ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ተናገረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ የጠቅላይ ሚኒስትሩን በታህሳስ አጋማሽ በጥር መጀመሪያ አዲስ አበባ እንገናኝ የሚለውን ጥሪ በተመለከተ ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅናሽ ያለበት መስተንግዶ እንደሚሰጥ ተናገረ፡፡

አየር መንገዱ ከአውሮፓ ፣ ከሰሜን አሜሪካ እና ኬሎችም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በእኔ በኩል ከሚመለከታቸው ጋር የሚፈለገውን ሁሉ እያደረኩ ነው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትኬት ቅናሽና ተጨማሪ የሻንጣ የኪሎ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል፡፡
አየር መንገዱ የማይበርበትም ሥፍራ ቢኖር፣ ገበያውን ለማምጣት እንደሚሰራ ከአየር መንገዱ ምንጫችን ሰምተናል።
ዝርዝሩንም በተመለከተ ምንጫችን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ነግሮናል፡፡
1 ሚሊዮን ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የአየር ትራንስፖርት፣ የአስጎብኚ ድርጅቶች፣ የጉዞ ወኪሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የሆቴል ባለቤቶች በትብብር እንዲሰሩ በዘርፉ የቀረቡ ባለሙያዎች ለሸገር ነግረዋል፡፡
የኢሚግሬሽን እና የከተማው የቱሪዝም ቢሮዎች ኤምባሲዎች የቆንስላ ፅ/ቤቶች የቪዛና የሰነድ አገልግሎት እያቀለጣጠፉ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲመጡ የሚያበረታታውን ማዕበል እንዲቀላቀሉ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ ፅፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚ ቀደምም ሆነ ወደፊትም ለልዩ ልዩ በዓልና ተመሳሳይ ወቅቶች የተለየ ቅናሽ እንዲሁም አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል
ተህቦ ንጉሴ
ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ተነሳ - ሰውይው መውረድ አለበት (የራያእና ቆቦ ሰላማዊ ሰልፍ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share