በደም ከሚነግደው ከሃዲ ህወሓት ጀርባ ያለው ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይል ማነው?

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

The essence of neo-colonialism is that the State which is subject to it is, in theory, independent and has all the outward trappings of international sovereignty. In reality its economic system and thus its political policy is directed from outside,” Neo colonialism: the last stage of imperialism, Kwame Nkrumah, 1966.

TPLFለጥቁር አፍሪካ ነጻነት፤ ፍትህና ብልጽግና ታግለው የጋናን ነጻነት ስኬታማ ካደረጉ በኋላ በአዲሱ የቅኝ ገዢዎች የበላይነት ሴራ ከስልጣናቸው የተወገዱት ክዋሜ ንክሩማ የአዲሱን የምእራባዊያንን የበላይነት ይዘት በሚገባ ገልጸውታል። “አንድ አገር በዓለም ደረጃ ሉዐላዊነት አለው ተብሎ እውቅናና ሽፋን ቢሰጠውም፤ ሃቁ ግን፤ የኢኮኖሚው ስርዓትና ተዛማጅ የሆነው የፖለቲካው መርህ የሚሽከረከረው በውጭ ኃይሎች ነው።” አዲሱ የቅኝ አገዛዝ ስርዓት ማለትም ይኼው ነው።

ህወሓት/ትህነግ ከአንድ ዓመት በላይ በኢትዮጵያ፤ በመላው ሕዝቧ (በተለይ በአማራውና በአፋሩ) ላይ የፈጸመው የሚዘገንን እልቂትና የኢኮኖሚ ውድመት በተከታታይ ትውልድ የማይረሳ ግፍና በደል ነው። ለኢትዮጵያ ሸክም ነው። ለትግራይ ሕዝብ አሳፋሪ ነው። በደም የሚነግደው ህወሓት የፈጸመው ወንጀል ሊረሳ አይችልም። ጥያቄው ከዚህ ሁኔታ ምን እንማራለን? ምንስ እንሰራለን? የሚለው ነው።

የጀኖሳይድ ነጋዴዎች የሚሉትን መለየት ያስፈልጋል።

ንጹሃን ዜጎችን ለይቶ በማንነታቸው ምክንያት ከአርባ ዓምስት ዓመታት በላይ በተደጋጋሚ እልቂት የተሄደው በአማራው ሕዝብ ላይ ነው። ይህ አረመኔነትን የሚያሳይ ጫካኔ የተሞላበት እልቂት ጀኖሳይድ የሚባለውን መስፈርት ያሟላል። ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ኢላማ ያደረጉት እልቂት (Genocide) በማያሻማ ደረጃ በአማራው ላይ ነው። በተጨማሪ ተራው የአማራው  ሕዝቡ ለኑሮው የሚመካባቸው የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ውድመት ምክንያት ይህ ሕዝብ ተስፋ እንዲቆርጥና ህልውናው ለአደጋ እንዲጋለጥ ነው። አንሞኝ ህወሓት የፈጸመው እልቂትና ውድመት የጣሊያን ፋሽስት ወራሪው ኃይል ካደረገው በላይ ነው። ለዚህ ነው፤ ይህ ወንጀል ይቅርታ ሊደረግለት የማይችለው።

እኔ፤ ህወሓት የፈጸመውን እልቂቱና ውድመት በተናጥል አላየውም። ይህ ሽብርተኛ፤ ጨካኝ፤ ዳቢሎሳዊ፤ ከሃዲና አውዳሚ ቡድን በቀጠና፤ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደጋፊዎች እንዳሉት መረዳት ያስፈልጋል። በሌላ አነጋገር በኢትዮጵያና በንጹሃን ላይ በተከታታይ የሚካሄደውን ግፍና በደል ያባባሱት የውጭ ኃይሎች የአዲሱ የቅኝ አገዛዝ ስርዓት አካላት ጫና ፈጣሪዎች ናቸው። ህወሓት አገግልጋይ፤ ሎሌና አሽከር እንጅ ለትግራይ ሕዝብ አስቦና ተቆርቁሮ የሚሰራ ኃይል አይደለም።

በቀጠናና በአህጉር ደረጃ ስመለከተው ህወሓት የወገነው ከሱዳንና ከግብጽ ጋር ነው። ሱዳን የግብጽን የጅዖፖለቲካ ፍላጎት፤ በተለይ በናይል ወንዝ ላይ ያላትን የበላይነት ለማስተጋባትና ታላቁን የሕዳሴን ግድብ ለመበከል በኢትዮጵያ ላይ የውክልና ጦርነት ታካሂዳለች። ህወሓት የአገር ውስጥ እልቂትና ውድመት ሲያካሂድ ሁለቱም አገሮች “በለው፤ አይዞህ፤ ታሸንፋለህ” የሚሉት ግብጽና የግብጽ የውክልና ጦርነት አፈቀላጢ የሆነው የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ ናቸው:: የሚሰሩት ደግሞ በመናበብ ነው። ጦርነቱ በቀላሉ ሊፈታ የማይችለውም ለዚህ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመራመረው፤ የአውሮፓ የጋራ ማህበር፤ የአሜሪካ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት አመራር በአንድ ላይ ሆነው ለህወሕት ድጋፍና ሽፋን ሲሰጡ ቆይተዋል። የግብጽንም ጥቅም ለማስተጋባት እንደሚሞክሩ እገምታለሁ።

የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ አስራ ሁለት ጊዜ በተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ካውንስል እንዲነሳ የተደረገበት ምክንያት ኢትዮጵያን ለመታደግ አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ልክ ህወሓት ያደርግ እንደ ነበረው ታዛዢና ተገዢ እንዲሆን ጫና ለማድረግ ነው። የአሜሪካ መንግሥት የሚፈልገው ይህንኑ መሆኑን አውቃለሁ። የሌሎች አገሮች መንግሥታትን እንደ ሸሚዝ ሲቀይሩ የቆዩ መሆናቸውን በመረጃ ለማቅረብ ይቻላል።

የአሜሪካ መንግሥት “እኛ ለማንም አንወግንም፤ ገለልተኛ ነን” የሚሉትን አልቀበለም። የምትቀበሉ ምሁራንና ልሂቃን ተሳስታችሁ ሌላውን አታሳስቱ።

አዲሱ የቅኝ ገዢዎች መርህና ስልት ክዋሜ ንክሩማህ ያሳሰቡትን ያንጸባርቃል። ይህንን ለማለት የተገደድኩበትን ምክንያቶች ከታች በዝርዝር አቀርባለሁ።

ከታሪክ እንማር

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የዓለምን ተቋማት በበላይነት የሚያሽከረክረው የአሜሪካ መንግሥት ነው። ለራሱ ብሄራዊ ጥቅም የሚመቹ መንግሥታትን የሚገልብጠውና እንደ ህወሓት ያሉትን ለራሱ ታዛዢና አገልጋይ የሆኑትን የሚተካው የአሜሪካ መንግሥት ነው። ችሌ ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር ተመሳሳይነት አላት። የተባበሩት መንግሥታት የሚወግነው ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ነው።

ጣልያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ በፊት ኢትዮጵያ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ ያቀረበችውን አቤቱታ ፋይዳ እንዳይኖረው ያደሩጉትን የምእራብ አገሮች አሳፋሪ ሚና ወደ ጎን እንተወውና ባለፉት አስርት አመታት የሆነው ግፍና በደል በአጭሩ እንዳሰው። J.S. Davies, 2014 (ዴቢስ) የተባለው የአሜሪካ ተመራማሪ የዛሬ ስምንት አመት ያቀረበው ጥናትና ምርምር የአሁኑን በኢትዮጵያ ላይ የሚካደውን የረቀቀና የተቀነባበረ ሴራ ያሳያል።

ሳሎን በተባለው መድረክ ኒኮላስ ዴቪስ “የአሜሪካ መንንሥት የገለበጣቸው፤ የደገፋቸው፤ የበከላቸው 35 አገሮች” የትኞቹ ናቸው? የሚለውን በዝርዝር አቅርቦታል። እነዚህ በመላው ዓለም የሚገኙ አገሮች “በፋሽስታዊነት፤ በሽብርተኛነት፤ በሙሰኛነትና” በሌሎች ጸረ-ፍትህ፤ ጸረ-ሕዝብ፤ ጸረ ዲሞክራሲ መለያዎች የታወቁ እንደ ነበሩ ያሳያል። በችሌ፤ ተራምጁን አሌንዴን አስወግድው በአምባገነን መንሥት ተክተውታል። ንክሩማን ገልብጠው ተክተዋል።

እነዚህ ሰላሳ አምስት በአሜርካ መንግሥት የተበከሉ አገሮች የሚከተሉት ናችው።

 1. አፍጋኒስታን፤ 2. አልባንያ፤ 3. አርጀንቲና፤ 4. ብራዚል፤ 5. ካምቦዲያ፤ 6. ችሌ፤ 7. ቻይና፤ 8. ኮሎምብያ፤ 9. ኪውባ፤ 10. ኤል ሳልባቫዶር፤ 11. ፍራንስ፤ 12. ጋና፤ 13. ግሪስ፤ 14. ሄይቲ፤ 15. ሆንዱራስ፤ 16. ኢንዶኔዢያ፤ 17. ኢራን፤ 18. ኢራክ፤ 19. ኮርያ፤ 20. ላኦስ፤ 21. ሊቢያ፤ 22. ሜክሲኮ፤ 23. ሚያንማር (በርማ) 24. ኒካራጓ፤ 25. ፓኪስታን፤ 26. ሳውዲ አረብያ፤ 27. ተርኪ፤ 28. ፓናማ፤ 29. ሶርያ፤ 30. ዩጎስላቭያ፤ 31. ዩሩጓይ፤ 32. ፊሊፒንስ፤ 33. ዛየር፤ 34. እስራኤል፤ 35. ጓቴማላ

እነዚህን አገሮች የበከላቸው የአሜሪካ መንግሥት ነው ይልና፤ ምክንያቶችን ሲዘርዝር ሰብሳቢው ሃሳብ ለአሜሪካ ባለኃብቶች ተገዠነታቸውና ታማኝነታቸው ጥርጣሬ ውስጥ ስለገባ ነው ይላል። ፋሽስትም ቢሆን የኔ ፋሽስት፤ ሽብረተኛም ቢሆን የኔ ሽብርተኛ ወዘተ ነው የሚለው ብሄል የመጣው ከዚህ ነው።

ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ባለሥልጣናቱ ስለ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መርህ የጦፈ ውይይት ያደርጉ ነበር። የነጩ ቤተመንግሥት አማካሪ የነበሩት ካርል ሮቭ “እኛ እኮ የበላይ ገዢዎች ነን ( the USA is an empire) መርሳት የሌለባችሁ መርህ ይህንኑ ነው” ብለው ነበር። በአንድ ወቅት፤ በስድሳ አገሮች በተድረገ የድምጽ ግምገማ፤ ሃያ አራት በመቶ የሚሆኑት ድምጽ ሰጭዎች “ለዓለም ሰላም ዋና ጠንቅ አሜሪካ ናት” እንዳሉ አስታውሳለሁ።

