“አሜሪካ የታጠቁ ሃይሎችን መደገፏን የኢትዮጵያን መንግስት ስም ማጥፋቷን ማቆም አለባት” ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

melkam Gendddddaffffdddddff
አሜሪካ የታጠቁ ሃይሎችን መደገፏን የኢትዮጵያን መንግስት ስም ማጥፈቷን ማቆም አለባት” ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ገለጸች።
አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የምታደርገውን መርህ አልባ አካሄድም ተቀባይነት የለውም ብላለች።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ የዛሬ ዓመት አሜሪካውያን በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ካፒቶል ሂል የተፈጠረውን አመጽና ወረራ ተቃውመው አንድ ላይ በቆሙበት ተመሳሳይ ጊዜ “በኢትዮጵያ የታጠቁ ሃይሎች” በፌደራል ወታደራዊ እዞች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት ገልጻለች።
ይሁንና አሜሪካ ጥቃቱን ከማውገዝ ይልቅ የታጠቁ ሃይሎችን የመደገፍና ለደረሰው ጥቃት የሚጠበቅበትን ምላሽ የሰጠውን የኢትዮጵያ መንግስት ማጣጣልና ስም በማጥፋት ስራ መጠመዷን ተናግራለች።
አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የምትከተለውን መርህ አልባ የሆነ አካሄድና ስም የማጠልሸት ተግባር ማቆም እንዳለበት አመልክታለች።
“በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ አካሄድን መከተል በቃ ሊባል ይገባል” ብላለች ጋዜጠኛ ሄርሜላ በትዊተር ገጿ ባሰፈረችው መልዕክት።
ትውልደ-ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ’አንድ ሚሊዮን የዳያስፖራ የአገር ቤት ጉዞ ጥሪ’ ተቀብላ ከቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ የሚታወስ ነው።
ጋዜጠኛ ሄርሜላ የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ ሀሳብ በመጀምርና በማስተባበር የኢትዮጵያን እውነት ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የማስረዳት ተግባር እያከናወነች ትገኛለች።
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ታህሳስ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ)“

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.