ብርሃኑ ነጋ እና መለስ ዜናዊ የአንድ ዘመን እኩያ ተማሪዋች – ሄኖክ ለይኩን

የብርሃኑ ነጋ እህት እስካለ ነጋ (ነፍስ ይማር) እና መለስ ዜናዊ የአንድ ዘመን እኩያ ተማሪዋች ነበሩ። ሁለቱም በ1965 ዓመት ምህረት ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ጎበዝ ተማሪዋች ነበሩ።

አስካለ ነጋ ከመድሃኒአለም መለስ ዜናዊ ከዊንጌት በብቸኝነት ከመላ የሀገሪቱ ትምህርት ቤት ተማሪዋች ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ሁለቱም ዮኒቨርስቲ በመግባታቸው ከንጉሱ በወር በወር የመቶ ብር ተከፋይም ነበሩ።

አስካለ ነጋ የኢህአፓ ሴል ሆና ስትንቀሳቀስ በመንግስት ሃይሎች አይን ገብታ መሐል አራት ኪሎ ከዩኒቨርስቲው በር ላይ ራሳዋን የጉሊት ሴት አስመስላ ስትንቀሳቀስ ተቱኩሷባታ ህይወቷ አልፍል።

መለስ ዜናዊ ደሞ ትምህርቱን አቋርጦ፤ ጭካ ገብቶ፤ ዘመን ጠብቆ፤ ድል ቀንቶት፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ በስተመጨረሻ ባዮሎጂ ስራውን ሲጨርስ አልፎል።

ብርሃኑ ነጋ የእህቱን የአስካለ ነጋ የተማሪ ቤት ጓደኛ፤ የመለስ ዜናዊን እውቀት እና ጉብዝና በሚገባ ያውቅ ነበርና በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ መክሮት ያውቃል።

“አሁን አንተ የታላቂቷ ሀገር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ነህ። በአንተ የመሪነት ዘመን ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲ ወደ እኩልነት ወደ ፍትህ ወደ ስልጣኔ ተለወጠች የሚል ታሪክ ከመስራት ወደ ኃላ እንዳትል። ከዚህ ውጭ ምንም የምትፈልገው ነገር መኖር የለበትም። ለአንተ ካለህ ብቃት አንፃር ገንዘብ፣ ስልጣን፣ እውቅና ምንም ናቸው።” ሲል ብርሃኑ ነጋ መለስ ዜናዊን መክሮታል።

መለስ ዜናዊ ግን የብርሃኑ ነጋን ምክር የሩብ ሩብ ለመፈፀም አንዳች ፍላጎት ሳይኖረው ዘመኑን ጨረሷል። መለስ ዜናዊ ‘የጉራጌ ነፃ አውጪ’ እያለ የሚቀልድበትን ብርሃኑ ነጋን ሰምቶት ቢሆን ኖሮ የሀገራችን ታሪክ ዛሬ ላይ ሌላ በሆነ ነበረ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ተከበረ

ብርሃኑ ነጋ ምክሩን አልሰማ ብሎት ሀገርን ከድጥ ወደማጡ ሲያወረዳት ሲያይ በመለስ ዜናዊ ላይ ነፍጥ ለማንሳት አላቅማማም።

ዛሬ ብርሃኑ ነጋ በመለስ ዜናዊ እና በድርጅቱ መቃብር ላይ የኢትዮጵያ ካስማ በሆኑት በአፋሮች መንደር አፋሮችን መስሎ በክብር ቆሞል።

ብዙዋች ብርሃኑ ነጋን ለምን አምርረው እንደሚጠሉት ይገርመኛል። የቆሎ ተማሪ ‘ውሻ ለምን ይጮኽብሃል’ ሲባል ‘ቁራሹን ስለምወስድበት’ ብሎ ይመልሳል። እናም የብርሃኑ ነጋ ነገር የግር እሳት የሚሆንባቸው ሰዋች የመለስ ዜናዊ ነገር እየሆነባቸው ይሆንን??? አላቅም።

ምንም ቢሆን ግን ሰውዬው የት መገኘት እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያቅ ፕሮፌሰር ነው።

 

