ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ዛሬና ነገ ነፃ ይወጣሉ

262348226 4902796979801044 712380264333129490 nዛሬና ነገ በሚከወኑ ኦፕሬሽኖች ኬሚሴ፣ ባቲና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ ከተሞች በወገን ጦር እንደሚያዙ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጃማ ደጎሎ ግንባር ባደረጉት ገለፃ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ወደ ደሴ የሚቃረብበትን መንገድም ይይዛል ብለዋል፡፡
በደጎሎ ግንባር ስልታዊ ኦፕሬሽኖች እየተደረጉ ሲሆን በዚህም ሰሜን ሸዋ የገባው የጠላት ኃይል እንዳይወጣ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
እንደ ጋሸና ባሉ ድል በተገኘባቸው አካባቢዎች ይዞታን የበለጠ የማስፋት ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
‹‹አሁን ላይ ጠላት ፈርሷል፤ ተሸንፏል›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ጠላትን የመልቀም፣ የዘረፈውን ንብረትና ትጥቅ የማስቀረትና ጠላት በቡድን ሆኖ የማይወጣበትን አግባብ የመፍጠር ሥራ ነው እየተሰራ ያለው ብለዋል፡፡
ኅዳር 23/2014 (ዋልታ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.