ኢትዮጵያ ለባንዳ እና ሞቶ ከዳ ከዚህ በኋላ ልትሆን አይገባም !!! – ማላጂ

ኢትዮጵያ ለዘመናት በአርቆ አሳቢ እና ሁሉን አቃፊ በሆኑ ህዝቧ የዕምነት እና የባህል እርሾ ከጥንት አስከ ጥዋት በይቅር ባይነት የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶቿን አቅፋ እና ደግፋ ኖራለች፡፡

ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ የሚገኙ የጠላት ጉዳይ አስፈፃሚዎች ለዘመናት በለመዱት አካሄድ በጥላቻ እና በሴራ አገርን የማፍረስ እና የህዝብን ህልዉና የመግሰስ የክፉ መንፍስ አባዜ ዛሬም እንደተጫናቸዉ ቢገኙም ዛሬ ትናንት አለመሆኑን መረዳት እና ዘመኑን መዋጀት አለመቻላቸዉ ዛሬም በዕብሪት እና ጉልበት አገርን የከዳ የባንዳ ምድር ለማድረግ የሞት ሽረት ትንቅንቅ ላይ ይገኛሉ ፡፡

በዕብሪት እና በክፋት ኢትዮጵያን ህዝብ አባር እና ገባር የማድረግ ፤የመለያየት እንዲሁም ከ1950ዎቹ ጀምሮ በተደራጀ እና ሁሉን አቀፍ በሆነ ዓለም አቀፍ ይዘቱን የጠበቀ ፤በብቃት እና በዕዉቀት የኢትዮጵያ እና ህዝቧ ብሄራዊ ህዝባዊ ሠራዊት መበተን የህልዉና እና ነፃነት ጉዳይ በግለሰብ እና በቡድን እጅ መዳፍ ስር እንዲወድቅ ሆኗል ፡፡

ይህ የዘመናት ኢትዮጵያን የማራቆት ሴራ የኢትዮጵያን ብሄራዊ እና ታሪካዊ ዕዉነት ወደ መንደር እና ጎጥ የማዉረድ ደባ የፖለቲካ ስልጣን እና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከህዝብ እና አገር ጥቅም በላይ የግለሰብ እና ቡድን አምልዕኮት ማዉረድ እና ለዚህ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለሚገኙበት ብሄራዊ ቀዉስ መንስኤ እና ዉጤት ነዉ ፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያም ሆኑ ህዝቧ በየዋህነት እና በይቅር ባይነት እንዲሁም በአድር ባይ የዉስጥ እና ዉጭ መኃል ሰፋሪዎች ድብቅ ዓላማ ለአገር እና ህዝብ ባለዉለታ የሆኑትን በመግፋት እና በማጥላላት ከዚህ በተቃራኒ ለአገር ደህንነት እና ብሄራዊ አንድነት ስጋት የሆኑትን የመሾም እና የመሸለም ልማድ አሁን ላይ ተቀባይነት የማያገኝበት የትዉልድ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡፡

ማንም ምንም ይበል ምን“ ኢትዮጵያዉያን ቁጭ ብሎ የሚያከብራቸዉን እና ቆሞ የሚንቃቸዉን ”አሳምረዉ የሚያዉቁ እንደመሆናቸዉ የቁርጥ ቀን ልጆች ላለፉት የሞት እና ጥልመት ድቅቀድቅ የጭለማ ዘመናት እምቢ ለነፃነቴ ፤ለአገሬ እና ክብሬ ያሉትን ባንዳ እና የከዳ አድር ባይ ጠላት ቢያሳድዳቸዉም ሞትም ሆነ ስደት ከዓላማቸዉ ሊያስተጓጉል ቀርቶ ይባስ እንደ ብረት እንዲጠነክሩ ፤እንደ ባህር አሸዋ እንዲበዙ በማድረግ ተጋድሏቸዉ እንደ ንጋት ክዋክብት ለትዉልድ የነፃነት እና የህልዉና ፋና ወጊ በመሆን የሚኖሩ እና የሚዘከሩ ይሆናል፡፡

አሁን እና ወደ ፊት እንደ ቀደሙት ዘመናት በአጉል አድር ባይነት እና ስመ ሆደ ሰፊነት ኢትዮጵያችን ሆነ ህዝቧ ለባንዳ እና ለከዳ የምትሆን ፤ለሞቱላት የማትሆንበት ጊዜ እና ትዉልድ ላይ አለመሆናችንን ልንገነዘብ እንዲሁም አጋም እና ቁልቋል ሆኖ መኖር በቃ ሊባል ይገባል፡፡

ለዘላለም በጭለማ ከመኖር ቁራጭ ሻማ ማብራት እንዲሉ ቁልቋል እና አጋም ከመሆን ባንዳ እና የከዳ ኢትዮጵያ አትሆናቸዉም ልንል ይገባል፡፡

አበዉ አገር የጋራ ፤ ኃይማኖት የግል እንዲሉ …..ከእንግዲህ ኢትዮጵያ እና ግዛቷ ለኢትዮጵያዉያን የጋራ ጎጆ እንጂ ለግዞት እና ለጥፋት ለሚመኛት ለገዳይ እና አግላይ እንዳትሆን ሆኖ ለዓመታት የተደረገዉ የኢትዮጵያዉያን የነፃነት እና ህልዉና ተጋድሎ በአንፀባራቂ እና አመርቂ ድል እና ገድል ሊቋጭ ይገባል፡፡

ማላጂ

አንድነት ኃይል ነዉ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.