እነስብሃት ሲፈቱ እኛም ደንግጠናል ይላል አብይ አህመድ። ኧረ ምን ጉድ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦችን ክስ አቋርጦ እንዲፈቱ ውሳኔ ያሳለፈው “ኢትዮጵያን በጠንካራ አለት ላይ ለማኖር፣ ጠላቶቿን ለመቀነስ እና ጉልበት ለመሰብሰብ” መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። “ጉዳዩን እኛም መጀመሪያ ስንሰማው” አስደንግጦናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሆኖም ውሳኔው “ለኢትዮጵያ የሚበጅ፣ ዘላቂ ጥቅም የሚያግዝ፣ በአውደ ውጊያ የተገኘውን ድል በሰላሙ መድረክ እንዲደገም የሚያደርግ” በመሆኑ “እየመረረን የዋጥነው እውነት ነው” ብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል]

271544543 7668886739804076 4456581959538528605 n

4 Comments

 1. መለፍለፍ የማይሰለቸው እንዲህ ያለ ዲስኩረኛ ገጥሞን አያውቅም። “እኛም ስንሰማ ደንግጠናል”። አንተ ራስህ ወሳኝ ሆነህ እንዴት ነው ደንጋጭ የምትሆነው? ሽማግሌዎች ቤታቸው ወይም ገዳም? ምን አይነት ሰው ነው? ወያኔን እንዴት ገዳም ግባ የሚባለው? አሸንፈናል የሚለውስ መቼ ጦርነቱ ተቋጨና ነው? ገዳም ገብተው አይደል እንዴ ያኔም አሁንም ሰዎችን የሚገድሉትና የሚዘርፉት? የወያኔን ደም አፍሳሾችን መፈታት የሚቃወሙ ሁለት ሃይሎች አሉ ይለናል። አንደኛው የወሬ ነጋዴ ነው ሲል ሌላውን ደግሞ እውነተኛ የሃገር ፍቅር ያላቸው የሚያነሱት ጥያቄ ነው ብሎናል። የእርሱ ሰልፍ ከየትኛው ነው? ወያኔና ግብረ አበሮቹ የአንተን መንግስት ፈርተው ጭጭ ብለው እንደማይቀመጡ ታሪካቸው ያሳያል። አሁንም ውጊያው እንደ ቀጠለ ነው። እናንተ በአዲስ አበባ የለበጣ ሹመት ስትሰጣጡ ወያኔ በዚህም በዚያም ሰላዪችን እያስገባና መድፍ እየተኮሰ እንደሆነ እየታየ ነው። ወያኔ ባለበት አለም ላይ ሰላም ይኖራል ማለት በጀግኖች ደም መነገድ ነው።
  ጠ/ሚሩ የተማታበት ሰው ነው። አንዴ እኔ በፍትህ ነገር አልገባም ፈችም አሳሪም የሃገሪቱ ህገመንግስት ነው ሲለን በሌላ በኩል ደግሞ ይኽው በተኙበት መኪና የነድባቸውን፤ ገድለው የጨፈሩባቸውን የወያኔ መሪዎች መልቀቁ የቱን ያህል ጭፍን እይታ እንዳለው ያሳያል። ወያኔ በቀሰቀሰው ግጭት የቆሰለ፤ የሞተ፤ የተደፈረ፤ የተዘረፈ ወዘተ ማን ይቁምለት? የ 27 ዓመት ያደረሱት መከራ አልበቃ ብሏቸው አይደል እንዴ ሽዋ ድረስ ገብተው እልፎችን ገድለውና ዘርፈው ጭነው ወደ መቀሌ የወሰድት? ለመሆኑ የጠ/ሚሩ ዲስኩር በምናባዊ እይታው የሚታየው ሰላምና በምድር ላይ ያለው እውነታ መቼ ይገናኛል? ደግሞ እኮ አያፍርም ወያኔ አዲስ አበባ ቢገባ ኑሮ ምን ያደርግ ነበር ይለናል። ዘቅዝቆ ነዋ የሚያንጠለጥልህ። እንዴት ይህ ይጠፋዋል። ከእነርሱ የክፋት ጆኒያ አይደል እንዴ የወጣው? ግን እቅድ አንድ ነው። የአማራን ህዝብ አንገት ማስደፋትና ሁሌም የበታች ሆኖ እንዲኖር ማድረግ ነው። 95% ወያኔ ጉዳት ያደረሰው በአማራ ክልልና በአማራ ህዝብ ላይ ነው። በአንድ ጥናት መሰረት 30 ዓመት ወደ ኋላ እንዲሄድ ተደርጓል። በምንም አይነት የፍትህ ሂሳብ የወያኔ የክፋት ቋቶች መፈታት አልነበረባቸውም። ግን ልብ ላለው ይህ የሴራው ጅማሬ እንጂ ፍጻሜው አይደለም። እጅግ የሚያሳዝኑኝ በወያኔ የታረድት ሰዎችና እንስሳት፤ ወያኔ እየጫነ የወሰደው ንብረትና ባዶ እጃቸውን የቀሩት ወገኖች ናቸው። የጠ/ሚሩ የማያቋርጥ ዲስኩር ያቅለሸልሻል። እግዚኦ ማለት ብቻ ነው። የፓለቲካ ሽፍጥ እንዲህ ሲገማ በዘመኔ አይቼ አላውቅም። በቃኝ!

