ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚልህን “ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ” በለው – ዮሐንስ ቧያለው

ፋኖ የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሬ ሽጦ ነፍጥ ያነሳ ከህዝብ አብራክ የተፈጠረ አራሽ፤ ተኳሽ፤ ቀዳሽ የነፃነት ታጋይ ነው። በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና ጠንቅ ሲቀለበስ ፋኖ ነፍጠኛው ሰላማዊ ህዝብ ሆኖ ይኖራል።
NB፦ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።
———————-
መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።
መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።
ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።
በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።
ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል። ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
አሚኮ
ተጨማሪ ያንብቡ:  አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የትግራይ ሴቶች እና ሕጻናትን ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ለጦርነት እየማገደ መሆኑን በአፋር በኩል በመከላከያ ሠራዊት የተማረኩ የቡድኑ ታጣቂዎች ተናገሩ

3 Comments

  1. ዮሀንስ ቧያለው እርግጠኛ ነህ? ፋኖን አሳምነውን አስመልክተህ የተናገርከው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው አሁን ባልከው አቋምህ ከጸናህ መልካም ነው በረከትና ሽመልስ የሚጋልቡህ ከሆነም የጊዜ ጉዳይ ነው እናያለን

  2. ትጥቁን መጀመሪያ መፍታት ያለበት የትግሬው ሕዝብ ነው፤ፋሺሽቱ ወያኔ ግን በግድ እንዲፈታ ካልተደረገ፣መንግስት በኃይል የፓርላማውን ውሳኔ የማስፈጸም ግዴታ አልተወጣምና ሊጠየቅ ይገባል።

  3. ዮሀንስ ያልከው አልተዋጠልኝም አለምነህ መኮንና አገኘሁ ተሻገር ጋር እየተሞዳሞድክ በረከት ስምንን ምን ልታዘዝ እያልክ አብይን ምን ያልፈጸምነው አለ እያልክ አማራው ላይ የሲኦል በር ተበርግዶ ለ 30 አመት ሲዘንብበት ድምጽህን ሳታሰማ ዛሬ ብያለሁ ለማለት ይህችን ብትልክ ግምት አይገባም። አንድ መንገድ አለ እንደ አሳምነው ጽጌ ስማችሁ ከመቃብር በላይ እንዲውል ስለምታውቀው ዝርዝሩ አያስፈልግም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share