የጦርነት ሁኔታ ዘገባ – ግርማ ካሳ

12/3/2021

ወያኔዎች በቀለኛ፣ ዘረኛ በጥላቻ የተሞሉ ናቸው፡፡ ፖለቲካቸው የትግራይን ሕዝብ በመጥቀም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ ምን እንዳደረጋቸው ባላውቅም፣ አማራ የሚሉትን ማህበረሰብ በመጥላት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ተጋሩን እንዴት እንጠቅም ሳይሆን አማራን እንዴት እንጉዳ የሚል ነው አጀንዳቸው፡፡

ለዚህ ነው፣ ጎንደር ወሎ በመሄድ፣ ለድሃው የትግራይ ነዋሪ ምንም ባይፈይድም፣ ከአማራ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን ብለው በአማራና በአፋር ክልል ወረራ የፈጸሙት፡፡

1) ወያኔዎች ጦርነት ሲጀምሩ መጀመሪያ ያሰቡት ነገር የሱዳንን ኮሪዶር መቆጣጠር ነበር፡፡ ከሃያ ጊዜ በላይ፣ ወልቃይትን ለመያዝ ብዙ ሞክረው አልተሳካላቸውም፡፡ በነኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የሚመራው የወልቃይት ህዝባዊ ሰራዊት ወልቃይትን የወያኔዎች መቀበሪያ ነው ያደረገው፡፡

2) ሲቀጥሉ አላማቸውን የአማራ ክልልን በማፍረስ ላይ አድርገው፣ በአራት መስመር በተለያዩ ጊዜያት ጎንደር ብለው ባህር ዳር ለመግባት ሞከሩ፡፡ 1ኛ በማይጠምሪ አድርገው በደባርቅ በኩል፣ 2ኛ በአምደወርቅ አድርገው በእብነት በኩል፣ 3ኛ በሰሜን ወሎ መቄት አድርገው በደብረ ታቦር በኩል፣ 4ኛ ከሱዳን ሳምሪ የሚባለውን አሸባሪ ቡድናቸውን በማሰለፍ በመተማ በኩል፡፡

በነዚህ ሁሉ ግንባሮች በጣም ከፍተኛ ሽንፈት የተከናነቡ ሲሆን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቻቸውን ገብረዋል፡፡ በጎንደር በኩል ወያኔ አሁን ያለችው፣ በጠለምትና በሰሜን ጎንደር አደርቃይ ወረዳ ላይ ብቻ ነው፡፡

3) ወያኔ ጎንደርን ትታ ኃይሏን በአንድ አቅጣጫ አድርጋ፣ ከመቶ ሺህ በላይ በከባድ መሳሪያ የታጠቀ ሰራዊት አሰልፉ፣ በደሴ መስመር፣ መስከረም 27 ቀን አዲስ ዉጊያ ከፈተች፡፡ ሁለት ዋና ዋና ግቦችን ሰንቃ፡፡ 1ኛ የጅቡቲ አዲስ አበባን መስመር በመዝጋት አዲስ አበባን ማነቅ ነበር፡፡ 2ኛው ደግሞ በሸዋ አልፎ አዲስ አበባ መግባት ነበር፡፡ እነዚህን ሁለት አላማዎች ለማሳካት ኦነግ ተባባሪ ሆኖ ከጎናቸው በይፋ ተሰለፈ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 77

ወያኔ ደሴንና ኮምቦልቻን ከብዙ ዉጊያ በኋላ ተቆጣጠረች፡፡ የፌዴራል መንግስቱ የወያኔና ኦነግ ጥቃት በመደበኛ ወታደር የሚቀለበስ አይደለም በሚል ህዝብ ባለበት እንዲንቀሳቀስ አዋጅ አወጣ፡፡ ለሕዝባዊ ሰራዊት አባላት ፋኖዎች፣ ሚሊሺያዎች ድጋፍ መስጠት ብቻ ሳይሆን ከመከላከያ ጋር በቅንጅት የሚሰራበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያስችሉ ስራዎች ተጀመሩ፡፡

