በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሓትን ለመታደግ የተካሄደው ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋለጠ

አሸባሪው ህወሓትን ከሚቀበርበት ጉድጓድ ለመታደግ የሽብር ቡድኑ አባላትና ምዕራባውያን የጥቅም አጋሮቹ ዲፕሎማቶች ያካሄዱት ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋልጧል።

ብርሃነ ገብረ ክርስቶስና ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅን ጨምሮ የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ የውጭ አመራሮች፤ እንዲሁም የጥቅም አጋሮቻቸው ምዕራባውያንና ዳያስፖራዎች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን ድብቅ ምክክር አካሂደዋል።
260684067 5029745430390626 3123158548309032716 n በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሓትን ለመታደግ የተካሄደው ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋለጠ
ከዚህ በተጨማሪ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ እና የቀድሞ የአሜሪካ የመከላከያ የአፍራካ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ቪኪ ኹደልስተን፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን በስብሰባው ከተሳተፉት መካከል ናቸው።
በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ “በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስትን ልናስቆመው አንችልም የአፍሪካ ህብረት የወከላቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትም ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እኛ እንደምንፈልገው አልተንቀሳቀሱም” ማለታቸው ታውቋል።
እንደምንም ብለን አሁን በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በማውረድ የምንፈልገውን የሽግግር መንግስት ማቋቋም ይኖርብናልም ሲሉም ነው የዶለቱት፡፡
በድርድርም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ የአሸባሪውን ህወሓትና የጥቅም አጋሮቹን ፍላጎት የሚያስፈጽም መንግስት መቋቋም እንዳለበት የተነሳ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶችን ጨምሮ ሌሎች አካላትን መጠቀም ይጠበቅበናል ሲሉ ከንቱ ዕቅዳቸውን አቅርበዋል።
በሌላ በኩል አሸባሪውን ቡድን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች አሸባሪውን የሚደግፉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን የማግባባት ሥራ ከመጋረጃ ጀርባ እያከናወኑ መሆኑም በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ ተዳሷል።
አሸባሪውን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት በዲፕሎማሲው መስክ ጫና ለማሳደር መንቀሳቀስ እንደሚገባም በሚስጢር መዶለታቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በዋሺንግተን ዲሲ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ዘጠኝ ሲሆኑ÷
1. ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ
2. ዶ/ር ኢሌኒ ገ/መድህን
3. አምባሳደር ብረሃነ ገ/ክርስቶስ
4. ፕ/ር ጥላሁን በየነ
5. አምባሳደር በቀለ ገለታ (ቀይ መስቀል)
6. ዶ/ር ታደሰ ወሂብ (CDC)
7. ወ/ሪት ኩለኒ ጀለታ (Uscongress) እንዲሁም ሁለት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።
EBC

2 Comments

 1. Well, whether this is true or False, it is neither new nor surprising at all! Because the political elites of the politics of either Oromization who the most important allies of TPLF are are who are parts and parcels and advisors and decision makers of the Arat Kilo palace. It is self-evidently true that the difference is one faction or junta of EPRDF is out of the palace politics and the one (the previous mastermind -TPLF) is in the Mekele palace and now fighting back and marching all the way down the capital, Addis Ababa which has made ABYI and his stupid and deadly opportunist cronies terribly frustrated and engage in a hopeless attempt to save not either democracy nor the unity of the country but their own on notoriously terrible political agenda and power. This comment of mine may sound bad, but if we really want to get rid of this kind of terribly notorious and deadly political game once and for all, we desperately need to talk clearly and straightforwardly! Until we get this kind of courage and a sense of patriotism to do, there is no and there will not be any other miracle to do it on our behalf at all! Yes, the very political culture of decrying and treating the very symptom of the very deadly illness, not the very root cause of it which is the political agenda and practice of TPLF/EPRDF/Prosperity is a very stupid and self-defeating political mentality and behavior! IT is from this very tough reality that the above piece of writing and the like are very clumsy if not extremely deceiving or misleading!

 2. ለምን ወሬውን ማግነን እንዳስፈለገ አይገባኝም። ኢትዮጵያውያን አንድ ችግራችን የራሳችንን ግዴታ ሳንወጣ ስለ ሌላው ማራገብ እናበዛለን።
  ይህን ስብሰባ ያቀናጀው የህወሓቱ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ነው፤ እራሱን እንደ መሓከለኛ አድርጎ ጥያቄ እንደሚመልስ መስሎ እያስተባበረ ነው።
  1/ የውጭ ጦር ኢትዮጵያን እንዲወርር ለመጋበዝ
  2/ አዲስ አበባ መግባት አንሻም ለማለት (ፍላጎታችን ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ ብቻ ነው ለማለት)
  3/ ህወሓትን እንደ ተበዳይ፣ እንደ አገር አልሚ፣ እንደ ሰላም ፈላጊ አድርጎ ለማቅረብ

  ጥያቄው፦ ኢትዮጵያውያን ለምን ይህን የመሰለ ስብሰባ ለማቀናበር አልቻሉበትም?
  ብርሃነ ገ/ክ፣ ስዬ አብርሃ፣ ወዘተ ስንት በደል በአገርና በሕዝብ ላይ ፈጽመው፣ ገንዘብ ዘርፈው አሜሪካና አውሮጳ ተዝናንተው ተቀምጠዋል።
  እንደ አርአያ ተስፋማርያም፣ ገ/መድህን፣ ወዘተ (ይልቁን የኢትዮጵያ መንግሥት) ብዙ መረጃ አለ። ታዲያ የህግና የፋይናንስ ባለ ሙያዎች ለምን ክስ አይመሠርቱም?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.