የአሜሪካ መንግሥት በሰላሳ አምስት አገሮች ላይ ጣልቃ እየገባ ሊከተሉት የሚገባቸውን የፖለቲካ፤ የውጭ ግንኑነት፤ የደህንነት፤ የንግድ፤ የኢኮኖሚና ሌላ መርህ በበላይነት የበየነውና አሁንም ለመበየን የሚሞክረው የወታደራዊና የስለላ አቅሙን በመጠቀም ነው። ለኔ የበላይነት (ኤምፓየር) ተገዢ ከሆንክ ድጋፍ እሰጥሃለሁ፤ አለያ ግን እተካሃለሁ የሚለው መርህ አሁንም አልተቀየረም። በህዝብ የተመረጠ መንግሥት ቢሆን ባይሆን ለአሜሪካ ባለሥልጣናት ፋይዳ የለውም። ለዚህ ነው፤ በሕዝብ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግሥት እውቅና ለመስጠት የተቸገሩት።

ንክሩማህ የተናገሩት ትዝ ይለኛል። “አዲሱ የቅኝ ገዢዎች ስልት ስልጣንንና የበላይነትን ያለ ምንም ሃላፊነት” የሚያስተጋባ ስልት ነው፤ “ምዝበራ ሲካሄድ ምንም አይነት መካካሻ የለውም” ያሉት ትክክል የሚሆነው። የህወሓት አመራርና የአሜሪካ መንግሥት አመራር ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው መሆኑን አሰምርበታለሁ።

አሜሪካ ሲመሰረት በጥንታዊ ነዋሪዎቹ ላይ ያለምንም ሃላፊነትና ሰብአዊነት ጭፍጨፋ ተካሂዷል። በጥቁር አሜሪካኖች ላይ ከአራት መቶ ዓመታት በላይ እጅግ የሚዘገንን ግፍና በደል ተፈጽሟል፤ አሁንም ቀጥሏል። ዲሞክራሲ አለ ይባል እንጅ ዲሞክራሲ ለማን ያገለግላል? የሚለው ጥያቄ አልተመለሰም።

በተመሳሳይ፤ ህወሓት የሚፈጽመውን ግፍና በደል የአሜሪካ ባለሥልጥናት ያውቁታል፤ ግን ለነሱ ፋይዳ ቢስ ነው። እልቂቱና ውድመቱ አይመለከታቸውም። የገለበጧቸው መንግሥታት ታሪክ የሚያስተምረን ዋናው ኢላማ ለነሱ ታዛዢና አጎብዳጅ የሆነ መንግሥትን በማንኛውም ዘዴ ተንከባክቦና ደግፎ ስልጣን እንዲይዝ ማድረግ ነው።

ይህ ወደ ችግሩ እምብርት ይመራኛል።

 1. የህወሓት ጽንሰ ሃሳብ፤ መርህ፤ ማኒፌስቶና ተደጋጋሚ ጥሪ (በአማራው ሕዝብ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን) የሚለውን ጨምሮ የሚያሳየው ይህ ድርጅት ለአማራው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ህልውና ስር የሰደድ ጠንቅስለሆነ አስተሳሰቡና መርሆዎቹ ሙሉ በሙሉ መወገድ አለባቸው።

 

 1. ህወሓት ባለፉት አርባ ዓመታት ያዋቀራቸው የድርጅት መዋቅር ሰንሰለቶች አጥፊና አምካኝ ስለሆኑ ሙሉ በሙሉ መደምሰስ አለባቸው።

 

 1. ህወሓት የፈጠራቸው፤ ያዋቀራቸው ዘውጋዊና የጠባብ ብሄርተኝነትን የበላይነት ያማከሉ ድርጅቶች፤ ተቋማት፤ መዋቅሮች፤ ሰንሰለቶች ሙሉ በሙሉ መፍረስ አለባቸው፤የከፋፍለህ ግዛውና ብላው ሕገ መንግሥትም በአስቸኳይ መሻሻል አለበት።

 

 1. ህወሓት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነትና ሉዐላዊነት ዋና ጸር መሆኑን በዚህ ጦርነት ተመልከታናል። ስለሆነም፤ የትምህርት ተቋማት የህወሓትን ታሪክ ልክ እንደ ጀርመን ናዚዎችና እንደ ጣሊያን ፋሽስቶች እንዲወገዙና እንዲባክኑ ማድረግ ወሳኝ ሂደት መሆኑን አሳስባለሁ።

 

 1. የኢትዮጵያ መንግሥት ልክ የኢስራኤል መንግሥት አይሁዶችን የጨፈጨፉትን ናዚዎች ከያሉበት ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዳደረገው ሁሉ፤ በንጹህ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ያደረጉትን የህወሓት መሪዎችና አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ክትትል የማድረግ ግዴታ አለበት።

 

 1. የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተማምኖና ተከባብሮ ለመኖር ይፈልግ ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ። ይህ ከሆነ የትግራይ ሊሂቃን፤ ምሁራን፤ ስብስቦችና ተራው ሕዝብ በመጀመሪያ ህወሓት ያደረሰውን እጅግ የሚዘገንን እልቂትን ውድመት የማውገዝ ግዴታአለባቸው። ይህ ምክር ራስን ከሸክሙ ነጻ ከማውጥት ግዴታና ሃላፊነት ጋር የተያያዘ ነው። ከላይ እንዳሳየሁት፤ ፈረንጆች እርስ በእርሳችን ብንጨራረስ ከይስሙላ መግለጫ በላይ ሊደርሱልን አይችሉም፤ አይፈቅዱም።

