የኢትዮጵያ ጦር ላሊበላን መልሶ ተቆጣጠረ

58775245 303

የኢትዮጵያ ጦር ላሊበላን መልሶ ተቆጣጠረ

ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ እና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዋም በዛሬው ዕለት ማምሻውን በተባበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያ እና ፋኖ ቁጥጥር ስር መግባታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ እና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዋም ዛሬ ማምሻውን በተባበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያ እና ፋኖ ቁጥጥር ስር መግባታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። መስሪያ ቤቱ ዛሬ ማምሻውን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላሊበላ ከተማና የአውሮፕላን ማረፊያዋን መልሶ የተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ጦር ፣ የላሊበላ አካባቢን በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደዚያው ማምራቱን አስታውቋል። ሮይተርስ የጠቀሳቸው በአንድ የላሊበላ መንደር የሚገኙ ነዋሪ የህወሓት ሀይሎች መንደራቸውን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል። ከላሊበላ በስተደቡብ ምዕራብ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለችው «ግራኝ አምባ» የሚገኙት እኚሁ ነዋሪ እንዳሉት የትግራይ ተዋጊዎች መንደራቸውን ጥለው የወጡት ትናንት ነው። ሲወጡም «የዐቢይ ወታደሮች እየመጡ ነው።» ብለው ነግረዋቸዋል። ነዋሪዋ እንደተናገሩት የህወሓት ኃይሎች ዛሬ ጠዋት ወደ ላሊበላ አቅጣጫ ሲሸሹ አይተዋል። ከላሊበላ የሚመጡ ነዋሪዎችም ተዋጊዎቹ ላሊበላን ጥለው መሄዳቸውን ነግረዋቸዋል። ዛሬ ጠዋት የአማራ ልዩ ኃይሎች መንደራቸው ገብተው እናንተን ለመጠበቅ ነው የመጣነው ሲሉ  አጽናንተውናልም ብለዋል ነዋሪዋ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

——————————-

 

የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያ እና ፋኖ የላሊበላ ከተማን እና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸውን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። ጥምር ኃይሎቹ የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር በግስጋሴ ላይ መሆናቸውን የኮሚዩኒኬሽን መስሪያ ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአሸባሪው ሕወሃት ጎን 'ተሰልፈን አገራችንን በመውጋታችን ተጸጽተናል' ሲሉ የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች የነበሩ ምርኮኞች ገለጹ

 

Lalibela Airport 1 768x518 1

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጠዋት በሰጠው መግለጫ፤ የመከላከያ ሰራዊት በጋሸና ግንባር በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን ገልጾ ነበር። የኢትዮጵያ ሰራዊት ጋሸናን መቆጣጠሩ፤ በላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ወልዲያ እና ደሴ በአማጽያን ቁጥጥር ስር ያሉ አካባቢዎችን “በአጭር ጊዜ ለማጽዳት መንገዱን የተመቻቸ ያደርገዋል” ሲል የቦታውን ስትራቴጂካዊነት አመላክቷል።

የህወሓት ኃይሎች ታሪካዊቷን የላሊበላ ከተማ መቆጣጠራቸው የተነገረው በሐምሌ ወር መጨረሻ ነበር። አማጽያኑ “ስትራቴጂካዊ” እንደሆነች የሚነገርላትን ደሴን የተቆጣጠሩት ደግሞ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ነው።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.