December 4, 2021
5 mins read

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠላት ኃይል እጁን እንዲሰጥ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች እጃቸውን እየሰጡ ነው

263128948 3083358245239967 6009070202969624093 n

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጠላት ኃይል እጁን እንዲሰጥ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች እጃቸውን እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ግንባር አምርተው የወገንን ጦር መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ግንባር ድል እየተመዘገበና የጠላት ሀይል እየተበታተነ ነው።

በዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነትየወገን ጦር ድል በድል እየደራረበ ሲገሰግስ በአንፃሩ የጠላት ኃይል በየጦር ግንባሩ ሽንፈትን እየደረሰበትና እየተደመሰሰ ይገኛል።

ለአብነትም በጋሸና፣ በሸዋ፣ በወረኢሉ፣ በጭፍራ እና በሌሎች ግንባሮች የወገን ጥምር ጦር ባደረገው ተጋድሎ በርካታ ከተሞችን ከወራሪው ኃይል ነፃ ማድረግ ችሏል፣ የወራሪው ቡድንም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት በመፈርጠጥ ላይ ይገኛል።

262694218 3083358508573274 31724477646219000 n

ከመደምሰስ የተረፈው የወራሪና ዘራፊ ቡድኑ ኃይልም እየተበታተነ ሲሆን የወገን ጦር በየግንባሩ የተበታተነውን የጠላት ኃይል የመልቀም ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ራዕይና ግቡ በማይታወቅ ጦርነት በዕውር ድንብር ጁንታው ያሰለፋቸው የትግራይ ወጣቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ መሆኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።

በዚህም ወጣቶች በማያውቁት አካባቢና ራዕይ በሌለለው ጦርነት ገብተው እንዳያልቁ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊትና ለክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የትግራይ እናቶችም ልጆቻቸው ራዕይ በሌለው ጦርነት እንዳያልቁ ልጆቻችን የት ደረሱብለው መጠየቅ እንዳለባቸው መግለፃቸው አይዘነጋም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎም በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ለውጊያ ያሰለፋቸው ታጣቂዎች እጃቸውን ለወገን ኃይል እየሰጡ ነው።

እጃቸውን የሰጡት ምርኮኞቹም ባለማወቅና በመገደድ ወደ ውጊያ መሰለፋቸውን ገልፀው፤ ቡድኑ በደረሰበት ሽንፈት እጅ ለመስጠት መገደዳቸውን ገልፀዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በቤተሰብ ልጅ አምጡ እየተባሉ በአሸባሪው ተገደው ቢሰለፉም በእስካሁኑ ድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ ጠይቀዋል።

አሸባሪው ቡድን የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን አሸባሪ ቡድኑ ተሸንፏል ብለዋል።

በርካታ ጓደኞቻቸው በከንቱ ሕይወታቸውን የሚናገሩት ምርኮኞቹ፤ እነርሱ ግን እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠታቸው እድለኞች ነን ብለዋል።

እጅ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በህብረተሰቡ ለተደረገላቸው እንክብካቤ አመስግነዋል።

263399639 3083358711906587 8458015164626355013 n

ሌሎች የትግራይ ወጣቶችም በአሸባሪው ቡድን እያሸነፍን ነው በሚል በሚዲያ በሚነዛው ሀሰተኛ መረጃ እየተደናገሩ ለውጊያ እንይሰለፉ፣ ውጊያ ላይ የተሰለፉትም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የትግራይ ወጣቶች በጁንታው ጦርነት ከመማገድ ይልቅ ለወገን ጦር እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸውን ማዳን እንዲችሉ የኃይማኖት አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።

262836880 3083358358573289 3190485293280328137 n

በየግንባሩ ተሸንፎ የተበታተነው የጠላት ኃይል የዘረፈውን ሀብት ይዞ እንዳይሸሽ ህብረተሰቡ አካባቢውን ተደራጅቶ እንዲጠብቅ፣ ብሎም የወራሪው ኃይል አባላትን እየማረከ ለመከላከያ ሰራዊት እንዲያስረክብ መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

263573436 3083358625239929 7535648849415106538 n

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

ህዳር 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop