የሠዉነት ልክ በቁም ነገር እና ተግባር ….ወይስ ወንበር  ?

በኢትዮጵያዊነት ፭ ሽ ዓመት ታሪክ የአደር ባይነት ባህል እና ልምድ ወደ ዕምነት ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን በተለያየ ጊዜ በልዩ ልዩ የታሪክ አጋጣሚ ከታሪካችን እንማራለን ፡፡

በቅርብ ዘመናት በእናት አገር እና በወገን  ላይ ክፉ ስራ እና ሴራ የፈፀሙት እና ያስፈፀሙት በወንበር (ኃላፊነት) ሊጠየቁ ሲገባ ከሳሽ እና ወቃሽ በመሆን ፈራጂ እና ነዳጂ ሲሆኑ አይተናል ፤ እያየን ነዉ ፡፡

በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች እናት አገር እና ህዝቧ ያሳለፏቸዉ የመከራ ዘመን እና ከዚህ በተቃራኒ የወንበር አምላኪ እና ተላላኪ ተስፈኞች የነበሩ እና የሚገኙ የታሪክ ቀበኞች  አበዉ “በጨዉ ደንደስ በርበሬ ተወደስ ” እንዲሉ  ለክፉ ቀን ደራሾችን በመግፋት እና በማጥፋት ከዘመናት ጀምሮ ተሰርቷል፡፡

ለአብነት ከሚጠቀሱ የወንበር ማክበር እና ማምላክ ክፉ ልማዳችን ከልማድ አልፎ   የተለጠፉት ለአስረጅ በኢጣሊ ፪ ኛ ዙር የግዛት መስፋፋት እና ቅዥ ግዛት  አባዜ ተከትሎ ባለወንበር እግሬ አዉጭኝ ብሎ ባህር በመሻገር መገለጫችን አስከመሆን መደረሱን ከኋላ ታሪካችን ድሮ እና ዘንድሮ ማየት ይቻላል ፡፡

ዐፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት 1889 አስከo 1913 .እ.ኤ.አ.

ዐፄ ኃይለስላሴ 1930 አስ 1974 እ.ኤ.አ.

1974 ዓ.ም. አስከ 1991.እ.ኤ.አ.

የነበሩትን ስርዓተ መንግስት ስንመለከት ጀግና እና ለአገር አንድነት እና ህዝብ ደህንነት በፍፁም የአገር ፍቅር ስሜት የመሩት ዕምየ ምኒሊክን የሚያህል እንዳልነበር ከታሪክ እና መልካም ስራወቻቸዉ እንረዳለን፡፡

ዕምየ ሚኒሊክ በዘመኑ የነበሩት የህዝብ እንደራሲዎች እና ባለስልጣን የምትተኩኝ እናንት ናችሁ በማለት ያበረታቱ ነበር ፡፡ ቂም በቀል አያዉቁም ነበር ፡፡ ፈሪሃ እግዜያብሄር ስለነበራቸዉ በዕዉነተኛ ሠባዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት እና ልበ ሙሉነት በዉስጣቸዉ ስለነበር በራስ መተማመናቸዉ ከፍተኛ የነበሩ የጥቁር ህዝብ  የነፃነት አባት ነበሩ ፡፡

ሆኖም ከሳቸዉ ህልፈተ ሞት በኋላ ለዕዉነት እና ለአገር ዕድገት እና ህልዉና ብልፅግና ከመኖር ለወንበር እና መንበር የመኖር እና የመመለክ ልማድ ተንሰራፍቷል፡፡

በንግስት ዘዉዲቱ የተጀመረዉ ወንበር የማስጠበቅ ትንቅንቅ  ከኢጣሊያ ሽንፈት በኋላ ለአገር ነፃነት ጉልህ ተጋድሎ ያደረጉ ስመ ጥር ያገር ባለዉለታወች ከሹመት እና ሽልማት ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡

ይህ በተከታይ መንግስታት በተለያየ መልኩ ቀጥሎ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ ከመነረበረ ስልጣን እና ፖለቲካ ዓመለካከት በተጨማሪ ማንነት እና ኢትዮጵያዊነት ተኮር ጅምላ ማግለል እና መግደል ቀጥሎ ዛሬ አገሪቷ እና ህዝብቧ ለሚገኙበት ምስቅልቅል የታሪክ እና ጊዜ ግጥምጥሞሽ ላይ ይገኛሉ፡፡

የቀድሞዎችን እና የአሁነኖችን ፍርደ ገምድል የመንበረ ስልጣን አፋቃሪ እና ተባባሪ አንድ የሚያደርጓቸዉ ህዝባዊ ወገንተኝነታቸዉን እና አለኝታነታቸዉን ያለምንም ቅድ ሁኔታ እና ጥቅም ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ በሆነ ከያት ቅድመ አያቶቻቸዉ በደም እና አጥንት ስጋ በለበሰ የአገር ፍቅር እና ክብር ዕግራቸዉን ለጠጠር ፤ደረታቸዉን ለጦር ብለዉ ቤዛ ለሆኑ እና ለሚሆኑት የነበራቸዉ እና ያላቸዉ ስሜት ከፖለቲካ ስልጣን ከሚገኝ ጥቅም ጋር መመልከታቸዉ ነዉ ፡፡

ልዩነቱ የዘመናች በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስም እንጂ በተግባር አንድን ህዝብ እና አገር በፍርኃት እና በጥላቻ በመለየት  ጠላት እና ወዳጂ የማድረግ ዝንባሌ እና አባዜ ነዉ፡፡

ከዚህ ዉጭ ወንበር እና መንበረ ስልጣን የማምለክ እና የመመለክ ፍላጎት እና ተግዳሮት ቅርፅ እናይዘት ከመለወጥ ዉጭ ተቀመጥ በወነወበሬ ….ተናገር በከንፈሬ  መኖሩ ዕዉነተኛ መንገድ ከመከተል ይልቅ ፍሬ አልባ መራመድ ሶስት ወደ ፊት ሁለት ወደ ኋላ በመንገዳገድ በነበርንበት መቆማችን ተጨባጭ የለዉጥ ፍሬ እንዳነወቀምስ ዳርጎናል፡፡

ሠዉነት እና ኢትዮጵያዊነት በድካም እና በተሰጠ አገልግሎት በስራ ልክ ሳይሆን ባወራ እና ባዋራ ሆኖ ለአገር እና ህዝብ የኖሩትን ፍቅር፣ክብር እና መኖር ዕዉቅና ሳንሰጥ ለይምሰል እና ለመኖር በሚል አፍቃሪ መንበር እና ወንበር የማምለክ እና የመከተል አባዜ ባለበት ዕዉነትን መፈለግ እና ዘላቂ  ብሄራዊ  ለዉጥ መጠበቅ  በጨለማ ማፍጠጥ ስለሚሆን በአገር እና በራሱ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል ምድር ላይ ያለዉን ከምግባር እና ተግባር ጋር አዋህዶ ሊመለከት ይገባል፡፡

ለእኛ ኢትዮጵያዉያን ጥላቻ እና ባዶነት ከወለዳቸዉ ድንቁርና፣ ከድህንነት  እና ሁለንተናዊ ኋላ ቀርነት ባርነት ቀንበር የሚያላቅቀን በአንድነት እና ህብረት በማዎቅ ፣በመጠበቅ ለስራ ስንቆም እና በጎ ምግባር እና ተግባር እና ባለቤቶች ክብር እና ፍቅር ስንቸር ብቻ ነዉ ፡፡

ዓምልኮታቸን መለኮታዊነት ፤ ምስክርነታችን ዕዉነትነት የተከተለ አስከሆነ ድረስ ብቻ የምንለዉን እና የምንነጋረዉን መሆን የምንችለዉ፡፡

 

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ !!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.