በአሁን ወቅት፤ በተለይ ህወሓት ግዙፍ እልቂትና ጥፋት አካሂዶ፤ የኢትዮጵያ ጥምረት ኃይሎች ወራሪውን ኃይል ብዙ መስዋእት ከፍለው ከአፋርና ከአማራው ክልሎች ካስወጡት በኋላ የሚደረገው የድርድር ጥሪ ስልታዊ መሆን አለበት። በእኔ ግምገማና እምነት ከአንድ ዓመት ከፍተኛ መስዋእት በኋላ ከህወሓት ወይንም ከትግራይ መከላከያ ኃይል ተብሎ በአዲስ ስያሜ ከሚጠራው አጥፊና አምካኝ ቡድን ጋር ግንኙነት፤ ውይይት፤ ንግግር፤ ድርድር፤ እርቅና ሰላም ለማካሄድ አይቻልም።

ከህወሓት ጋር እርቅና ሰላም የማይታሰብ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ለአውሮፓ የጋራ ማህበር፤ ለአሜሪካ መንግሥት፤ ለተባበሩት መንግሥታት አመራርና በተለይ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባላት በአስቸኳይ ማስታወቅ አለበት።

የብሄራዊ መግባባት ጥሪውን ሙሉ በሙሉ እየደገፍኩ፤ የትግራይን ሕዝብ ማን ይወክለዋል? ለሚለው የኢትዮጱያ መንግሥት ሌሎችን አማራጮችን የማመቻቸት ግዴታ አለበት። እርቅና ሰላም ሕዝብ ለሕዝብ እንዲሆን እመኛለሁ።

ከላይ ያቀርብኳቸውን ምክረ ሃሳቦች ለማስተናገድ ህወሓት የፈጸማቸውን ግፎችና በደሎች የሚያንጸባርቁ መረጃዎችን በአጭሩ ላቅርባቸው።

 1. የእልቂቱንና የውድመቱ መሰረት የሆነውን ጦርነት አቅዶና አስልቶ የጀመረው ህወሓት ነው። ይህ ጦርነት በሰባዊ ፍጥረት ላይ ያስከተለው ጭካኔ በታሪክ ተመዝግቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሚተላለፍ አልጠራጠርም። የወደመው ሃብትና ንብረት በቀላሉ የሚተካ አይደለም። ህወሓት የተከተለው መርህ፤ “ግደል፤ አቁስል፤ ድፈር፤ አዋርድ፤ ቀማ፤ አውድም፤ አምክን” ወዘተ የሚል መርህን የሚያንጸባርቅ ነው። ህወሓት ግደል ሲል፤ ወንድነትህንና ጀግንነትህን፤ የበላይነትህን የምታሳየው “አማራውን በመግደል ነው” የሚል ትምህርት እንደሚሰጥ ይወራል። በማንም አገር ያልሆነው በኢትዮጵያ ሆኗል።

 

 1. ህወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ሰባት ሽህ ትምህርት ቤቶችን ዘርፏል፤ አውድሟል፤ አባክኗል፤ እነዚህን ተቋማት መልሶ ለማቋቋም ብቻ የሚያስፈልገው መዋእለንዋይ ከአስር ቢሊየን ብር በላይነው።

 

 1. ህወሓት ወጣቱ የአማራና የአፋር ትውልድ ራሱን እንዳይችል ከሁለት ሚሊየንበላይ ተማሪዎች የትምህርት እድል እንዳይኖራቸው ወይንም ትምህርታቸውን እንዲያቆሙ አድርጓል።

 

 1. ህወሓት አራት ሽህ የጤና ጣቢያዎች ዘርፏል፤አውድሟል ወይንም አበላሽቷል፤ በመንግሥት የተደገፉ ሰማንያ ሁለት የጤና ጣቢያዎች፤ አራት መቶ አምሳ ሶስት የጤና ኬላዎች፤ አራት የደም ባንኮችና አንድ የኦክስጅን ፋብሪካ ዘርፏል፤ አውድሟል ወይንም አበላሽቷል። እነዚህን ለመተካት አስርት ቢሊየን ብር ፈሰስ እንደሚያስፈልግ ይገመታል

 

 1. በደሴ የሚገኘው የቲታ የመድሃኒት መደብር ተዘርፏል፤ ተኮላሽቷል፤ ለመተካት ወደ ሶስት ቢሊየን ብር ወጭ ይጠይቃል።

 

 1. በደሴና በኮምቦልቻ አርባ ፋብሪካዎችተዘርፈዋል፤ ተበላሽተዋል፤ አስራ አንድ ሽህ ሰራተኞች የስራ እድል ተነፍገዋል።

 

 1. የግል ንብረት የሆኑ አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሆቴሎች፤ሱቆችና ህንጻዎች ተዘርፈዋል፤ እንዲበላሹ ወይንም ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል። እነዚህን ለመጠገን ሁለት መቶ ስድሳ አንድ ሚሊየን ብር ያስፈልጋል።

 

 1. ህወሓት ነዋሪውን ሕዝብ በረሃብ እንዲሰቃይ ለማድረግ በሰራው ተንኮል አንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ ሄክታርየሰብል መሬት እንዲባክን አድርጓል፤ አርባ ሚሊየን ኩንታል እህል ወድሟል።

 

 1. እንኳን ለሰው ለእንስሳት ርህራሄ የማያሳየው ህወሕት ከብቶችን ሰብስቦ በጥይት ጨፍጭፏቸዋል፤ ዛፎችን እያነጠጣረ እንዲረግፉ አድርጓቸዋል። አንድ ግለሰብ እንዳሳሰቡት፤ “የጥይቱ ዋጋ ከዛፎቹ” ይበልጣል። አላማው ግን ማምከን ነው።

