“ሕዝቡ አሁንም የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ዝግጁ ይሁን” ዶክተር ይልቃል ከፋለ

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር

ሕዝቡ በከፋፋይ ሐሳቦች ሳይረበሽ የትህነግ የሽብር ቡድንን በጋራ ለመደምሰስ ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።

ርእሰ መሥተዳድሩ በክልሉ የደረሰውን ውድመት ሲዘግቡ ለቆዩ የመገናኛ ብዙኀን ሙያተኞች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ከአሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታዎች አኳያ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል። ❝አሁን ላይ ከአሸባሪው ትህነግ አባላት የእስር መፈታት ጋር ተያይዞ ሕዝቡ ሁኔታው ቢያስቆጣው ትክክል ነው ፤ እውነትም አለው፤ የቡድኑ አባላትም ወንጀለኝነታቸውን እናምናለን❞ ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ከታሰሩም በኋላ የቡድኑ ወረራ ተባብሶ የቀጠለና አሁንም ድረስ ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ በመሆኑ የአባላቱ መለቀቅና መታሰር ያለውን ሁኔታ ጋር ሲታይ የሽብር ቡድኑን ከመደምሰስ ዋና ዓላማ የሚያነጥል ጭንቀት ውስጥ የሚከት እንዳልሆነ ገልፀዋል።
ምንም እንኳን ሕዝቡ ከሀገራዊ አንድነትና ሰላም ፍላጎት አኳያ የቡድኑ አባላት መፈታት ቢያሰጋውም በተለይም የችግሩ ገፈት ቀማሽ የአማራ ሕዝብ በርካታ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ከጀመረው ሽብር ቡድኑን የማጥፋትና ኅልውናውን የማረጋገጥ ዘመቻ መዘናጋት የለበትም ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ቡድኑ እየወጋን ያለው ብቻውን አይደለም በተለይም ከቅማንት ጽንፈኛ ቡድን፣ ከጉምዝና ሸኔ ቡድኖች እንዲሁም ከውጭ እንደ ግብጽና ሌሎች አንዳንድ ሃገራት ጋር በመሆን ኢትዮጵያ እንዳትለማ ለማድረግና ለማውደም እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ የሽብር ቡድኑ ካልተወገደ እንደ አማራ ሕዝብም ይሁን እንደ ኢትዮጵያ ትልቅ ስጋት በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ከፌደራል መንግሥት ጋር በመነጋገር ሽብር ቡድኑ በሚጠፋበትና የወደመው ሃብት በሚተካበት ልክ ይሠራል ብለዋል። ሆኖም ሕዝቡ በሚነሱ አንዳንድ ሐሳቦች ተበርዞ ሽብር ቡድኑን ከመደምሰስ ዐቢይ ዓላማው እንዳይነጠል አሳስበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Food Safety: Keep Your Family Healthy This Summer

“የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ፖሊስ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኝ የመንግስት መዋቅር በርካታ የህይወት እና የአካል መስዋዕትነት ከፍለው ክልላችንን ብሎም ሀገራችንን ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ በማውጣት እና ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ላይ እዲቀበር አድርገዋል።
/ዶ/ር ይልቃል ከፋለ/
እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ የሚከፍሉ የፀጥታ ኀይል፣ የፍትህና የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ሰራተኞች እንዳሉ ሁሉ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡም አሉ።
የፍትህ ተቋማት የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል እና ስርዓትን በማስፈን ህዝብ ፍትህ የሚያረጋግጥልኝ ተቋም ስለሆነ የኔ ተቋም ነው እንዲለው ለማድረግ ኀላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት ይገባል። ለዚህም ቁርጠኛ የሆነ ዳኛና አቃቤ ህግ መገንባት ያስፈልጋል።
ህግን ለማስከበር ቀን ከሌት የሚሰራና ቁርጠኛ የሆነ የፖሊስ ሰራዊት መገንባት ያስፈልጋል። ሚሊሻ ሲቋቋም የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ቢሆንም በተለያዩ ግንባሮች በከፈለው መስዋዕትነት ታሪክ ሰርቷል። ቀጣይም ለህዝብ እና ለሀገር የሚጠቅም አካባቢውን የሚጠብቅ ሚሊሻ መገንባት አለብን።
የአማራ ልዩ ኀይል ወደር የማይገኝለት፣ ቆራጥ፣ ጽኑ፣ ጀግናና ለጠላት የማይበገር ሰራዊት ነው። የአማራ ልዩ ኀይል የአማራ ህዝብ የጀግንነት መገለጫ ሆኖ እንዲቀጥል መስራት አለብን።
ፋኖ ሀገር ተወረረች ሲባል በከፍተኛ ንቅናቄ ተነስቶ ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ መስዋዕትነት የከፈለ ኀይል ነው። በቁርጠኛነትና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ስራ ሰርተን የህዝብን የፀጥታ፣ የፍትህና የደህንነት ጥያቄዎቹን መመለስ ይገባል።
የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ኀላፊነት የኛ ተቀዳሚ ተግባር ነው። ልማት፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚመጣው ሰላምና መረጋጋት ሲኖር መሆኑን ማመንና መስራት ያስፈልጋል። የዚህ ኀላፊነትም በእኛ እጅ ነው። ጠላታችንን የመታገል ተቀዳሚ ኀላፊነት የኛ ስለሆነ አንድነታችንን በማጠናከር በሁሉም መስክ ቀድመን መገኘት ይገባናል።
የመንግስትን የመጀመሪያ ተልዕኮ በኃላፊነት የሚወጣው የፍትህ እና የፀጥታ ተቋም ግንባር ቀደም ኀላፊነት ወስዶ መወያየት፣ መፈተሽ፣ መገምገም እና ከችግሮች ተነስቶ ማስተካከያዎችን በማድረግ እንደገና በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ መንገድ እና በሀሳብ እንዲፀና አደራጅተን መንቀሳቀስ ከኛ ይጠበቃል።”
.
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
.
የአማራ ክልል የፍትህ፣ የፀጥታና የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ውይይት ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

4 Comments

  1. ክአብይ ጀርባ ሆነው ክ ወያኔ ጋር የ ሚያደራደሩት አቶ ሌነጮ ለታ፣ ወርቅነህ ገብየሁ እና አባዱላ ገመዳ ናቸው
    አመራ ሆይ ተክደሃል

  2. እንጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ
    ሕግ አዋቂው ቆሞ ሌባ እየፈረደ
    አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ
    ሰው እየተጋዘ አውሬ እየነገሰ
    ቀሳውስት ተወግዘው ሌባ እየቀደሰ
    ይሕ ሁሉ ሲሰራ መላው ጠፍቶን እኛ
    እረ ወዴት ገባህ የሰማዩ ዳኛ!!!!!!

    ገጣሚ ህሊና ደሳለ

  3. ዶር ከፍያለው በክፉ ቀን አብይም ሆነ አገኘሁ ተሻገር አያድኑህም ታዳኞች ናቸውና ብልጥ ከሆንክና በግልህ እንድትቆም ከፈቀዲልህ። ፋኖንና የአማራ ልዩ ኃይልን አሰልጥነህ በህዝብ ተማምነህ ኑር ይህን ካላደረግህ እንደ አገኘሁ ተሻገርና ሌሎችም የሽመልስ አብዲሳ ዱቄት ተሸካሚ ሁነህ አሟሟትህ አያምርም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share