በአማራና አፋር ክልል ሕወሓት ሽንፈት እንደደረሰበትና ውጊያውን መቋቋም እንዳቃተው ዶ/ር ደብረጺዮን በቁጣ ተናገሩ

ዶ/ር ደብረፂዮን ከአፋር እና አማራ ውጊያ ከተሸነፉ በኋላ የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦችን ማጽዳታቸው ተሰምቷል ። ደብረፂዮን ታጣቂዎቹ እንዲያፈገፍጉ ቀደም ብሎ ቢናገርም የጦር አመራሮቹ ባለመስማታቸው በደረሰው እልቂት በደብረፂዮን እና በቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። በደብረፂዮን መግለጫ የዲያስፖራው ክንፍ ቁጣውን ገልጿል። ከሽንፈታቸው ጋር በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ሽንፈታቸውን አምነዋል። በአራት ወር ውጊያ ውስጥ፣ ደሴና ኮምቦልቻን ለመያዝ እና እስከ ሽዋ ለመድረስ በርካታ የትግራይ ወጣቶች እንደ ቅጠል መርገፋቸውን በአደባባይ ለትግራይ ህዝብ መርዶውን በመግለጫው አስታውቋል።መግለጫውን ከታች ያገኙታል።

ምንልክ ሳልሳዊ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ከዚህ ቀደም ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ትእዛዝ ሲሰጥ የቆየው  በአፋር እና በአማራ ክልል የሕወሃት ሃይሎችን ሲመሩ በነበሩ ከፍተኛ አማፂ ጄኔራሎች ላይ በቁጣ መናገሩ የተዘገበ ሲሆን  የኢትዮጵያ ፌደራል ሃይሎች እየደረሰ ያለውን ግስጋሴ ማስቆም ባለመቻሉ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ንዴታቸውን ገልጸዋል።

የፌደራል ሃይሎች በሕወሓት ወራሪዎች ላይ ያገኙትን ድሎች ተከትሎ በደብረፂዮን እና በቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች መካከል አለመግባባት መፍጠሩን የአሜሪካው የአማፂ ቡድን ከፍተኛ ተወካዮች በዙም ስብሰባቸው መናገራቸው ታውቋል። በአሜሪካ የሚገኙ አንድ የቡድኑ ከፍተኛ አመራር ደብረፂዮን በአፋር እና በአማራ ክልል የሚገኙ የአማፂያኑ አዛዦች እንዳያፈገፍጉ መመሪያ ቢሰጥም የኢትዮጵያ ፌደራል ሃይሎች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እያደረጉት ያለው ግስጋሴ ደብረፅዮን አንዳንድ አዛዦችን ለመተካት ሲሰራ የነበረውን ትርምስ ፈጥሯል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሚኒሶታ የሚገኘው ቅዱስ ዑራኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በኦሮሚያና በጎንደር ለተገደሉት ወገኖች የጸሎት እና የሻማ ማብራት ጥሪ አቀረበ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.