የህወሓት የስልጣን ዘዋሪዎች መጨረሻ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ዓላማ ማስፈጸም ነው ሲል ጄፍ ፒርስ የእነ ኤፍሬም ይስሀቅን ድብቅ ሴራና ሴረኞቹን የተነተነበትን ጽሁፍ ለዓለም አጋርቷል

tplf 89988በዓለም አቀፉ የሰላምና ልማት ማእከል አማካይነት የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደሮች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የአሸባሪው ህውሓት ቡድን አባላት የተሳተፉበት ስብሰባ ባሳለፍነው ሳምንት በድብቅ ተካሂዶ ነበር። የዚህን ስብሰባ ምንነትና የተሳታፊዎችን  ማንነት ጄፍ ፒርስ ዘርዘር ባለ ጽሁፉ አስነብቧል። ከመጋረጃ በስተጀርባ ያለውን ሴራ ገላልጧል።

ውይይቱ የተመራው በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ ሲሆን፤ ይህ ውይይት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምሎ የተነሳው አሸባሪው ሕወሓት ከመሰሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር የዶለቱበት እንደነበረም አደባባይ ወጥቷል።

በዚህ ስብሰባ ላይ በሀገሪቱ የተቀናጀ ከፍተኛ ብጥብጥ እና ሴራ በመሸረብ የማፍረስ የመርዝ ተንኮል በሰፊው የተሰበከበት ነበር፤ ለዚህ እውነታ ደግሞ የአሸባሪው ሕወሓት 0 3wzEv mVIyTBCeq6የውጭ ክንፍ ዋና ዘዋሪ የሆነው አሸባሪው ብርሀነክርስቶስ ሐሳብን መጥቀስ በቂ ነው ይላል ጄፍ ፒርስ፡፡

አሸባሪው የህውሓት ቡድን በግልፅ እንደሚናገረውና እያደረገም እንዳለው ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በሚሉ የውጭ ባንዳዎች ተጋላቢ ከመሆን አልፎ ከውልደቱ ጀምሮ አሁን እስከሚገኝበት የጣረሞት አፋፍ ድረስ የሚመራውና የሚሽከረከረው ከነጩ ቤተመንግስት ሰዎች በሚውረውሩለት የዳቦ ፍርፋሪ እና የነተበ የቅኝ ግዛት እሳቤ እንደሆነ በውይይቱና ከዚያም ቀደም ብሎ ገሃድ ወጥቷል።

በመሆኑም ለአሸባሪው ሕወሓት እኩይ ተግባር እና አላማ ማስፈጸሚያ እንዲሆን ታስቦ በጋላቢዎቹ የተዘጋጀ መድረክ በመሆኑ የሴራውን መርዝ ለመርጨት ሊጠቀምበት ሞክሯል። በውይይቱም ላይ የሰላምና ልማት ማእከሉ መስራች የሆነችውና የባህር ማዶ የግል ኢንቨስትመንት ኮፖሬሽን ስራ አስፋፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚሚ አለማየሁን ጨምሮ አንዳንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል፡፡

photo 2021 11 27 17 02 07 3

ሚሚ አለማየው በ2013 ከ20 ተፅዕኖ ፈጣሪ እንስት ባለሀብቶች በሚል ፎርብስ መፅሄት ባወጣው ዝርዝር ውስጥ የተካተተች ሲሆን በጆባይደን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይም የተሳተፈች ናት። በተጨማሪም በትዩተር የማህበራዊ ሚዲያ ላይ “ገለልተኛ” በሚል የቦርዱ ዳይሬክተር በመሆን ተሰይማ ታገለግላለች። ይህች ሴት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ባለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት በትዩተር ገፅ ላይ አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለማወገዝ ኢትዮጵያዊያን የሚለጥፏቸውን ጽሁፎች እግር በእግር እየተከታተለች ታስጠፋ ነበር፤ አካንታቸውንም ስታሳግድ ቆይታለች። አገራቸውንና የኢትዮጵያ መንግስት የሚደግፉ ሰዎችን “የቲዊተርን ህጎችን ጥሰዋል” በማለት ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው በርካታ ስራዎችን ስትሰራ ነበር፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የአሸባሪው ህውሓት ደጋፊዎች ሽብር እንዲነዙ ፣ሕጻናትንና ሴቶችን ለእኩይ አላማና ተግባር ሲጠቀሙባቸው ስታበረታታም እንደነበር ጄፍ ፒርስ በዚህ ጽሁፉ ላይ አብራርቷል።

