የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ለመጡ የዲያስፖራ አባላት ለማስተዋወቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

ሁመራ: የሀገራቸውን ጥሪ የተቀበሉ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው ገልጸዋል።

የምዕራባዊያንን የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለማስፈፀምና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ የወገን ጦር ድልን ሲጎናፀፍ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሕልውና ዘመቻው የተለያየ ድጋፍ አድርገዋል። የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ሙከራ ያልተሳካላቸው ምዕራባዊያንም በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ለማሳደር ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው። የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እሸተ ደምለው ከ30 ዓመት በኃላ በጀግናው የወገን ጦር ነፃነቷን የተጎናፀፈችው ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ኢትዮጵያዊያንን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች ብለዋል። ዞኑ የኢንቨስትመንት አማራጭ መሆኑን ለማሳየትም ኮሚቴ ተዋቅሮ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡

አቶ አሸተ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የቀድሞ አገዛዝ የወልቃይት ጠገዴ ምድር የአማራ ነው ብለው ማንነታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ብዙ መከራን ተቀብለው እና ስደትን ምርጫቸው አድርገው የኖሩ የአካባቢውን ተወላጆችና ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎችን በመቀበል ዞኑ ከፋተኛ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያለው መሆኑን ግንዛቤ ለመፍጠር ዝግጅቱ መጠናቀቁን ነው ያብራሩት፡፡

ወደ ወልቃይት ጠገዴ ምድር ለሚመጡ ዲያስፖራዎች ዞኑ ከጎንደር ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ዞኑ በእርሻ እና ከተማ ልማት ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ የሚያስችል መጠነ ሰፊ ዝግጅት መደረጉንም አቶ አሸተ ገልፀዋል። በዞኑ ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ እና ማሾ በከፍተኛ ሁኔታ ይመረታሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባለስልጣኑ ተገደለ - ጎንደር ተወጠረች | በቻይና የአብይ ጠባቂዎች ኮበለሉ

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወደ ወልቃይት ጠገዴ ምድር ለመግባት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጎ ድባቅ ሲመታ በሬ ወለድ ወሬዎችን በማናፈስ በዞኑ ሰላም እንደሌለ ለማስመሰል ሞክሯል ያሉት አቶ አሸተ ዞኑ ሰዎች በነፃነት የሚንቀሳቀሱበት እና አስተማማኝ ሰላም የሰፈነበት ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር የገቡ ዲያስፖራዎችም ምንም ስጋት ሳይገባቸው ወደ ዞኑ በመምጣት ነባራዊ ሀቁን ማየት አለባቸው፡፡ የተዘረጋውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀምም ወደ ልማት እንዲሰማሩ እና መጭውን የልደትና የጥምቀት በዓል ከ30 ዓመት በኃላ ነፃነቷን በተቀበለችው የአማራ ምድር እንዲያከብሩ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

አሚኮ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share