238 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በአሸባሪው ህወሃት ዘረፋና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል

ታህሳስ 04 ቀን 2014(ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች በ238 የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋና ውድመት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሽብር ቡድኑ በወረራ በገባባቸው አካባቢዎች በባንኩ ሰራተኛች ላይ ግድያ እንዲሁም በተቋሙ ላይ ዘረፋና ውድመት ፈፅሟል።
አሸባሪው ሃይል በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት ዲስትሪክት ስር ባሉ 238 የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋና ውድመት አድርሷል ነው ያሉት።
ከአሸባሪው ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የባንኩ ቅርንጫፎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አረጋግጠናል ያሉት የባንኩ ፕሬዚዳንት በመቀሌ የሚገኙት 61 እና በሽሬ 59 የባንኩ ቅርንጫፎች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን አይታወቅም ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ ገንዘብ፣ ኮምፒተር፣ ጀነሬተሮችና ሌሎች ንብረቶችን በመዝረፍ የኤቲኤም ማሽኖችን በመስበርና በማውደም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል።
ከወራሪው ነፃ የወጡ አካባቢዎች በባንኩ ቅርንጫፎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ለማወቅና ዳግም ስራ ለማስጀመር የጥናት ቡድን መሰማራቱን ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ በባንኩ ቅርንጫፎች ላይ የሰነድና የንብረት ውድመት ቢደርስም የደንበኞች መረጃ ግን ሙሉ በሙሉ ማዕከል ላይ ስለሚገኝ ደንበኞች “መረጃዬ ይጠፋል” የሚል ምንም አይነት ስጋት ሊኖራቸው አይገባም።
ከአሸባሪው ህወሃት ነፃ በወጡ አካባቢዎች እስካሁን 12 የባንኩ ቅርንጫፎች ዳግም ስራ መጀመራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ደግሞ 30 የሚሆኑትን ስራ ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
_ አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!!!

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share