6 Comments

  1. ይህ አጭር የፖለቲካ ህይወት ትርክት የፖለቲካ ታሪካችንን አሳዛኝነትና አስከፊነት ለማሳየት ያለውን ጠቀሜታ መቀበል አያስቸግርም።
    ፈተናውግን ከእንዲህ አይነቶች አስከፊ ተሞክሮዎች መማርና የተሻለ ማድረግ ተስኖን ለዘመናት ከመጣንበት ክፉ አዙሪት መውጣት አለመቻል ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ከምንገኝበት ክፍለ ዘመን አንፃር ሲታይ እጅግ በባሰ የመከራና የውርደት አባዜ ውስጥ የመገኘታችን ግዙፍና መሪር ሃቅ ነው።
    ይህ ደግሞ ያለምክንያት ሳይሆን እንደ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ዶር/ መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እና ሌሎችም የዚያ ትውልድ ሰዎች እድሜ ልክ ኖረንበታልና ታግለንለታል በሚሉት የእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለውጥ ንቅናቄ ላይ እጅግ አስከፊ የሆነ የአድርባይነት በረዶ ቸልሰውበት ከተረኛ ኢህአዴጋዊያን ጋር የፖለቲካ አመንዝራ ውስጥ መዘፈቃቸው ነው።
    ያ ትውልድ በወቅቱ በነበረው የአገር ውስጥ የጃጀ ፍፁማዊ የዘውድ አገዛዝ ምክንያት በወቅቱ ከነበሩት ሁለት ዓለም አቀፍ ጎራዎች አንዱን መታገያ አድርጎ እንዲቀበል ከተገደደ እና በዚህ ምክንያት ከተገደለና ከተገዳደለ ትውልድ ከምር ተምሮ የተሻሉ ሆኖ እና አድርጎ ከመገኘት ይልቅ ያንን ትውልድ እያብጠለጠሉ ከእርሱ በከፋ አኳኋን በተረኝነት አዙሪት ውስጥ ለምንገኝበት ወንጀለኛ ሥርዓተ ኢህአዴግ እራስን በፍርፋሪ ለቃሚነት አሳልፎ ከመስጠት የከፋ የፖለቲካ አዙሪት የለም።
    ለዚህ ደግሞ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ እና መሰሎቻቸው በላይ የተሻለ ማሳያ የለም። ለዚህ ነው የአድርባይነት (የልክስክስነት) ፖለቲካ ሰብእና በሦስት ዓመታት ውስጥ ለተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ከዓመት ወዲህ ደግሞ ባለጌና ጨካኝ ኢህአዴጋዊያን በሁለት የሥልጣን ሽሚያ አንጃዎች (ህወሃትና ኦህዴድ/ብልፅግና) ተከፍለው ለሚያካሄዱት የእርስ በርስ እልቂት (ወንድም ወንድሙንና እህቱን ወይም እህት እህቷንና ወንድሟን ገድለው የሚፎክሩበት ክፉ ልክፍት) ተጠያቂ መሆኑን ለማስተባበል የትርክት ድሪቶ መደረት ቢያንስ አስከፊ ነውር ነው ብሎ በግልፅና በቀጥታ መናገር ትክክል የሚሆነው።
    እናም የሚሻለው እውነትን ስለእውነት ተነጋግሮ ከአደገኛው የፖለቲካ ጋግርት ለመላቀቅ የጋራ ጥረት ማድረግ እንጅ በከንቱ የመሞጋገሱ አስቀያሚ ልማድ የትም አያደርሰንም!

  2. ሔኖክ ምን አይነት ስብእና እንዳለህ ማወቅ የምትችለው አንተ ነህ ብርሃኑ ነጋ እንዲህ የምትዘምርለት ሰው አልነበረም እኛ የተቸገርነው እንዳንተ አይነት አዝማሪዎች እዉነቱን ሃሰት ሃሰቱን እውነት እያደረጉ የሚያቀርቡልን በመብዛታቸው ነው ድካምህ ከንቱ ሆነ እንጂ የጠቅስካቸውን ሰዎች ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን አሳመርኩ ብለህ የነገርክን አንድ እውነታ አለ ብርሀኑ ነጋ አንዳርጋቸውና መለስ የቆየ ወዳጅነት እንዳላቸው ምንም እንኳን እኛ ጠንቅቀን ብናዉቀዉም ካንተ ከወዳጃቸው መነገሩ ጥሩ ነው። እንደ ተዋጊም እንደ ፈላስፋም እንደ ሃገር ወዳድም አድርገህ አቅርበሃቸዋል እውነታዉ ግን ጩሉሌ ያራዳ ልጆች ስልጣንና ጥቅም የት ሊገኝ እንደሚችል ጠንቅቀዉ የሚያዉቁ ናቸው ፐሮፌሰር የሚባለውን ቅጥያ እንኳን ብትተወው ይሻላል ለማንኛዉም ጊዜ ይፍረድ። ለማንኛውም በብርሃኑ ቦታ ዶር በፍቃዱ በቀለ ዶር ዳኛቸውን እና ሌሎች ለሃገር ቀን ክሌሊት የሚደክሙ ዜጎችን ብታስገባበት ያንባቢን ክብር ታገኝ ነበር።