 

 1. ስድስት የኃይማኖት፤ ሁለት የባህል፤ ሃያ ሁለት የእንግዶችመቀበያና ማስተናገጃዎች ወድመዋል፤ ዋጋቸው ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ ነው። የመንዝ ጓሳ፤ የቦረና ሳይንት፤ የአቡነ ዮሴፍ ማህበረሰብ መገልገያ ቅርሶች፤ የወረይመኑ መናፈሻ ፓርክ እንዲወድሙ ሆኗል። ይህ የተደረገበት ዋና ምክንያት ከውጭ ጉብኝት የሚገኘውን የስራ እድልና ገቢ ለማማከን ነው። በአመት የሚገኘው ገቢ ጥፋት ሃያ አምስት ሚሊየን ብር ነው። በጉብኝት የሚመካው ህዝብ ቁጥር ሰላሳ ስድስት ሚሊየን ይሆናል። እነዚህ ወገኖቻችን በምን ገቢ ሊመኩ ይችላሉ? የሚለውን እናስበው።

ለማጠቃለል፤

 1. የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት አስቸኳይ ግምገማ መሰረት ሲታይ ህወሓት በአማራውና በአፋሩ ክልል ብቻ በቅርቡ ያካሄደው ውድመት መጠን ሁለት መቶ ሰባ ዘጠኝ ቢሊየን ብር ወይንም የአሜሪካ ዶላር አምስት ቢሊየን ስምንት መቶ ሽህ ይደርሳል።

ይህም ማለት የአሜሪካ መንግሥት ባለፉት አምስት አመታት ለኢትዮጵያ ከለገሰው አምስት ቢሊየን ዶላር በላይ መሆኑ ነው።

 1. እኔ ህወሓት በንጹሃን፤ በተለይ በአማራ ወጣት ሴቶች፤ እናቶች፤ መነኩሴዎች ላይ ያካሄድውን ጭካኔ፤ ግፍና በደል በቃላት ለመግለጽ ተመጣጣኝ ቃላት ላገኝ አልቻልኩም። በማይካድራ፤ በአንቶክያ ገምዛ፤ በጋሸና፤ በጭና ተክለ ኃይማኖት ቀበሌ፤ በደሴና በኮሞቦልቻ አካባቢዎች እና በጋሊኮማ አፋር የተካሄዱት ወንጀሎች ብቻ መስፈርት በማድረግ ከህወሓት ወራሪዎች ጋር እርቅና ሰላም የማይቻል መሆኑን አሰምርበታለሁ። ለዚህ ነው የጭፍጨፋው መሪዎችና ጨፍጫፊዎቹ በሃላፊንት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው የምለው።

 

 1. ህወሓት እንኳን ለንጹሃን ወገኖቻችን ቀርቶ ለእንስሳዎችም ምህረት አላሳየም። ከዛፎች ጋር ጦርነት ያካሄደን ቡንድ በምን ቃላት ለመግለጽ እንደሚቻል አንባቢው ያስብበት። እኔ አልችልም።

 

 1. የምእራብ መንግሥታት፤ በተለይ የአውሮፓ የጋራ ማህበር፤ የአሜሪካና የተባበሩት መንግሥታት ይህንን ሁሉ የግፍና የጥፋት መረጃ ያውቃሉ። ህወሓትን በሃላፊነት ሊጠይቁና ድርጊቱን ሊያወግዙ የማይችሉበትን ምክናያቶች የሰላሳ አምስት አገሮች መንግሥታትን ሲያፈርሱና ሲያድሱ ካደረጉት ድርጊት ለይቸ አላየውም። ኢትዮጵያ ሰላምና እርጋታ ኖሯት፤ በአፍሪካ ውስጥ የጃፓን ወንይም የደቡብ ኮሪያ አይነት ልማት እድገት እንድታሳይ አይፈልጉም።ይህንን አደገኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የተገነዘቡት ኢትዮጵያዊያንና ወዳጆቻቸው በዓለም ዙሪያ “በቃ” (NOMORE) ብለው የጀመሩት እንቅስቃሴ ለመላው ጥቁር ሕዝብ አግባብ ያለውና ወቅታዊ ጥሪ መሆኑን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሊገነዘቡት ይገባል። ለራሳቸውም ዘላቂ ጥቅም ይረዳቸዋል። አለያ መላው የጥቁር አፍሪካ አንድ ቢሊየን ሶስት መቶ ሚሊየን ሕዝብ ይንቃቸዋል፤ ለራሱ ጥቅም ሲል ፍትሃዊ አማራጮችን ይፈልጋል።

 

 1. ምእራባዊያን፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት መጠየቅ ያለባቸው እናንተ የምትደግፉት ሽብርተኛው ቡድን ህወሕት ይህንን የመስለ ጥፋትና ውድመት ስላመጣ የወደመውን ኢኮኖሚ መልሶ ለማቋቋም ድርሻችሁን ተወጡ ነው።

 

 1. የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ደግሞ ከአሁኑ ጀምሮ ህወሓትና ደጋፊዎቹ ለእልቂትና ለውደመቱ ተጠያቂመሆናቸውን በማያሻማ ደረጃ በመረጃ ተደግፎ ለአውሮፓ የጋራ ማህበር፤ ለአሜሪካ መንግሥት፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊና ለአፍሪካ አንድነት ማህበር መሪዎች የማስታወቅ ግዴታ አለብት።

 

