መንግሥት የትግራይ ሕዝብ አሸባሪውን ትሕነግ በአደባባይ ወጥቶ ሊቃወመው ይገባል አለ

tplf terrorist group

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ያለበት ማኅበራዊና ምጣኔሃብታዊ ችግር ተፈቶ በዘላቂነት ሰላሙ እንዲረጋገጥ አሸባሪውን ትሕነግ ማውገዝ ብቻ ሳይሆን በአደባባይ ወጥቶ ሊቃወመው ይገባል አለ፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የትግራይ ሕዝብ አሸባሪው ትሕነግ በጦርነት ብቻ የመኖር ፍላጎት እንዳለው በመገንዘብ ሊያስቆመው ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያም ይሁን በውጭ አገራት የሚኖር የትግራይ የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል የሽብር ቡድኑን እኩይ ሴራ በማሳወቅ ሕዝቡን ሊያነቃ ይገባልዋልም ነው ያሉት።
መከላከያ ወደ ትግራይ መግባቱን ትቶ ባለበት እንዲፀና የተደረገው የትግራይ ሕዝብ በድጋሚ የማስተዋል ጊዜ እንዲያገኝ በማሰብም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል አሸባሪው ትሕነግ በከፈተው ጦርነት የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎችና አካባቢዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
መላው ኢትዮጵያዊ ለመልሶ ማቋቋሙ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት ሚኒስትሩ የቴሌኮም፣ የኤሌትሪክ፣ የባንክ ና መሰል አገልግሎቶች ወደ ሥራ መመለሳቸውን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ ላሊበላና ኮምቦልቻ በረራ መጀመሩን አንድ እምርታ ሲሉም አንስተዋል፡፡
በመስከረም ቸርነት
ዋልታ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share