ባልደራስ፤ የፌደራል መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” አለ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ማዕከላዊ መንግስት ህወሓትን “ያለበት ድረስ ሂዶ ማጥፋት አለበት” ሲል አስታወቀ። ፓርቲው የኢትዮጵያ መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱን ባለበት ጸንቶ እንዲቆይ ያስተላለፈውን ውሳኔንም ነቅፏል።
ባልደራስ ይህን ያለው፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ አራት አመራሮቹ ከተፈቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ዛሬ ሐሙስ ጥር 5፤ 2014 በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዋነኛ ትኩረት የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው።
ፓርቲው “መንግስት ‘ምዕራፍ አንድ’ ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ፤ ትልቅ አደጋ ያዘለ ነው” ሲል ስጋቱን ገልጿል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል” ያለው ባልደራስ፤ መንግስት “ዘመቻውን ያቆመበትን ምክንያት በተመለከተ በቂ ምላሽ አልሰጠም” ሲል ተችቷል። የፌደራል መንግስቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ “ንቀት እያሳየ ነው” ሲልም ነቅፏል፡፡
ባለፈው ሳምንት አርብ ከእስር የተፈቱት አቶ እስክንድር ነጋ፤ መንግስት “እከሌ ወሰን ጋር ሄጄ አቆማለሁ ማለት አይችልም” ሲሉ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩትን የፓርቲያቸውን አቋም አሳውቀዋል። “ብልጽግና ይህን ሊወስን ይችላል። መንግስት ግን እንደመንግስት አማራጭ የለውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የገቡትን ቃለ መሃላ ማስጠበቅ አለባቸው” ሲሉ አቶ እስክንድር አሳስበዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  (ሰበር ዜና) ሲአን የፊታችን እሁድ ከሚደረገው ምርጫ ራሱን አገለለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share