የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው እያሉ አሸባሪው ህወሓትን እየሞገቱ ነው

263744645 2156946001123403 3646063793688042234 n
ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎትሚኒስትር
የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው እያሉ አሸባሪው ህወሓትን እየሞገቱ ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑ በትግራይ እናቶች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አሰመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የትግራይ እናቶች በአሸባሪው ህወሓት ስብሰባዎች ላይ አንገኝም እያሉ ነው።
ተገደው የተገኙትም ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው ብለው እየሞገቱ ነው። በዚህም ምክንያት አሸባሪው ቡድን ሕዝባዊ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።
አሸባሪዎቹም እርስ በእርሳቸው መናቆር አብዝተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የአሸባሪው ቡድን ግብዓተ መሬት ሩቅ እንዳልሆነ ያሳያል ብለዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፤ ተላላኪው ሸኔ ላይ አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ ነው፤ እርምጃውም ይቀጥላል ብለዋል።
(ኢ ፕ ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.