በዴሞክራሲ ስም የሚፈጸመው ወንጀልና አገር ማፍረስ ሊበቃ ይገባል ሲሉ ሌላኛዋ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጥሪ አቅርበዋል

260241984 2146847782133225 930589756417898280 n በዴሞክራሲ ስም የሚፈጸመው  ወንጀልና አገር ማፍረስ ሊበቃ ይገባል ሲሉ ሌላኛዋ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጥሪ አቅርበዋል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሚስተር ዋንግ ዌንቢን ትናንት በማህብራዊ ገጻቸው ላይ የኢትዮጵያዊያንን የበቃ (#Nomore) የተቃውሞ ዘመቻ መቀላቀላቸውን አስታውቀው ነበር።
ቃል አቀባዩ በዚሁ መልዕክታቸው ላይ “በዴሞክራሲ ስም ምንያህል ወንጀል ተፈጸመ” ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
በዛሬው እለትም የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር እና ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንይንግ በተመሳሳይ #Nomore ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ለተቃውሞ ሲወጡ ይዘዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል አንዱን ሲሆን፤ በግልጽም ቃል አቀባዩ “#NOmore” ሲሉ ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል።
ረዳት ሚኒስትር እና ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንይንግ በመልዕክታቸው “በዴሞክራሲ ስም ምንያህል ወንጀል ተፈጸመ” ሲሉ ምዕራባዊያን አገራትን ተችተዋል።
ቃል አቀባይዋ የተጠቀሙት ምስልም በተመሳሳይ አፍጋኒስታንን፣ ኢራቅን፣ የመንን እና ሶሪያን ፈርሰዋል ቀጣይዋ ተረኛ ኢትዮጵያ ናት ወይ ሲሉ ሰልፈኞቹ የአሜሪካን መንግስት የጠየቁበትን ነው።
አካባቢህን ጠብቅ ‼
ወደ ግንባር ዝመት ‼
ሠራዊቱን ደግፍ ‼
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ዩቲዩብ
(ኢ ፕ ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.