በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረዋል በሚል ላለፉት 2 ዓመታት ከ6 ወራት የታሰሩት የጦር መኮንኖች በህልውና ዘመቻው ምክንያት አቃቢ ህግ ረዥም ቀጠሮ እንዲሰጥ መጠየቁን ተቃወሙ

አማራ ሚዲያ ማዕከል
ህዳር 16 ቀን 2014 .
አዲስ አበባ ሸዋ

ወገኖቻችን በወሎ፣በጎንደር እና በሸዋ በአሸባሪዎች ጥምረት ሕልቆ መሳፍርት ጥቃት እየተፈጸባቸው መሆኑን የሚጠቅሱት የጦር መኮንኖቹ አላጠፋንም፤ አጥፍተንም ከሆነ ዘምተን ህዝባችን እንድንክሰው ይፈቀድልንበሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመንግስት እያቀረቡ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሰሚ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረው በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት ታስረው 2 ዓመት ከ6 ወራት በላይ ያስቆጠሩ የጦር መኮንኖች፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትና የአዴኃን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ከበደ ምስክር የማሰማት ሂደቱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀላቸውም።

አቃቢ ህግ 133 ምስክር አቀርባለሁ ብሎ 84 ካስመሰከረ በኋላ በተከሳሾች በኩል የመከላከያ ምስክር ማሰማት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፤ እስካሁን ከ50 በላይ ምስክሮችን አሰምተዋል፤ የተወሰኑ ይቀራሉ።

ህዳር 16 ቀን 2014 /ቤት ቀርበው የመከላከያ ምስክር የማሰማት ሂደቱ ይቀጥላል ሲሉ በመሃል አቃቢ ህግ ለዘመቻ ህልውና ስምሪት በመደረጉ ባለሙያ ስለሌለ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተከሳሾችም ሆነ የተከሳሽ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ደንበኞች ለረዥም ጊዜ የታሰሩ መሆናቸውን በመጥቀስ የአቃቢ ህግን ጥያቄ ተቃውመውታል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የአቃቢ ህግን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ህዳር 23 ቀን 2013 ቀሪ የመከላከያ ምስክሮች እንዲሰሙ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷል።

በተከሳሾች በኩል ለዘመቻ ህልውናው በመሳተፍ የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚፈልጉ በመግለጽ ፈጣን ፍትህ እንዲሰጣቸው፤ ያ ካልሆነ ደግሞ መንግስት እጁን አስገብቶ በመፍታት እንዲዘምቱ ቢያደርግ መልካም ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በወሎ ያለው ሁኔታ እየተባባሰ ሄዷል | በመርሳ፣ በመሃል አምባ፣ በሲሪንቃና ሌሎች ቦታዎች የትራንስፖርት፣ የንግድና የባንክ አገልግሎቶች ተቋርጧል

አሚማ አጠቃላይ ሂደቱን በተመለከተ ከጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታሰሩ 512 ቀናት ያስቆጠሩት እነ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ቀለብ ስዩምና አስካለ ደምሌ ህዳር 16 ቀን 2014 በነበራቸው ቀጠሮ አለመቅረባቸውን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል።

የፌደራል ማ/ቤቶች አስተዳደር በጸጥታ ችግር ምክንያት በሸዋሮቢት ማ/ቤት የነበሩ እስረኞችን ወደ ዝዋይ እያዘዋወርኩ በመሆኑ የአጃቢ እጥረት ስላጋጠመኝ ለማቅረብ አልቻልኩም እስካደራጅ ድረስ ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱን የተከሳሽ ጠበቆች የመከራከሪያ ፍሬ ነገሮችን በመጥቀስ ተቃውመውታል።

ዳኛም የማ/ቤት አስተዳደር እነ እስክንድር ነጋን በቀጠሮአቸው ለምን እንዳላቀረበ ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማለት ለህዳር 17 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተገልጧል።

ከሁለቱ ጠበቆች ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share