ጠ/ሚ አብይም ፤ ታጋይ ዘመነ ካሴም ወደ ጦር ሜዳ የወረዱት ሃገር ለማዳን ነው ! – መስከረም አበራ

abiy and zemene“አሁን ዋና ትኩረታችን መሆን ያለበት ሃገራችን ከውስጥም ከውጭም የተቃጣባትን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ መቀልበሱ ላይ ነው፤ ሌላው ሃገራችን መትረፏን ካረጋገጥን በኋላ ይደርሳል” የሚለው ተገቢ አቅጣጫ የእኔ ቢጤውን ተራ ሰውም ጉልበታሙን መንግስትም እኩል ሊገዛ ይገባዋል።
ስለዚህ ባለ ብዙ ጠበቃው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‘ሃገር ለማዳን የጦር ሜዳ ስለወረዱ በጥያቄ ብዛት አታድክሟቸው’ የሚለው ጥብቅና ሃገር ለማዳን ጦር ሜዳ ለወረዱት እነ ዘመነ ካሴም ሊሰራ ይገባል።
ጅንስ እና ሱፉን አውልቆ መለዮ ለብሶ የሚንጎራደደው ዲያስፖራም ሆነ ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛም ሆነ ካድሬ ይህን ሊናገር ይገባል! ካልሆነ መለዮ ያስለበሳቸው የመንግስት አዝማሪነት እንጅ ሌላ እንዳልሆነ ገሃድ ይወጣል።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሀይማኖት አባቶች ሕዝብ ሲበደል ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ዝምታ ማንን ለመጥቀም ? ሀይማኖቱ በደል ይደግፋል? ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ ያብራሩታል

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.