 1. የአሜሪካመንግሥት፤ የምእራብ መገናኛ ብዙሃን፤ የተባበሩት መንግሥታት አለቃዎችና የአውሮፓ የጋራ ማህበር አባላት በተደጋጋሚ ህወሓት ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ ነው። ሳምንታት፤ ከዚያም ቀናት ቀርተውታል ሲሉ መቆየታቸውን ታሪክ መዝግቦታል። ሆኖም፤ አሁንም ቢሆን (ህወሓት እየተሸነፈና በብዙ ሽህ የሚገመቱ ተዋጊዎችን እየገበረና ወደ ትግራይ እየሸሸ ባለበት ሁኔታ) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አይን ያወጣ ውሸት ሲያስተጋባ ይታያል። አንድም ቀን ቢሆን የኢትዮጵያ፤ ፋኖ፤ የአማራው፤ የአፋሩ ልዩ ኃይሎችና የኢትዮጵያ መከካለክያ በጋራ ሆነው ለሰሩት ጀብዱ እውቅና ከመስጠት ተቆጥቧል። ለምን? ብየ እጠይቃለሁ። በተጨማሪ፤ አሁን የአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ያወጣው ሰነድ፤ ህወሓት መሸነፉን ይቀበልና ህወሓት ወደፊት ሽብርተኛነቱን ቀጥሎ ዱሮ እንደ ለመደው ወደ ሽምቅ ውጊያ ይሄዳል ይላል። እኔ የምጠይቀው፤ የአሜሪካ መንግሥት “በአፍሪካ ቀን ሰላምና እርጋታ ያስፈልጋል” የሚል እምነት ካለው ለምን ህወሓትን ይህንን አማራጭ እኛ አንደግፍም ለማለት አልቻለም? ነው።

 

 1. በዘላቂነትስገመግመው፤ ኢትዮጵያ ሃገራዊ (ብሄራዊ) ውይይትና መግባባት ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ መልካም ነው። ግልጽ እንዲሆኑ ከምመኛቸው አስኳል ጉዳዮች መካከል፤ ምክክሩ በምን ላይ? ለድርድር የማይቀርቡት ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ኮሚሽኑ የመንግሥት ተቀጥላ ነው ወይንስ ከመንግሥትና ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ ነጻ የሆነ? የሚሉት ይገኙበታል። በዚህ የምክክር ጉባኤ ህወሓት እንዲሳተፍ ከተደረገ ከድጡ ወደ ማጡ የሆነ ጉዞ እንደሚሆን አገምታለሁ።

 

 1. የሚዘገንንእልቂትና ውድመት ያካሄደው ህወሓት በሃላፊነት ካልተጠየቀ ብሄራዊ ምክክር ፋይዳ አይኖረውም።

 

 1. በአገር ቤትና በውጭ የምንኖረው ኢትዮጵያዊያን ከማህበረሰቡ ጋርና አግባብ ካላቸው ባለሥልጣናት ጋር በመመካከር የሞያ፤ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፋችን የመለገስ ግዴታችን እንድንወጣ አደራ እላለሁ። በዚህ በአዲሱ በዓል ለስጦታ የምናወጣውን “ለወገን ደራሹ ወገን” ስለሆነ በተቻለን መጠን ለተጎዱት ወገኖቻችንና ለወደመው ኢኮኖሚ አስተዋጾ እንደምናውለው አምናለሁ።

 

 1. በመጨረሻ፤የአሜሪካ ባለሥልጣናት በማንኛውም አገር ጣልቃ ሲገቡ አስበውበት፤ አቅደውበት መሆኑን አሳስባለሁ። የሚፈሩት ነገር ቢኖር በተጠቂው ወይንም ኢላማ በሆነው አገር ያለው የውስጥ ብሄራዊ አንድነትና ደፋርነት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ አገር ወዳድና ጀግና መሆኑን እየተገነዘቡት መጥተዋል የሚል ጭምጭምታ አለ። ለዚህ የሚበጀው ቆራጥነትና ህወሓትን ሙሉ በሙሉ ማማከን ብቻ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ

https/://satenaw.com/2021/12/16/terrorist-tplf-ravages-1-5-mil-hectares-of-agricultural-land-in-amhara-afar regions

(https://www.fanabc.com/english/terrorist-tplf-brutally-massacred-hundreds-of-innocent-civilians-in-amhara-region/)

https://www.youtube.com/watch?v=npGYEJJsNTI

 

December 22, 2021

dr aklog birara 2
Dr. Aklog Birara former Sr. Advisor at World Bank,, Commentator at Center for Inclusive Development (ABRAW) and a regular contributor to Zehabesha.com