ሌላው በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሲሳተፍ የነበረው ዳንኤል ዮሃንስ ሲሆን የቀድሞ የአሜሪካ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ተቋም ሀላፊ ነበር ፡፡ ይህ ሰው ከአሜሪካው መንግስት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ሲሆን ያለውን ቅርበት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ሐሰተኛ መረጃዎችን በመንግስት ላይ በመሸረብ መረጃዎችን ለባዕዳን ያቀብል እንደነበር ነበር ተደርሶበታል፡፡

የዓለም አቀፉ የሰላምና ልማት ማዕከል አባላት በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፊልትማንን ጨምሮ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደሮች የጥቅም አጋራቸውን አሸባሪ ቡድን ነፍስ ለማዳን ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። እነዚህ አካላት በሀገሪቱ በሕወሓት እብሪት ስለተከሰተው ግጭት፣ በአሸባሪው ቡድን በዜጎች ላይ ስለሚፈጸሙት ግፎች ትንፍሽ አይሉም፧ ይልቁንም በአገሪቱ ዜጎች የተመረጠውን መንግስት በሐሰት ጥላሸት በመቀባት ለመወያየትና ለማደራደር በሚል ከአዲስ አበባ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ከሚመላለሱ መካከልም ናቸው፡፡

ስፑቲ ኢንተር ናሽናል የተሰኘው ሚዲያ እንዳስቀመጠው የሰላም ማዕከሉ ከአጋሮቹ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት (USAID)፣ ናሽናል ኢንዶሜንት ፎር ዶሞክራሲ (NED) ከተሰኙ ድርጅቶች ጋር በእርዳታ ስም ይንቀሳቀሱ እንጂ በጥምረት ታዋቂና እራሱን የቻለ የስለላ ተቋም እንዳላቸው ገልጿል።

photo 2021 11 27 17 02 07 2

ሌላኛዋ የስብሰባው ተሳታፊ ሰናይት ፍሰሃ ፣ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው እንዲሾሙ በዋና አማካሪነት ስታገለግል የነበረች ሲሆን፤ ከዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጥምረት ፈጥረው የአሽባሪውን ቡድን ሀሳብ ከማቀንቀን እና ከማራመድ ባለፈ ለአሸባሪው ቡድን ጥብቅና ቆመው አገራቸውን የረሱ ባንዳ ናቸው፡፡

ካሳዬ ከበደ፣ በዋሽንግተን የሐሳብ አፍላቂና አራማጆች (ቲንክ ታንክ) ማዕከል ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ኢትዮጵያን እንዲት ማፍረስ እንችላለን? የሚልና ቀጣዩ የኢትዮጵያ ዕጣ ፍንታ ምን ይሆናል ?በሚሉ የተለያዩ ከፋፍይ የሟርት ጽሁፎች በማሳተም የአሻባሪውን ቡድን አጀንዳ ሲያራምድ ነበር፡፡ የዓለም አቀፉ የሰላምና ልማት ማዕከል አባላት ከቀድሞ አምባሳደሮችና ከህውሓት ሰዎች ጋር በ “ዙም” ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት ሌላው የተነሳው ጉዳይ የስብሰባቸው ዋና አላማ የአሸባሪው ህውሓት ቡድን ሴራንና ወንጀልን ለመሸፋፈን የታሰበ ነበር፡፡

