ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራ ከነጩ ቤተ መንግስት – ካናዳዊው ፀሐፊ ጄፍ ፒርስ

260504911 429182175403947 3650410493678633356 nየአሜሪካው የስለላ ማዕከል (ሲ አይ ኤ) CIA ሌሎች ሀገራትን ያፈረሰበትን መንገድ በኢትዮጵያ ሊተገብር ተንቀሳቅሷል” #ካናዳዊው_ፀሐፊ_ጄፍ_ፒርስ

ኢትዮጵያ በየዘመኑ በወለደቻቸው ልጆቿ ክህደት ሲደርስባት ተስተውሏል፡፡ በየዘመኑ ከተነሱ መኳንንቶቿ፤ ምሁራን ነን እስከሚሉት ቀለም ቀመስ ግለሰቦች የሚዘልቀው የክህደት ልቃቂት ቢተረትሩት አያልቅም፡፡

የግል ጥቅም ያልሆለላቸው፣ የህዝብ እና የሀገር አደራ የማይቆረቁራቸው ግለሰቦች ያለ ይሉኝታ ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው ሲበሉ በትዝብት ተመልክተናል፡፡ በአንፃሩ የአብራኳ ክፋይ ያልሆኑ የመንፈስ ልጆቿ ከተለያዩ የዓለም ጥጋ ጥጎች አለንልሽሲሏት ይስተዋላል፡፡

በዕድሜ ዘመናቸው የሰበሰቡትን ጥሪት እና ያካበቱትን ዕውቀት ሳይሰስቱ፤ ለብልጽግናዋ እና ለህዝቧ የኑሮ መሻሻል ያለመታከት ደፋ ቀና ብለዋል፡፡ ተረኛው የመንፈስ ልጇ ጄፍ ፒርስ ይመስላል፡፡

ካናዳዊው ፀሐፊ ጄፍ ፒርስ ከሰሞኑ በህዝብ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣውን የኢትዮጵያ መንግሥት በህገ ወጥ መንገድ በኃይል ሊቀይሩ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በድብቅ ሲዶሉቱ የነበሩ ባንዳ ልጆቿን ምስጢር በዝርዝር ይፋ አድርጎታል፡፡

ሙያዊ ሀቀኝነትን በተላበሰ መንገድ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም በርካታ መረጃዎችን እያወጣ የሚገኘው ፀሐፊው፤ የጆ ባይደን አስተዳደርን ጉድ ለዓለም እያጋለጠ ሲሆን የሰሞኑ ማስረጃዎቹ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ እና የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ዓይን የገለጠ ሆኗል፡፡

በተንቀሳቃሽ ምስል ተደግፎ ይፋ በተደረገው ማስረጃ ህጋዊውን የኢትዮጵያ መንግስት ከሥልጣን በማስወገድ አሸባሪውን ቡድን ወደ ሥልጣን ለመመለስ የተቀነባበረው ሴራ በአሜሪካው የሥለላ ድርጅት የተመራ፤ በታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ተቀማጭነታቸውን በአሜሪካ ባደረጉ ተሰሚነት ባላቸው ኢትዮጵያውያን የሚዘወር መሆኑ ታውቋል፡፡

አሸባሪውን ቡድን ወደ ሥልጣን ለመመለስ ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ሰዎች ጋር ሲዶልቱ በማስረጃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ጉዳይ ልቃቂቱ ሲተረተር በቀጥታ ወደ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጓዳ እንደሚያመራ ጄፍ ፒርስ በማስረጃ አረጋግጦ ይፋ አድርጎታል፡፡እነዚህ የጥፋት ኃይሎች የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በሽፋንነት ተጠቅመው እንደሚንቀሳቀሱ ያጋለጠው መረጃው፤ አላማቸውን ለማሳካት ዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ማዕከል (Peace and Development Center International) የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በቋቋም ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው ነው የታወቀው፡፡ በዚሁ ድርጅት አማካይነት የሴራው አካል የሆኑ ዲፕሎማቶች ባሳለፍነው እሁድ ከአሸባሪ ቡድኑ አመራሮች ጋር ውይይቶችን ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ማህበር በአሜሪካ ሊቀመንበር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ ስላጸደቀው ኤች አር 128 ማብራሪያ ሰጠ

የሩሲያውን የዜና ወኪል ስፑትኒክ ዓለምአቀፍን በመጥቀስ ጅፍ ፒርስ እንዳለው፤ ይኸው ዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ማዕከል (Peace and Development Center International) የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት (USAID) እና ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ (NED) ከተባለ ድርጅት ጋር በጥምረት ይሰራል፡፡

ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ (NED) ታዋቂ እና ራሱን የቻለ የሲአይኤ ግንባር ሲሆን እነዚህ ሁለቱ ተቋማት ተቃዋሚ አካላትን በገንዘብ በመደገፍ ከሆንግ ኮንግ እስከ ኒካራጓ ሀገራትን በማመስና ማመሰቃቀል የሚታወቁ እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡ስለ ኢትዮጵያ የሚሟገተው የሶፍትዌር ኢንጂኒየር ኤሊዘር አባተ እንዳጋለጠው፤ ‹‹ዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ማዕከል›› የተሰኘው ድርጅት የተመሰረተው በመስከረም ወር 2013 .ም ሲሆን ጥቅምት 24 ቀን 2013 .ም አሸባሪው ህወሓት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን አጥቅቷል፡፡

ፒርስ እንደሚለው ድርጅቱ በይፋ በድረገጽ ዕውቅና በማግኘት የተመዘገበው በዚያን ቀን መሆኑ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን የሴራው አንድ አካል በመሆኑ ነው፡፡የሰላምና ልማት ማዕከል (Peace and Development Center International) የራሱን ማንነት በሚያስተዋውቅበት የድረ ገጽ ክፍል ሥማቸው ተዘርዝሮ የነበረውን የጥፋቱ አካል የሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ሥም ዝርዝር ወዲያው ከድረ ገፁ ላይ እንዳጠፋው ታውቋል፡፡ እንደ ፒርስ አባባል ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ጉዳዩን ለማድበስበስ ረጅም ርቀት ቢጓዝም እንደ ዕድል ሆኖ፣ አሁንም የእነዚህን ሀገር ሻጭ ግለሰቦች ዱካ ለማግኘት የሚያስችሉ ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡ እናም ‹‹ዱካውን ተከትሎ እስከ መጨረሻው የተጓዘ አካል ወደ ኋይት ሀውስ ሰተት ብሎ ይገባል›› ነው ያለው፡፡

ጉዳዩን በዝርዝር የሚያስረዳው ፀሐፊው፤ አሜሪካ እና መሰሎቿ ሀገራትን ለመፍረስ የሚጠቀሙበትን መንገድ በኢትዮጵያ ላይ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከነጩ ቤተ መንግስት በግልጽ ትዕዛዝ ወርዶላቸዋል ይላል፤ በመሆኑም ይህን ድርጅት በመመስረት ኢትዮጵያውያንን ያለ መንግስት የማስቀረት ውጥኑ ተጀምሯል ባይ ነው፡፡ ከድርጅቱ መስራች አባላት መካከል ሀብታም እና ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ይገኙበታል፡፡ የባህር ማዶ የግል መዋዕለ ነዋይ ኮርፖሬሽን (OPIC) ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን ያገለገለችው እና እ..አ በ2013 በአፍሪካ ከሚገኙ ሃያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣት ሴቶች መካከል አንዷ በመሆን በፎርብስ መጽሔት ምርጫ ውስጥ የተካተተችው ሚሚ አለማየሁ አንዷመሆኗ ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነትና መድረክ ተለያዩ

ሚሚ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን በመጠቀም ፕሬዝዳንት ባይደን እንዲያሸንፉ የቅስቀሳ ስራ የሰራች ሲሆን ባሳለፍነው ሰኔ ወር በትዊተር ድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ ገለልተኛ ዳይሬክተር ሆና ተሾማለች። ፒርስ እንዲህ ይላል፡– ‹‹ባለፉት ሁለት እና ሶስት ወራት ኢትዮጵያን የሚደግፉ በርካቶች የትዊተር አካውንታቸው ይታገድ፤ ይሰረዝ ወይም ህጎቹን ጥሳችኋል ተብለው ማስጠንቀቂያ ይደርሳቸው የነበረ ሲሆን የህወሃት ደጋፊ የሆኑ አካላት በትዊተር አካውንቶቻቸው ማስፈራሪያ፣ የስድብ አስተያየት እና የተሳሳተ ትርክት ሲያሰራጩ ምንም አይባሉም፡፡›› በመሆኑም የሚሚ ዋነኛ ተልዕኮዋን እየተወጣች ነው ይላል፡፡

ሌላው የድርጅቱ መስራች አባል ዳንኤል ዮሃንስ በምጣኔ ሀብት ትብብር እና ልማት ድርጅት የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ሲሆን፤ በአሜሪካ መንግስት እና በመሰሪው ግብረ ሰናይ ድርጅት መካከል አገናኝ ነጥብ ሆኖ አገልግሏል፡፡

እነዚህ ግለሰቦች የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በነሐሴ ወር ወደ አዲስ አበባ ከመጓዙ በፊት እሱን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመዶለት ወደ ኋይት ሀውስ ከተጋበዙ ኢትዮጵያውያን መካከል እንደሚገኙበት መረጃው ጠቁሟል፡፡

ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሾሙ የተደረገውን ዘመቻ ስትመራ የነበረችው እና በኋላም ዋና አማካሪ የሆነችው ሰናይት ፍሰሀ በዚህ ሴራ ውስጥ ከመጀመሪያው ጀምሮ እጇ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ቴድሮስ አድሀኖም በማህበራዊ መገናኛ ገፆች ላይ ለወያኔ ያለውን ሀዘኔታ በግልፅ ሲያሳይ የነበረ ዋናው ሰው እንደሆነ ልብ ይሏል።ካሳሁን ከበደ ወይም ‹‹ካሲ›› የቀድሞ አትራፊ የግል ድርጅት መስራች እና አስተዳዳሪ ሲሆን ከዋሽንግተን ቲንክ ታንክ ግሩፕ ጋር ግንኙነት የነበረው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

‹‹ሀገር እንዴት ማፍረስ ይቻላል፤ ኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ አላት?›› የሚል ፀረ ኢትዮጵያ ጽሑፍ በማዘጋጀት ያሰራጭ እንደነበር ነው የታወቀው፡፡ ከማዕከሉ ጋር በሥም ያልተመዘገበ ግንኙነት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡በርካቶች እንደታዘቡት ታዋቂ ጡረተኞች እና ዲፕሎማቶች ከህወሓቱ ባለስልጣን ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር የተገናኙበትን እና ምስጢራቸው የተጋለጠበትን የቴሌፎን ካሜራ ውይይት የዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ማዕከል አባላት ለማስተባበል እየሞከሩ መሆኑን ፒርስ ገልጧል፡፡በዙም ስብሰባ ላይ ከነበሩ ዲፕሎማቶች መካከል ቲም ክላርክ ብርሃኔን ሲያወድሱ የነበረ ሲሆን፤ ቪኪ ሃድልስተን ህወሀት በቅርቡ ወታደራዊ ስኬት እንደሚያስመዘግብ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዝናብ እጥረት የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው በውስን ጨረታ ስንዴ እንዲገዛ ተፈቀደ

ስቴፋን ጎምፐርትስ እንዲህ የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፤ “…በመንግስትም ሆነ ዐቢይ ዙሪያ በጦር ሰራዊት ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደሚገነዘቡት ተስፋ አደርጋለሁ። ሩጫቸው የትም እንደማይደርስ፤ እሱም ጦርነት ማቆምን እንዲቀበል ወይም ከሥልጣኑ እንዲወርድ ሊያስገድደው ይችላልን?” ሲሉ ስለ ውይይቱ ይዞ ስለሚመጣው ውጤት እያነሱ በግልጽ ተወያተዋል ይላል፡፡ ከሶማሊያ ጡረታ የወጣው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ አሁንም ከአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር አብሮ እየሰራ ሲሆን፤ ዐቢይ እየሰማ አይደለም፡፡ ኦባሳንጆ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ ለማገዝ ንቁ ተሳትፎ አላደረገም፡፡

ሌሎች የሚታዩዋችሁ መልካም እድሎች አሉ?” ሲሉ ሴራቸው በምን መልኩ ፈር ሊይዝ እንደሚችል አንስተው ተወያይተዋል።በተጋለጠው የዙም ስብሰባ ሆን ተብሎ የተሳሳተ መረጃ ቀርቧልበማለት የማስተባበያ መግለጫ ያወጣችው ኢሌኒ ገብረ መድህን ነች ሌላዋ የማዕከሉ መስራች አባል እና የማዕከሉን ድረ ገጽ ያቋቋመች፡፡ በውይይቱ የነበራት ተሳትፎ የሚያሳየው የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት መሰራጨቱ፤ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ዋና የፈጠራ ባለሙያነት ስራዋን እንድታጣ ሰፊ ጥሪዎች እንዲቀርቡ አድረጓል፡፡

ኢትዮጵያውያን በድህነት አቅማቸው አስተምረው ለወግ ማዕረግ ያበቋቸው ከሀዲዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ሀገር የማፍረስ ስራ ላይ መሰማራታቸው ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ ሲገለጥ የሴራው ልቃቂት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል የሚያልፍ ነው ሲል ለነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እውነታ ትልቅ ማረጋገጫ ነው፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዲፕሎማቶችን ከሀገር እስከማባረር የደረሰበትን እርምጃ ትክክለኛነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል፡፡

Suleman Abdela

https://amharic.zehabesha.com/the-tplfs-circle-of-powerful-movers-and-shakers-leads-right-into-joe-bidens-back-yard/

1 Comment

 1. Great Jief Pirse!!! You will have put remarkable point in the world history. Always truth prevails.

  Message to those US and its allies.

  US, it allies and media wings not only accountable to fake news and information, they have to be liable and sue in international criminal court for all mess, sabotage in Ethiopia and tireless effort on supporting terrorist group for dismantling Ethiopia and their plan of establishing confederation states. If truth and justice prevail in United nations and across the world, this actions have to be done. But fake things dominate in the world who will take the initiatives to ask these arrogant countries???????????????

  Ethiopian government action of evacuating some Embassy employees have to be strengthen further and serious actions need on all those who support TPLF group including embassy ambassadors and fake foreign journalist.

  Victory to Ethiopian people.
  Long live to Ethiopia!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.