ወያኔዎችና ኦነጎች በጭፍራ በኩል፣ በካሳጊታ በኩል፣ በቡርቃ በኩል ሚሌን ለመያዝ ከሃያ ጊዜ በላይ ሙከራ አደረጉ፡፡ በአፋር አርበቶ አደር ሚሊሺያዎች፣ በአፋር ልዩ ሃይል አባላትና በመከላከያ ስራዊት ጥምር ጦር ከፍተኛ ጉዳይ ስለደረሰባቸው ሳይሳካላቸው ቀረ፡፡

በአፋር ግንባር ሲሸነፉ ወደ ኬሚሴ በመሄድ፣ በዚያ በመሰባሰብ በሁለት መስመር አዲስ አበባ ለመግባት እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ በአጣዬ፣ ሰንበቴ ሸዋሮቢት ብለው ደብረ ሲና ደረሱ፡፡ ሆኖም የጣርማበር ዋሻን ማለፍ አልቻሉም፡፡ ከማጀቴ ወደ መሃል ሜዳ በማለፍ፣ በሞላሌ አድርገው በሰላ ድንጋይ በኩል ፣ በጣርማ በር ሳያልፉ፣ የደብረ ብርሃኑን መንገድ ለመያዝ ተንቀሳቀሱ፡፡ በርሱም በኩል ሳይሳካላቸው ቀረ፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ስህተቶች ተሰርተው የነበረ ቢሆንም፣ የራሳ ገበሬዎች፣ ፋኖዎች፣ የአማራ ሚሊሺያዎች፣ የመንዝ ተዋጊዎች የመከላከያና የአማራ ልዩ ኃይል ጥምር ጦር ወያኔንና ኦነግን ሙሉ ለሙሉ ከስሜን ሸዋ አጸዳ፡፡ እጅግ በጣም በርካታ የኦነግና የወያኔ ታጣቂዎች ተገድሉ።፣ ተማረኩ፡፡ መሸሽ የቻሉትን ልብሳቸውን ቀይረው የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ወደ ሚባለው ሸሹ፡፡

4) ወያኔዎች በምእራብ ወሎ እስከ መካነ ሰላም ደጃፍ ደርሰው ነበር፡፡ ሆኖ አሁን ከዚያ ተገፍተው፣ ወረኢሉ፣ አቃስታ፣ ገነቴ የመሳሰሉት ሳይቀሩ በወገን ስር ወድቀዋል፡፡

5) በደቡብ ወሎ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ፋኖዎች የገቡ ሲሆን፣ በቀናት ውስጥ የመከላከያ ሃይል ገብቶ መልሶ አስተዳደሮችን ይዘረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡ ሃይቅ፣ ቢስቲማ፣ ኩታበር ፣ ተንታ ….ያሉት ወያኔዎች አቅጣጫቸውን ወደ ስሜን አድርገው እየሸሹ ነው፡፡ በሰዓታት ውስጥ ደቡብ ወሎ ሙሉ ለሙሉ ከወያኔ ነጻ ትወጣለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው ተባለ • ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው

6) ጋሸናን ተከትሎ የወገን ጦር ወደ ወልዲያ መስመር እየገስገሰ ነው፡፡ እስታሽን በወገን ስር ስትሆን በምእራብ አቅጣጫም እንዲሁም ከጭፍራ አቅጣጫም ወደ ወልዲያ የወገን ጦር እየቀረበ ነው፡፡

7) ወያኔዎች ወደ ራያ ለመሸሽ፣ ከላሊበላ ወደ ኮረም ፣ ከቆቦ ወደ አላማጣ የሚወስዱትን መንገዶች ለማስከፈት፣ በቆቦ ዉጊያዎች ከፍተዋል፡፡ ሆኖም የቆቦ ዞብል ሚሊሺያዎችን መቋቋም የቻሉ አይመስልም፡፡ መንግስት በአፋር በኩል የዞብል ሚሊሺያዎችን የበለጠ በስንቅና ትጥቅ ማገዝ ከቻለ ፣ በቆቦ በኩል በአስተማማኝ ሁኔታ ዋናውን መንገድ፣ ወያኔዎች የማስከፈት እድል እንዳይኖራቸው ያደርጋል ተብሎ ነው የሚገመተው።