2 Comments

 1. የምንኖርባት ዓለም ከቀን ወደ ቀን እየተንጋደደች እንደሆነ ግልጽ ነው። ሴት ወይም ወንድ ሆኖ በፊትህ በመቆም ጾታዬን አላውቅም ከሚሉ እብዶች ጋር እየኖርን ነው። አዎን ሰልጥነናል። ግን ስልጣኔአችን ሰይጣናዊ አርጎናል። ከቤቱ በራፍ ላይ ተቀምጦ የድሮን ፓይለት የሆነው እልፍ ሰዎችን ጨርሶ ለምሳ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ቁጭ ብሎ ኑሮውን የሚያጣጥምበት ዘመን ላይ ነን። ለዚያ የድሮን ፓይለት ውጊያ ከፊት ተሰልፎ እንደሚዋደቀው እግረኛ ሰራዊት አይደለም። የቪዲዮ ጫወታ እንጂ። አሁን በሃገራችን ውስጥ እየተደረገ ያለው የእብዶች ግብግብ ዘመን ተሻጋሪ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነው። በዝምታ የታሰረው አንደበታችን ከደም አፍሳሾችና ከዘራፊዎች ጋር ተሰላፊ አርጎናል። ለይቶለትም ድምጼን አሰማለሁ የሚለው እንደ ድር አራዊት በዘሩ ተሰልፎ ስለ ዘሩ ያቅራራል። ለሰው ልጆች ስብዕናና ልዕልና መቆም ተረስቷል። በቅርቡ አንድ ታክሲ ውስጥ አንድ ህንድ/ፓኪስታን የሆነ ሰው ኤርትራዊ ነህ ወይስ ኢትዮጵያዊ አለኝ። አፍሪቃዊ ስለው ነገሬ እንዳልጣመው ገምቶ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ያወራኝ ጀመር፡ እኔም በትህትና ወሬህን ቀይር ስለው ነገሩ በዚያው ቆመና ከአሰብኩበት ደረስኩ። በሻቢያና በወያኔ አማራ መከራውን ያየና በማየት ላይ ያለ ወገን ነው። ለምን ይህ ሁሉ መከራ በአማራ ህዝብ ላይ ደረሰ ለሚለው መልሱ ውስብስብ አይደለም። ሲጀመር ሻቢያ ራሱንና ታጣቂዎቹን የጋተው አማራ ጠል በሆነ ፕሮፓጋንዳ ነው። ይህኑ መርዝ ከነመለኪያው የዋጠው ደግሞ ወያኔ ሃርነት (ባርነት) ትግራይ ነው። ዛሬ በህይወት ያሉ የሻቢያም ሆነ የወያኔ ታጋዮችን ምስከር ማቆም ይቻላል። ለነገሩ ተግባራቸው የታየና እየታዬ በመሆኑ ምስክር ማቆም አያስፈልግም። ወያኔ ደግሞ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ነን የሚሉትን በሃሳብ የዘገዪ ጅሎች የችግርህ ሁሉ ምክንያት አማራ ነው በማለት የቀረውን መርዝ አስጨለጣቸው። የአማራ ወገኖቻችን መከራ ምንጩ ከእነዚህ ሃይሎች ክፋትና የፓለቲካ ሽርክናና ፍች የመነጨ ነው።
  አማራው ሰው ያምናል በዚህም የተነሳ ከንጉሱ ዘመን እሰከ ዛሬ ድረስ በድብቅና በይፋ ከላይ በተጠቀሱት ሃይሎች ግፍ ተሰርቶበታል። ይሰራበታል። የመንግስት ያለህ፤ በህግ አምላክ ተብሎ ለእርዳታ ሰው በማይደርስበት የሃበሻው ምድር ላይ መንግስት መንግስት ቢሉት ዋጋ ቢስ መሆኑን እንደ ድቄት ተበትኖአል፤ ዳግም እንዳይነሳ በማድረግ ደቁሰናቸዋል በተባልን ማግስት ነው ወያኔ ሽዋ ድረስ በመዝለቅ ይህ ነው ተብሎ የማይገለጥ ሰቆቃ የፈጸመው። አሁን ደግሞ መታናቸው፤ ገፋናቸው፤ መቀሌ ገቡ እየተባልን ነው። ተመልሰው እንዳይመጡ የሚከለክላቸው ምን ነገር አለ? ስለሆነም የወሎ፤ የሽዋ፤ የጎጃምና ጎንደር አማራ ወይም ለሰው ልጆች መብት ቆሜአለሁ የሚሉ ሃይሎች ሁሉ ከከተማ እስከ ገጠር በመሰልጠን፤ በመታጠቅ፤ ራሳቸውን የሚከላከሉበት የተቀናጀ ለዛሬም ለወደፊትም ለህዝብ ደጀን በሚሆን ነገር ላይ እስካልቆሙ ድረስ ለዳግመኛ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው። የእርስ በእርስ መናቆሩ፤ ፋኖን ለማዳከም መጣሩ ሁሉ ለአማራ ህዝብ ጉዳት እንጂ አይጠቅምም። ጄ/ አሳምነው ጽጌ ይህ ሁሉ ጉድ እንደሚመጣ አስቀድሞ አውቆ ነበር። ግን በዚህ በዚያም ገዳይና ተገዳይ ሳይታወቅ በግርግር ሁላችንም ወደ እማንቀርበት ዓለም ተሸኝቷል። ለዚህ ነው የሃበሻው ፓለቲካ የመጠላለፍ ፓለቲካ ነው የምለው።
  ኢህአደግ (ወያኔ) ከሥልጣን ከወረደ በህዋላ የተፈጸሙ ጎዶች ሁሉ መልስ አላገኙም። ለምሳሌ ኢ/ስመኘውን ማን ገደለው? ጄ/ጻዕረና ጓደኛውን የገደለው እንደተባለው አስር አለቃው ነውን? አምባቸውንና የስራ ባልደረቦችን ማን ገደላቸው? ጄ/ አሳምነው ነው ከተባለስ ለምን ተገደለ? ለምን አልተያዘም? ከዚህ በላይ ብዙ አጠያያቂው ነገር ደግሞ ደቆስነው የተባለው ወያኔ መድፍ፤ ታንክ፤ አየር መቃወሚያ ይዞ ሽዋ ድረስ እስኪደርስ ለምን ዝም ተባለ? ይህ የሚያሳየው ትላንትም ዛሬም አማራን ለማጥፋት የሚሰሩ ሴራዎች እንዳልቆሙ ነው። ይህ እንግዲህ በወለጋና በሌሎች አካባቢዎች በስመ አማራ ከሃገራችን ውጡ ከሚሉ እውሮች ጋር ያለውም ግብግብ ሊታወቅ ይገባዋል። የእስከ ዛሬው የውጭ ሃይሎች በእኛ ላይ እቃ እቃ መጫወት አልታየኝም አልገባኝም የሚል ካለ አሁን እንሆ አሜሪካና ተመድ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን የፓለቲካ ፌዝ ልብ ማለት ያለፈውንም የምዕራባዊያን ሴራና ተንኮል ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በጥሞና በሃሳብ መፋለምን እንደ ውርደት ቆጥሮ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው አፍሪቃዊ እይታ መሞረድ ያስፈልገዋል። በቅርቡ በጋና ምክር ቤት አባላቱ በሃሳብ ሳይግባቡ ቀርተው ቡጢ ሲገጥሙ ማየት ምንኛ ያስጠላል። ይህን ድክመታችንና ሌላውን የዘር የቋንቋ የሃይማኖትና የጎሳ መንሸራተት እየተጠቀሙ ዛሬ በናይጄሪያ፤ በካሜሩን በሌሎችም የአፍሪቃ ሃገራት መከራ የሚያዘንቡት ነጮች ናቸው። 54 ሃገሮች ሃገር ነን ብለው ባንዲራ የሚያውለበልቡባት የአፍሪቃ አህጉር አንድ ሆነው መቆም እስካልቻሉ ድረስ የዓለም መሳለቂያ እንደሆኑ ይቀጥላሉ። የአንዲት ሃገር ነጻነት የሚለካው ባንዲራዋ ከፍታ ቦታ ላይ ሆኖ በመውለብለቡ ብቻ አይደለም። የሰዎች የዲሞክራሲ መብቶች ሲከበሩና አንድ አገልጋይ ሌላው ተገልጋይ መሆኑ ሲቀር እንጂ።
  በራሱ ዘፈንና የግል ታሪክ የሰከረው የወያኔ ቡድን አሁን ደግሞ እንገነጠላለን ይላል። እኮ በሉ ሂድ ተገንጠሉ። ልብ ላለውማ የተገነጠሉ ሃገር ነን ባዮች ዛሬ የቆሙበትን ሁኔታ በማጤን ትርፍና ጉዳትን ባሰላሰለ ነበር። ወያኔ ሂሳብ ማወራረድ እንጂ ሂሳብ መስራት አያውቅም። ጄ/ጻድቃን በቅርቡ በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንዴት እንዲህ ያለ ውድመት በአማራና በአፋር ክልል ትፈጽማላቹሁ ሲባል እነርሱ በትግራይ ካወደሙት አይበልጥም ነበር ያለው። ይህ አስተሳሰብ ነው ዛሬ ላለንበት የመከራ ዶፍ ያደረሰን። ግን እኮ የወያኔ መሪዎች እነርሱ አይሞቱ፡ የሚረግፈው የድሃና የገበሬ ልጅ ነው። የእነርሱ ቤተሰቦችና ዘመዶች ጭራሽ ወደ ግንባር አይሄድም ብዙዎችም በሃገር ውስጥ የሉም። ወያኔ ድርቡሽ ነው ስንል በመረጃ ነው። የትግራይ ህዝብ ዋና ጠላቱ ሻቢይ ወይም አማራ ወይም ደግሞ የአብይ መንግስት አይደለም። ራሱ ወያኔ ባርነት ትግራይ ነው። ትግራይ ውስጥ ያላችሁ ይህን ፈትሹ። ግልጽ ሆኖ ይታያቹሃል። ዝምታ አያዋጣም። መንቃትና ወያኔን ከጀርባቹሁ ላይ ማውረድ ነው። በቃኝ!

