ሀገሬን ከስራ ስመለስ አጣኋት ” ከሚል መራር ወግ ይሰውረን

እስክንድር ከበደ
261033515 4692718477434640 6441303254606313666 n ሀገሬን ከስራ ስመለስ አጣኋት ” ከሚል መራር ወግ ይሰውረን
አትሌት ሀይሌ ገብረሰላሴ በዓለም አቀፍ የሩጫ መድረክ ደጋግሞ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ያዘፍናል፡፡ አንድ ቀን የኬኒያው አትሌት ፖል ቴርጋት አንደኛ ወጣ፡፡ ፖል ቴርጋት የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር ይዘምር ጀመር፡፡ ( ይህ የተጋነነ ቀልድ ሊሆን ይችላል) አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ የማሸነፍ ምልክት ነው፡፡ አንድ ሀገር ሄዳችሁ ከየት እንደመጣችሁ ቢጠይቋችሁ፤ ከኃይሌ ገብረስላሴ ሀገር እንደመጣችሁ ከተናገራችሁ ወዲያው የሚረዷችሁ ብዙ ናቸው፡፡ ኃይሌ ገብረስላሴ በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ወክሎ ብዙ ሜዳሊያዎች ወስዷል፡፡ የወርቅ ሜዳሊያዎቹ ተራ አሸብራቂ ጌጦች አይደሉም ፡፡ ስለኢትዮጵያ ያገኛቸው ውድ ክብሮች ናቸው፡፡ ከፊት ቆሞ የበርካታ ሀገራት አትሌቶች ከኋላው አስከትሎ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙርና ባንዲራን አስጠንቷል።

https://fb.watch/9zpG6AREPP/

በተስፋዬ ገብረአብ አንድ ድርሰት ውስጥ ስለአንድ የሶቭየት ህብረት ዜጋ ወግ ጽፎ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ስደተኞች ተራ በተራ እየተመዘገቡ መዝጋቢዋ የሞስኮቡን ሰው የየት ሀገር ዜጋ እንደሆነ ትጠይቀዋለች፡፡
261278822 4692761934096961 4281796897804311344 n ሀገሬን ከስራ ስመለስ አጣኋት ” ከሚል መራር ወግ ይሰውረን
”ሀገሬን ከስራ ስመለስ አጣኋት ” ይላል ስደተኛው
” ሀገርህ የት ነው ?” አለችው መዝጋቢዋ በመገረም ፡፡
” የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ናት፡፡ ከስራ ስመለስ ፈራርሳ ጠበቀችኝ ”
” ስራህ ምን ነበር ?” አለች ስደተኛውን በመገረም እያየችው፡፡
”ጠፈርተኛ ” አላት ያ ስደተኛ ፡፡ ወደ ህዋ ከሄደ በኋላ ሶቭየት ህብረት 15 ትናንሽ ሀገራት ሆና ጠበቀችው፡፡ ይህ ጠፈርተኛ የሶቭየት ህብረት ዜጋ ሆኖ ወደ ህዋ ሄዶ መሬት ሲወርድ አጣት ፡፡ በዚህ ሰው የሚፈጠረውን የሀዘን፣የመከፋትና የመሰበር እንዲሁም ብዙ ውል አልባ ጉድለቶች የትኛውም ነገር አይሞላውም፡፡ የአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴም ሆነ የአዛውንት ጀኔራሎች የግንባር ዘመቻ የላቀ ግብ ያጠለቁት ኒሻኖች ምትሀትና ህያውነት ሀገራቸው ናት፡፡
262163711 5041610105870825 7104490287734847178 n ሀገሬን ከስራ ስመለስ አጣኋት ” ከሚል መራር ወግ ይሰውረን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.