ሰቆጣ ከሁለት ሳምንት በፊት በወገን ጦር ስር ወድቃ ነበር፡፡ ሆኖም የላሊበላን መያዝ ተከትሎ ከትግራይ ከ25 ሺህ በላይ ታጣቂዎች በማሰማራት፣ ወያኔ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ሰቆጣ እንዲሁም ላሊበላን በመያዝ፣ በጋሸና የነበራቸው ጦር ለማጠናከር ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ውስጥ። ሆኖም ላሊበላ ከተማ ላይ ውጊያ በማድረግ የአገር ቅርስን ላለመጉዳት፣ ከተማዋን ለቆ የወጣው የወገን ጦር ፣ ላሊበላ ዙሪያ ባደረጋቸው የማጥቃት ዘመቻዎች በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መልሶ ላሊበላን ተቆጣጥሯል፡፡ ከላሊበላ እንዲሁም ከአምደወር የተጠናከረ የወገን ጦር መልሶ ሰቆጣን ለመያዝም እንቅስቃሴዎች እያደረገ ነው፡፡

9) በስሜን ጎንደ በኩል አደርቃይን ብሎ ማይጠምሪን ለመቆጣጠር የሚታዩ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች እስከአሁን አልተጀመሩም።

መንግስት ድክመቱን አምኖ፣ በመደበኛ ወታደር ብቻ፣ የተቃጣዉን አገርን የማፍረስ ጥቃት መመከት አይቻልም በሚል፣ በህዝብ ተማምኖ፣ እንደ ፋኖ ላሉ አደረጃጀቶችን እውቅና ሰጥቶ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ድጋፍ ለማድረግ መሞከሩ ፣ ትኩረቱንም ጦርነቱ ላይ በማድረግ የማጥቃት ዘመቻ እንዲጀመር ውሳኔ ማሳለፉ፣ ይኸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጦች እንዲመጣ አድርጓል፡፡ ዶር አብይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር መሄዱ ቀላል የማይባል መነቃቃትን በወገን ጦር ዘንድ ሊፈጥር ችሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሐረር ከተማ ባሉ ነጋዴዎች ላይ እየተደረገ ያለው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል

ሆኖም በነዚህ ተገኙ በተባሉ ውጤቶች መዘናጋት አያስፈለግም፡

1ኛ ወያኔ ሙሉ ለሙሉ ከሰሜን ወሎ፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከራያና ከጠለምት አልወጣችም

2ኛ በተለይም በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ውስጥ አሸባሪ ኦነጎች፣ አሁን ሰላማዊ መስለው ህዝቡ ተቀላቀሉ እንጂ ብዙም እርምጃ አልተወሰደባቸውም፡፡ ነገሮች ሲረሳሱ መልሰው ጥቃት መፈጸማቸው አይቀርም፡፡

3ኛ ሕወሃቶች እስካሉ ድረስ፣ ወደ ትግራይ ቢገፉም፣ እንደና ጦርነት ሊከፍቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በትግራይ ሕዝቡ ራሱን ይዞ ለፍርድ እንዲያቀርባችው የመገፋፋት ስራዎች መሰራት አለባችው፡፡ ካልሆነም ወደ ትግራይ በመዝለቅ ህወሃትን ያለችበት ቦታ ሄዶ የማስወገድ ስራ ይጠብቀናል፡፡

4ኛ በጉጂ፣ በወለጋ አሁን ያለ ምንም ችግር ኦነግ ህዝብን እያሸበረ ነው፡፡

5ኛ ከአማራ ጋር ሂሳን እናወራርዳለን እንዳሉት፣ ወያኔዎችና ኦነጎች የአማራ ክልልን በተለይ፣ 30 አመት ነው ወደ ኋላ ያደረጉት፡፡ ብዙ የአማራ ክልል ከተሞች ሸዋ ሮቢት፣ ወረኢሉ፣ ደብረ ሲና ፣ ንፋስ መውጫ፣ የመሳሰሉት ወድመዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆተሩ ተፈናቅለዋል፡፡ ተፈናቃዮችን የመመለስ፣ የወደሙትን የመገንባት ትልቅ ስራ ከፊታችን አለ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share