 2. የዘንድሮ ጉድ ይገርማል።
  መረጃ በቀብድ ሆነ ደግሞ? ክሱን ለጥፋችሁ “ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል” ምን የሚሉት ነው?

  んにちは

 3. 1. የህወሃት አመራሮች ከተፈቱ፣ ከእነሱ ጋር ግንኙነት አላት ተብላ የታሰረችው መአዛ መሐመድ እስር ቤት ምን ትሰራለች?
  2. የኢትዮጵያን ወታደሮች በተኙበት እንዲታረዱ፣ መብረቃዊ ትዕዛዝ የሰጡና መርቀው ያዘመቱ ከተፈቱ፣ ነገ አብይ ሊለቃቸው፣ መከላከያ ለምን እነ ደብረፅዮንን ለመያዝ በከንቱ ደሙን ያፈሳል?
  3. ጦርነቱ ሳይጠናቀቅ፣ አጥፊዎች በህጉ መሰረት ሳይፈረድባቸው እንዴት ሆኖ ነው ክሳቸው የሚቋረጠው?
  4. የአማራ ህዝብ ጠላታችን ነው፣ ሂሳብ እናወራርዳለን በማለት ሆስፒታል፣ ት/ት ቤት፣ ሆቴል፣ አውሮፕላን ማረፊያ የግል ቤቶችን እና የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማቱን ያወደሙ፣ ሴት የደፈሩ፣ ከተሞች ላይ መድፍ እና ሚሳየል በመተኮስ በጅምላ ህዝብ የጨፈጨፉ፣ የዘር ማጥፋት የፈፀሙ የህወሃት አመራሮችን መልቀቅ በአማራ ህዝብ ደም ላይ ማፌዝ ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ተባባሪ መሆንም ነው።
  5. በፓርላማ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀ የህወሃትን አመራሮችን የለ ፍርድ መልቀቅ ከአሸባሪ ጋር መተባበር ስለሆነ በሽብርተኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው።
  6. ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን የኦነግ ሰራዊት አዲግራት ላይ የምሳ ግብዣ አድርገው ለተቀበሉት ለእነ ስወብሃት ነጋ ውለታ መመመለስ ብቻ ሳይሆን የስትራቴጂ አጋርነትን የሚያሳይ ነው።
  7. ዲያስፖራውን አገር እንዲገባ ጥሪ አድርጎ እነ ስብሃት ነጋን መልቀቁ በተለይ የሃገሪቱ ጠ/ሚ እሱ ሆኖ አብይ አህመድ እኔም ስሰማ ደንግጫለሁ ማለቱ ህዝብን መናቅ ነውና ይህችን የበሻሻ እርድናን እዛው ውሰዳት።
  8. ጂጂ ስለ አድዋ በዘፈነችው ውስጥ “የወዳደቁት መች ተነሱና” እንዳለችው ወያኔ በተኙበት ያረዳቸው የሰሜን ዕዝ አባላት ተሰባስበው መች ተቀበሩና፣ የወታደር ቤተሰቦችስ መች ተረድተው ነው ገዳዮቹ የተለቀቁት?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.