  3. የሃገራችን የፓለቲካ ችግር ቆሻሻ ክምር ላይ እንደሚያነፈንፍ የተራበ ውሻ የተቀበረን ነገር ጎትቶ በማውጣት ሃገር እንዲገማ ማድረግ ነው። በሃበሻው ምድር እጣቱ ጠቆሞ ሰው ያላስጠለፈ፤ በሃሰት ያልመሰከረ፤ በዘር የፓለቲካ አዙሪት ገብቶ ሌላውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያልጎዳ፤ ከዚያም አልፎ ከሰው ልጅ ባህሪ የማይጠበቁ ነገሮችን የፈጸሙ የግፍ ደብዳቢዎች፤ ገዳዮች አፋኞች የሚራወጡባት ምድር ሆና እያለ ከእጣት እጣት ይበልጣል የሚሉን አሁን በቀል ፓለቲከኞችና ተምረናል ባዪች የሚሰጧቸው አስተያየቶች አፍራሽ ናቸው። ዛሬ በአፋርና በአማራ ወያኔ ለሚያደርሰው ግፍ የ 60 ዎቹ የፓለቲካ ውሾች የፈጠሩት የትርክት ፓለቲካና የከፋፍለህ ግዛው ሴራ ውጤት ነው። የፓለቲካ አራዊትነት በገጠርና በከተማ ሥር በሰደደባት ሃገር እከሌ እንደዚህ ነበር ያ እንዲያ ነበር እያሉ መቀላመድ ለወገንም ለሃገርም ጭራሽ አይጠቅምም።
    አንድ ፈላስፋ ሲናገር ” ሰው በቀን ለደቂቃም ቢሆን ያብዳል” ይለናል። የእኛው እብደት ግን ዘመን ተሻጋሪና ተላላፊ በሽታ በመሆኑ አዲሱን ትውልድም እኛን ምሰል እያለን ለሞት እየማገድነው እንገኛለን። እኔ ፕ/ር ብርሃኑም ሆነ አንዳርጋቸው ሃገራቸውን ከልባቸው እንደሚወድ እረዳለሁ። ያ ባይሆን ኑሮ ወያኔ ዘብጥያ ባላወረዳቸውም ነበር። ደግሞ አንድ ነገር ሊታወቅ ይገባል በኢህአፓ ውስጥ የነበሩ ልጆች እይታቸው ጥቅል የሃበሻ ህዝብን የሚወድ እይታ ተላብሰው ነው ፓለቲካውን የተጋቱት። በጭራሽ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ነገር እናርግም ቢሉ ህሊናቸው አይፈቅድላቸውም። ይህ ከወያኔና ከሌሎች ዘር በቀል ድርጅቶች የሚለያቸው ዋንኛው ገጽታቸው ነው። ድርጅቱ እውነተኛ ህበረ ብሄራዊነት የነበረው ነበርና። የዛሬው የክልል ጡሩንባ ሰውን ከማደንቆሩ በፊት ሌላም ጡርንባ ይነፋ ነበር። ኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም የሚል። የሃበሻው የፓለቲካ እይታ ሸፋፋ ነው። ዶ/ር አብይ አማራን አስጨረሰ፤ ከንቲባዋ እንዲህ አለች፤ የኦሮሞ ክልል ፕሬዚዳንት ይህን ተናገረ እየተባለ የውሸትና የተጋነነ ወሬ በማዛመት ሳንቲም የሚሰበስቡ ስንቶች እንደሆኑ እናውቃለን። በፍልሚያና በጨበጣ የፓለቲካ ውጊያ ውስጥ ማን ማን መሆኑ የሚለካው በቃሉና በተግባሩ ነው። ፕ/ር ብርሃኑንም ሆነ አንዳርጋቸው ጽጌን እኔ በግል አላውቃቸውም። ግን ይህም ያም ቢንጫጫ፤ የዚህም የዛም ጓደኛ ነበሩ ቢባል ዋጋ የከፈሉ አሁን በሃገራቸው ላይ ሆነው የሚታገሉ ወገኖች በመሆናቸው ደስ ይለኛል። ይህ በስማ በለው ወሬ የሚነገሩ ሃገር አፍራሽና እንቅፋት ፈጣሪ ጽሁፎችም ሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከተልካሻ እይታ የሚመነጩ አብረን እንዳንራመድ በፈጠራ ወሬ ሰውን የሚያደነቁሩ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው።
