የምዕራብ ጎንደር ዞን የፍኖ እና ሚሊሻ አባለት በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ወደ ግንባር ሽኝት ተደረገላቸው

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
261474662 6411238582284041 1020894288327481918 nበምዕራብ ጎንደር ዞን የፋኖ እና የሚሊሻ አባላት በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ያነጋገርናቸው የሚሊሻ እና ፋኖ አባላት እንደተናገሩት ወራሪው የጁንታ ቡድን በሃገርችን በተለይም በክልላችን ያሉ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ፣ነብሰ ጥሩ፣ ህፃናት ፣መነኩሴዎችን በመድፈር ፣መሠረት ልማቶችን በማውደም ከፍተኛ የሆነ ኢሰባዊ ተግባር ሲፈፅም መቆየቱን ገልፀዋል።
በመሆኑም እኛ እያለን አገራችን መፍረስ የለባትም፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘምተዋል እኛም ወደ ግንባር በመዝመት ሃገራችንና ህዝባች ከስቃይ ለመታደግ ወደ ግንባር እየተሸኘን እንገኛለን ብለዋል።
261024684 6411238445617388 1289152545064459197 nዘማቾች አያይዘዉ እንደገለፁት አሁን የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም አካላት በጉልበቱ ፣በገንዘቡና በእውቀቱ የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል ሲል የገንዳውሃ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.