የአማራና አፋር ተጎራባች ወንድማማቾች የሰላም መድረክ በቀወት ወረዳ ኩሬ በረት ቀበሌ በመካሄድ ላይ ነው!

የአንድ እናት ሀገራቸውን ህመም በጋራ የታመሙ፣በፍቅርና ህብረት በጋራ ተቀናጅተው ሀገር አፍራሽ አሸባሪዎችን በጋራ የቀጡት በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የራሳ ማህበረሰብና የአፋር ወንድሞቻቸው የጋራ ምክክር በቀወት ወረዳ ኩሬ በረት ቀበሌ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደአማኑኤል፣ የአፋር ዞን 5 ሀረር ራሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ማቴ፣ የሰሙ ሮቢ ገለአሎ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሀሰን ሀንድዬ እንዲሁም የቀወት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ ሸዋዬን ጨምሮ በርካታ አመራሮችና ከሁለቱም ህዝብ የተውጣጡ በርካታ ተወካዮች ታድመዋል።
የሁለቱ ወንድማማቾች የጋራ የሰላም መድረክ ከዚህ በፊት በአፋር ክልል ዞን 5 ሰሙሮቢ ገለአሎ ወረዳ መካሄዱ ይታወሳል።
በዝርዝር ዘገባ የምንመለስበት ይሆናል።
መረጃው የሰሜን ሽዋ ዞን የዲጂታልና የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share