    አሁን ሃገሪቱ በውጭና በውስጥ ጠላቶች ተወጥራ በቢሊዪን የሚቆጠር ሃብትና ንብረት ወድሞ ሰው ከቀየው ተፈናቅሎ ሃገር ወገን ያሉ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ገብተው እየተማገድ በሚገኙበት በዚህ ሰአት ላይ የመሸታ ቤት ወሬ የሚመስል እንዲህ ያለ እኩይ ነገር መጣፍ ለማንም አይበጅም። ምድሪቱ ታምሳለች። አማሽና በዳይ እየተራወጠ ይገኛል። መረጃ ይዞ የተሰራን ክፋት የሚያጋልጥ፤ የተጎድ ወገኖችን ሰቆቃ አዳምጦ የሚዘግብ፤ እንጂ የዛሬ 100 አመት ወይም ከዚያ በህዋላ እንዲህ ሆነ የሚሉን ሰላቢዎች ጭጭ ቢሉ ለሃገርና ለወገን ይጠቅማል። ዛሬ የትግራይ ወራሪ ሃይል አሮጊቶችንና መነኩሴዎችን የሚደፍር፤ ያለምንም ርህራሄ ሰውንና እንስሳን በጥይት የሚደበድበት ጊዜ ላይ ሆነን ፕ/ሩ መለስን እንዲህ ብሉታል ብሎ ማላዘን ጠቃሚነት የለውም። ወያኔ ከጅምሩ የሞት መልአክ እንደሆነ ለፕ/ሩ ዘግይቶም ገብቶት በሃሳብ ወያኔን ተፋልሟቸው ታስሮና ከሃገር እንደወጣ ግልጽ ነው። ስለዚህ አሁን ተመልሶ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑ ደስ ያሰኛል እንጂ አያስከፋም። በሥራው እንመዝነው። ያለፈውን ትፉት!
    ማሳሰቢያ – በመላ ሃገሪቱ በትግራይ ተወላጆች ላይ ወከባና እስራት እየተደረገ እንደሆነ እየሰማን ነው። ይህ መፈተሽ አለበት። በጥርጣሬም ከታሰሩ ነገራቸው ታይቶ ዋስ ሰተው ህግ ውስጥ እንዲቀርቡ ማድረግ እንጂ አጉሮ መያዝ ወያኔን መሆን ነው። ሌላው የተጠቆመበት ሁሉ ወያኔ አይደለም። ራሳቸው ወያኔዎች እየጠቆሙ ሰውን ለማስመረር የሚያደርጉት ሴራም እንዳለ የጸጥታ ሃይሎች ማወቅ ይኖርባቸዋል። ወያኔ የሰሜን እዝን ሲያጠቃ ከወያኔ ጎን አንሰለፍም ብለው ከሰራዊቱ ጋር አብረው የተዋደቁ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል። ትግራይ ዶ/ር ደብረጽዪንና ጌታቸው ረዳን ብቻ አይደለም የወለደችው። በህቡዕና በይፋ ወያኔን ከልባቸው የሚጠሉ፤ ኢትዮጵያዊነትን የሚወድ ዛሬም አሉ ወደፊትም ይኖራሉ። ወያኔ ካልተቀበረ የትግራይ ህዝብ በሰላም አይኖርም። ይህን ማድረግ የሚችለው ደግሞ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ጠብቃችሁ እዪ። ይሆናል!

  4. ተስፋ ነብስህ ተሰቃየች የትግሬ ወንጀል ደምህ ውስጥ ገብቶ ብዙ አላስቸግርህም 10 ትግሬ ክ5.5 ሚሊዮን ህዝብ መጥራት ትችላለህ? አንተን ጨምሮ።

  5. ብዘገይም ከላይ የተስጡት አስተያየቶች ከተሰፋ በስተቀር ከድንቢጥ ወፍ አፍ ከሚፈልቀው ጩኸት ያነስ ነው።ለተስፋ ሁልጊዜ የምትጽፈው አስተያየት እውነተኛ እና ጠብ ስለማይል በርታበት።ለነቢዩ ደግሞ ነቢዩ የሚለውን ስም ራስህ ብትሰጠውም አማረኛ ፊደል መጻፍህ እንጂ ነፍስህ የተሰቃየች በሞገድ እና በጠባብነት እንዲሁም ለከርስህ መሙያ ስሙኔ ወይም ሳንቲም ፍለጋ በመሆኑ ከገንጣይነት ለመላቀቅ ቆዝምበት። የጠገናው ጎሹ እንኳን ያው የተለመደ መውደቂያ ያጣ ያበደ ውሻ ነውና አይፈረድበትም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share