ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ

264931312 4927451297335612 6545641707203542032 nየመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ።
የልዩ ዘመቻዎች ኃይል፣ የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይል እና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ሌተናል ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሽብር ቡድኑን የመደምሰስ ግዳጅ በድል መገባደድ እና ለቀጣይ ወሳኝ ተልዕኮ መነቃቃትን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ በግንባር በተካሄደ መድረክ ላይ ተገኝተው ነው።
ቀይ መለዮ ለባሾቹ በወሳኝ ወቅት አስቸጋሪና ፈታኝ ግዳጆችን በድል በመወጣት በደማቅ ቀለም የተፃፈ ታሪክ መስራታቸውን ተናግረዋል።
ጀግኖቹ ከሰሞኑ በጣርማበርና ዙሪያገባዎቹ የፈፀሙት አንፀባራቂ ድል የጠላትን ቅስም የሰበረ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ባጫ አሁንም የደም የመስዋዕትነት እና የድል አድራጊነት ምልክት የሆነውን ቀይ መለዮዋቸውን አጥልቀው ለዳግም ድል መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የልዩ ዘመቻዎች፣ የሪፐብሊኩ ኃይልና አየር ወለዶች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እና የምድር ላይ ድሮን መሆናቸውን እንዳስመሰከሩ ሁሉ የኅልውናችን ጠንቅ ሆኖ በአንዳንድ ፅንፈኛ ምዕራባዊያን የሚጋለበውን የሕወሓት ሽብር ቡድን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን ብለዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ኅዳር 30/2014 (ዋልታ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.