግምገማ ክፍል 1 - ገምጋሚ መንግስቱ ሞሴ (ዶ/ር)

2 Comments

  1. እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬ ነው።
    ህወሓት ከሞከረው ውጭ “ሳልሳዊ” ይባል ሌላ ስም ይሰጠው፣ ምን የተለየ አሳብ አለው?
    የሚገርመው ዘሐበሻ ሰሞኑን ጨርሶ የህወሓት መነኻርያ መሆኑ ነው።

  2. ድልድይ እያፈረሱ የሽግግር መንግስት ብሎ ነገር የለም። እንዲያውም እንዲህ አይነቱ ወሬ የትግራይን ህዝብ እርስ በእርስ እንዲጋደል የሚጋብዝ የእብደት ሃሳብ ነው። እንደዚህ ያለ ሃሳብ ከሩቅና ከቅርብ ሆነው የሚያቀርቡ የትግራይ ተወላጆች ሁሉ እብዶች ናቸው። በነደደ እሳት ላይ ጭማሪ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ነው። የትግራይን ህዝብ ከ 1 ለ 5 እስራቱ የሚፈታ፤ ለዘመናት በስሙ የነገደበትንና አሁን ደግሞ ያለ ምንም ሂሳብ ልጆቹን የሚያስጨርስበትን ወያኔን ከስሩ የሚያመክን የጋራ የሆነ እይታ ያለው ቡድን በዚያ ምድር ሊበቅል ይገባል። ያ ቡድን ግን በጊዜው የትግራይ ህዝብ የነጻ መርጫ እንዲያደርግ የሚፈቅድና የሚያመቻች እንጂ አዲስ አለቃ መሆን የለበትም። ለዚያም ነው አሁን በየምድሩ የተበተኑ ወያኔን የሚደግፉ የትግራይ ልጆችን ከምር የምሟገተው፡፡ የህይወት ስንክ ሳር እንዴት ሁሌ ያዘው ጥለፈው፤ በለው ግደለው እያለሁ መኖር ብቻ ይሆናል? የህይወት ጥሪ ጀጋኑ ለመባል ብቻ አይደለም። ከዚያ የዘለለ እንጂ። የትግራይ ህዝብ በራሱ የሚተማመን፤ ሃገርና ሃይማኖቱን አክባሪ ነው። ግን በወያኔ ሴራ አፍ፤ እጅና እግሩ ተቀፍድዶ ማሰቡን ተነጥቋል። ከወያኔ ወረንጦ ሃሳብ አምልጦ በራሱ በግልም ሆነ በህበረት አስቦ መኖር እስካልቻለ ድረስ በነጻነት ስም በምድራችን ላይ እንደ አሸን የሚፈለፈሉት የፓለቲካ ድርጅቶች ሁሉ አሻሮዎች ናቸው። በዘመናት መካከል አይተናል ነጻ አውጪ ተብለው ባርነትን ሲያጎናጽፉን። ያለፈውን መከራ እያወሩ እነርሱ ዞረው ተመልሰው ሰቆቃና መከራ አዝናቢዎች ሲሆኑ። ስለሆነም የትግራይ ህዝብ አሁን የሚያስፈልገው የሽግግር መንግስት ሳይሆን የሚራመድበት ጎዳናና ድልድይ ተጠግኖ ወያኔ ጠላት እያለ ከሚፈርጀው ወገኑ ጋርና ከጎረቤት ሃገሮች ጋር ሰላም አግኝቶ መኖር ነው። ለዚህ ደግሞ የወያኔ መክሰምና አሁንም በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ የሽግግር መንግስት እያሉ የሚሸቅቡት የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ከወያኔ ጋር አብረው ሲቀበሩ ብቻ ነው። ህዝቡ ራሱን መምራት ይችላል። ተውት ይተንፍስ። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share