 2. I am sorry to say but I have to say that it is very embarrassing to see our intellectuals being victims of very shallow, emotion-driven, highly skewed, short-sighted, unproductive, and above all opportunistic way of dealing with a highly toxic and deadly political system of ethnic identity. Needless to say, the system created by TPLF a long time ago and became constitutional and operational three decades ago has continued with no meaningful element of a desirable change.
  The only difference is that those who had been very instrumental in carrying out the policies and programs of the deadly politics of ethnic identity took over the thorn by purged out their creator and master (TPLF). They kept the very chronically ill system in a much worse manner of bitterness and scope under their hegemonic control of power simply by renaming themselves as Prosperity, a name directly driven from a religious sect which is the product of a highly deceptive or misleading way of interpretation of the Great BOOK (the Bible).
  Yes, TPLF should be hold responsible and accountable for what it did and what it is doing and must be rejected and defeated if a democratic and peaceful Ethiopia should become a reality. But it is politically stupid and morally bankrupt not to reject and defeat those who let the very deadly criminal political system of TPLF/EPRDF continue under their much more ruthless hegemonic political grab.
  Outrageously enough, many of our intellectuals totally lost the very real sense and value of intellectualism which is supposed to rescue society from any catastrophic situation, including a political system of tyranny of ethnocentrism.
  I hate to say but I have to say that it is painful to witness many compatriots including well–educated and experienced intellectuals being victims of losing or abandoning the very demand of the people for a change of a fundamental democratic political system, not to see the continuation of the same if not a much worse political system of ethnocentrism driven by a faction of EPRDF.
  Yes, it is embarrassing to witness those intellectuals being victims of the very dirty politics of blaming others whereas losing the courage to stay firm on the very principle and objective of making a truly democratic society by forcing those who keep playing a very hypocritical, cynical, conspiratorial, dishonest, and above all criminal political game either to come to the negotiating table or getting rid of them with a legitimate and well-organized political action of the people.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.