በስብሰባቸውም እንደ ቲም ክለርክ ያሉ ተሳታፊዎች የአሸባሪው ቡድን አባል የሆነውን የብርሃነ ክርስቶስን ሀሳብ ከማወደስም ባላፈ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስኬት እንደሚያስመዘግቡም ጭምር ሲተነብዩ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዙሪያ ያሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን በማሳመን የጦርነት ማቆም ሀሳብን እንዲቀበሉ ለማድረግ ይጥራሉ። ይሄን ጉዳይ እንዲያስፈጽሙም በሶማሊያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር እና የቀጠናው መልዕክተኛ ዶናልድ ያማሞቶ እና ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆን ምርጫቸው በማድረግ የጁንታውን ነፍስ ለማዳን ተስፋን ሰንቀው ሲጥሩ ነበር፡፡

ኢሌኒ ገ/መድህን በስብሰባው ከተሳትፉት የአሸባሪውን ቡድን ምስለኔዎች መካከል አንዷ ነበረች። የአሸባሪው ቡድን ሽንፈት እየተከናነበ መምጣቱን ተከትሎም በነፍሱ መድረስና መታደግ እንዲቻል ሀሳቧን በጥያቄ አስደግፋ ገልፃለች፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ ያጋጠማትን ከፍተኛ ውግዘት ተከትሎ ጬኸቴን ቀሙኝ አይነት “በስብሰባው ላይ ያቀረብኩት ሀሳብ በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሞብኛል”” በሚል ቅሬታዋን ገልፃለች። ይሁንና ሀገር ወዳድ ኢትዮጰያውያን ስራዋን እንድትለቅ ጭምር የማህበራዊ ሚዲያ የውግዘት ዘመቻውን አጠናክረው ቀጥለውበታል።

photo 2021 11 27 17 02 07

የሰላም ማዕከል የተሰኘው የአገር እናፍርስ ውይይት አዘጋጅ ድርጅትም በሚመለከተው አካል የጀመረውን የሴራ ጥንስስ ሳይቋጭ ሕዳር 17 እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡

በሙሐመድ ሁሴን

https://amharic.zehabesha.com/the-tplfs-circle-of-powerful-movers-and-shakers-leads-right-into-joe-bidens-back-yard/

2 Comments

  1. ውድ ዘሃበሻ አዘጋጆች፣
    “ይህች ሴት [ሚሚ አለማየሁ] ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ባለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት በትዩተር ገፅ ላይ አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ለማወገዝ ኢትዮጵያዊያን የሚለጥፏቸውን ጽሁፎች እግር በእግር እየተከታተለች ታስጠፋ ነበር፤ አካንታቸውንም ስታሳግድ ቆይታለች። አገራቸውንና የኢትዮጵያ መንግስት የሚደግፉ ሰዎችን “የቲዊተርን ህጎችን ጥሰዋል” በማለት ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው በርካታ ስራዎችን ስትሰራ ነበር” ላላችሁት፣
    1/ በትዊተር ቦርድ አባልነት ተመረጠች ማለት የፈቀደችውን በትእዛዝ ማሳገድ ትችላለች ማለት አይደለም! እናንተ እንደምትሉት፣ ትህነግን የተቃወሙ ታግደው የትህነግ ደጋፊዎች አልተነኩ ከሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል
    2/ ስጋቴ በደም ፍላት ስንወነጅል ወዳጅ ሊሆኑን የሚችሉትን ማግለል እንዳይሆብን

  2. ሰው ፊት የማያቀርብ መድኃኒት የማይገኝለት ክፉ እከክ ይልቀቅባችሁ ምን ይባላል። እየሰረቅሁ የሰው ገንዘብ እየዘረፍኩ እየገደልኩ እድሜ ልኬን ልኑር እንዴት ይባላል? ቢፈልግ ቁልቋል እየበላ አገሩ ይኑር ኢትዮጵያ ላይ ምን ጉዳይ አለው ትግሬ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.